Semayawi Thought

Semayawi Thought Equipping Ethiopian Christians to renew their minds through this media, serve the church and create culture to the glory of God

Semayawi Thought is a nonprofit online magazine published in Amharic and English both, a platform for Ethiopian Evangelical Christians Professionals and for those who are attracted in Semayawi (heavenly) thoughts. Our online magazine is much more than a blog, which is simply a chronological list of posts focused on publishing different types of spiritual contents and devoted to personal and spirit

ual growth. Together as a community, we will experience the fullness of life, grow spiritually and personally. For those of you who have been wishing to read and write your deepest reflections and ideas for Ethiopian Churches, Semayawi Thought will provide you opportunities. On Semayawi Thought, we issue a spiritual perspective on world events as well as tools for your spiritual practice, all based on Bible. Filled with convenient as well as inspirational content, hoping it will change your life. And don't miss our ever-expanding line of bringing quality contents to Ethiopian Christians!

"ተርጓሚዎቹ ሆነ ብለው እንጂ ባለማወቅ አላደረጉትም!"  ዕለተ ዕሁድ፣ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የተገመገመው መጽሐፍ በዓይነቱ ለየት ያለ ነበር። ርዕሱ፣ "ተፋልሶ...
18/11/2025

"ተርጓሚዎቹ ሆነ ብለው እንጂ ባለማወቅ አላደረጉትም!"

ዕለተ ዕሁድ፣ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የተገመገመው መጽሐፍ በዓይነቱ ለየት ያለ ነበር። ርዕሱ፣ "ተፋልሶ" ይሰኛል። ጸሐፊው፣ ከጥቂት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የግሪክ ቋንቋ መምህር የነበሩ፣ መምህር ጌታቸው ተረፈ ሲሆኑ፣ መጽሐፉን የገመገሙት ደግሞ የሥነ መለኮትና የግሪክ ቋንቋ መምህሩ፣ አክሊሉ ኩማ ነው። ገምጋሚው የመጽሐፉ አዘጋጅ ለደከሙት ድካም እውቅናን የቸረ፣ ሥራቸው ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስላለው ፋይዳ በስፋት የተነተነ ሲሆን ጥቂት ቢታከሉ ያላቸውን ሃሳቦችም አክሏል።

መጽሐፉ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር፣ በ2000 ዓ.ም ባሳተመችውና፣ "የሚሊኒየም መጽሐፍ ቅዱስ" የሚል ስያሜ በተቸረው አዲስ ትርጉም ላይ ያጠነጥናል። ይህ ትርጉም ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ አንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ ከፍተኛ ሙግት ሲነሳበት ቢቆይም እንደ መምህር ጌታቸው ድምጹን ከፍ አድርጎ የጮኸ ለመኖሩ ግን እርግጠኛ ዓይደለሁም። ከእሁድ ዕለቱ ስሜታቸው እንደታዘብኩት ደግሞ ዛሬም ድረስ እንኳ ድንጋጤው እና የልብ ሀዘኑ አለቀቃቸውም።

በመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሥራ ውስጥ የሚነሱ ሙግቶች በአብዛኛው በቃላት ምርጫና በአተረጓጎም ዘዴ ላይ የሚያተኩሩ መሆናቸው የተለመደ ቢሆንም መምህር ጌታቸው ተረፈ፣ በሚሊኒየሙ ትርጉም ላይ ያነሱት ምሁራዊ ሙግት ግና ጉዳዩን ከቀላል የትርጉም ሙግት ወደ ሌላ፣ እጅግ ከባድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። በተለይም የቤተ ክርስቲያኒቱ የታወቀ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ አካል የሆነ ሰው፣ አንድን ይፋዊ የቤተ ክርስቲያን እትም፣ "ተፋልሶ" ብሎ የተቃውሞ መጽሐፍ እስከመጻፍ መድረሱ የርዕሰ ጉዳዩን ክብደትና ጥልቀት ያሳያል።

ለመምህር ጌታቸው የዚህ እትም በስህተት መሞላት የአጋጣሚ ስህተት ሳይሆን ሆነ ተብሎ የተደረገ፣ እውነትን የመበረዝ ተግባር እንደሆነ ተቆጥሯል። ተርጓሚዎቹ "ባለማወቅ ተሳስተዋል" ሳይሆን "ሆን ብለው መሠረታዊ የሆኑ አስተምህሮዎችን ለመለወጥ ሞክረዋል" የሚል ሙግትም አላቸው። ለዚህ ሥራ ግብረ መልስ የሰጡበት፣ "ተፋልሶ" የተበረዙትን ሃሳቦች ከቀደምት ምንጩ፣ የግሪክ ቋንቋ ጋር "በንጽጽር የሚያሳይ" መሆኑ፣ ጬኸታቸው በስሜት ወይም በወሬ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፣ ማስረጃዎችን በማቅረብ ስልታዊ በሆነ መንገድ የቀረበ መሆኑን ሥራቸውን ተዓማኒ ያደርገዋል።

መምህሩ ሙግታቸው በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ወደ ሕዝብ እጅ እንዲገባ ከማድረጋቸው አስቀድሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ እና ለሊቃውንት ጉባኤ፣ ከዚያም ተሻግረው ለመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ሙግታቸውም ቢያቀርቡም ጥያቄያቸው ከየትኞቹም አካላት መልስ ሳያገኝ በመቅረቱ እጅግ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ይህ ማለት ደግሞ ችግሩ የትርጉም ስህተት ብቻ ሳይሆን፣ የተቋማዊ ምላሽ አልባነትና የአመራር ቀውስ ጭምር መኖሩን በግልጽ ያሳያል።

እንዲያም ሆኖ መምህሩ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የሄዱበት መንገድ ሥርዓትን የጠበቀና ለአንድ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ የሚገባውን ኃላፊነት የተሞላበት ተግባር ነው። ጉዳዩን በቀጥታ ወደ ሕዝብ ከማድረሳቸው በፊት፣ ለሚመለከታቸው የበላይ አካላት፣ ማለትም ለቅዱስ ሲኖዶስ እና የሊቃውንት ጉባኤ አቅርበዋል። ይህም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓትና መዋቅር ያላቸውን አክብሮትና የሙግት አቀራረባቸውን ጨዋነት ያሳያል። የመጽሐፉ ገምጋሚ፣ ወንድም አክሊሉ ለማም ይህንኑ አክብሮት በመጽሐፉ ውስጥ መመልከቱን በአድናቆት ገልጾታል።

መምህሩ፣ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስን የማስተርጎምና የማሳተም ሥልጣን ላለው የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበርም ጭምር ማብራሪያ ጠይቀው ምላሽ ማጣታቸው "ተፋልሶ" የተሰኘውን መጽሐፍ የማሳተማቸው የመጨረሻ አማራጭ ሆኗል። ባጭሩ፣ መምህሩ ወደ ሕዝብ የወጡት በሮች ሁሉ ከተዘጉባቸው በኋላ ነው። የዚህ ውሳኔያቸው ዓላማ አንዳንድ የዋሃት እንደሚያስቡት ቤተ ክርስቲያንን የማጥቃት ሳይሆን፣ ምላሽ ያጣው እውነት ድምጽ እንዲያገኝ የማድረግን፣ የሕሊናን ግዴታ መወጣት ነው። ለዚህም ነበር የዕለቱ መርሀ ግብር አሳላጭ፣ መጋቢ መርዓዊ ንጉሤ፣ "ኢትዮጵያዊው ሉተር" ያላቸው።

መምህር ጌታቸው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ እና የሌሎች አካላት ዝምታ እና ቸልተኝነት የእግር እሳት ሆኖ ቢያንገበግባቸውም በእኔ ዕይታ ግን ጉዳዩ ከተራ ቸልተኝነት የከበደ ትርጉም አለው። ዝምታው በዋናነት ለቀረበው ሙግት መልስ መስጠት አለመቻልን ያሳያል። በመምህሩ የቀረበው ማስረጃ በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ፣ ሊቃውንቱ ሊከላከሉት እንዳልቻሉም ነው የምቆጥረው። ሌላው ግምቴ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ በይፋ ያሳተመችውን መጽሐፍ፣ "ተሳስተናል" ብሎ መቀበል፣ ለብዙዎች ከባድ ውርደት ስለሚመስላቸው ዝምታን እንደ መከላከያ ተጠቅመውበትም ሊሆን ይችላል የሚል ነው።

እናም የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት አሁን ላይ ሸክሙ በምዕመኑ ጫንቃ ላይ ወድቋል፣ ያሳዝናል! ውሎ አድሮም ቢሆን፣ "የትኛው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ትክክለኛው?"፤ "ማንን ነው ማመን ያለብን?" የሚሉ የብዥታ ጥያቄዎች በምዕመናን ዘንድ መፈጠራቸውም አይቀሬ ነው። ዝምታው በከፍተኛ ደረጃ መተማመንን ይሸረሸራል። ምዕመኑ በመሪዎቹ ላይ ያለው እምነት በእጅጉ ይጎዳል። "ይህን ያህል ትልቅ ጉዳይ ደብቀው ዝም ካሉ፣ በሌላ ምን ጉዳይ ላይ ልናምናቸው እንችላለን?" የሚል ጥያቄም ይፈጥራል።

መምህር ጌታቸው ተረፈ፣ በዕለቱ፣ "ይህቺ መጽሐፍ ቅዱስን እና ክርስትናን ለሺ ዘመናት ጠብቃ ያቆየች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን በዚህ ደረጃ መበረዝ አይመጥናትም!" ማለታቸውም ከዚህ ቁጭታቸው ይነሳል። ይኼ አባባላቸው በጣም ልብ የሚነካና የጉዳዩን ክብደት በአንድ ዐረፍተ ነገር ያጠቃለለ ንግግር ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አባባሉ ከተራ የአካዳሚክ ሙግት የዘለለ፣ ጥልቅ የሆነን የልብ ስብራት ያስተዋልኩበት ነው። መምህሩ፣ የሚሊኒዬሙ ትርጉም ዓለም አቀፋዊውን የመጽሐፍ ቅዱሰ ትርጉም ደረጃ ያልጠበቀ፣ በይዘቱ "ሴክቴሪያን" ወይም የአንድ ቡድን አስተምህሮ ብቻ ለማንጸባረቅ የተዘጋጀ መጽሐፍ ለመሆኑ አጽንኦት መስጠታቸውም በቤተ ክርስቲያናቸው እንዲህ ያለ ከባድ መሳት ያደረባቸውን ቁጭት ያሳያል።

መምህር ጌታቸው፣ ከዓለም አቀፋዊው ትርጉም በተለየ መልኩ የራስ እምነት ማንጸባረቂያ እንዲሆን ተደርጎ፣ እውነትን በሚያፋልሱ 596 ቃላት የተቀሽበውን፣ የሚሊኒዬሙን ትርጉም ያነጻጸሩት፣ ከይሖዋ ምስክሮች፣ "የአዲስ ዓለም ትርጉም" ከተሰኘ እትም እና ራሱን፣ "የኋለኛው ቀን ቅዱሳን" ብሎ ከሚጠራው "ዘ ቡክ ኦፍ ሞርሞንስ" ከተባለ የሃይማኖት መጽሐፍ ጋር ነው። መምህሩ፣ የሚሊኒየሙን ትርጉም ከእነዚህ ሁለት መጻሕፍት ጋር ሲያነጻጽሩ፣ በይዘት ፍጹም አንድ ናቸው እያሉ ሳይሆን ይልቁንም፣ የተጠቀሙበት ዘዴ እና ያስከተሉት ውጤት ተመሳሳይ በንጽጽር ለማሳየት የተጠቀሙበት ምሳሌ ነው።

እንግዲህ በሚያሳዝን ሁኔታ ይኼ ሸክም ቀኝና ግራውን በማያውቀው ሕዝበ ክርስቲያን ጫንቃ ላይ ወድቋል። ትናንት ያየሁት የመምህር ጌታቸው ተረፈ ውስጥን የሚያናውጥና አንጀትን የሚያላውስ ቁጭትም ይኼ ሕዝብ ከአምላኩ ጋር የሚገናኝበት፣ ኀጢአቱን ተገንዝቦ፣ በእርሱ አምኖ የሚድንበት ግልጽ የወንጌል መልዕክት ተበርዞ በመቅረቡ ነው። በመጨረሻም የእሳቸው ጩኸት የእኛም ጩኸታችን እንዲሆን አደራ ብለዋልና ይኸው እኔም ጩኸቴን አስተጋብቻለሁ። በእሳቸው በኩል ቁጭቴን ለአራተኛ ጊዜ ተንፍሻለሁ። እናንተም በምትችሉት መንገድ ይህንኑ ታደርጉ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ። የዕለቱ መርኃ ግብር እና የመምህሩ ምላሾች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በሕንጸት ድረ ገጽ ላይ ስለሚጫንም ትመለከቱት ዘንድ ግብዣዬ ነው።

© ሽመልስ ይፍሩ

negerechristina

11/11/2025

“ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።”
2ጢሞ. 4:3

መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ፣ ሰኔ 29፣ 2017 ዓ.ም. በ17ኛው የመካር መድረክ ተገኝተው፣ ተወዳጅ ዝማሬዎቻቸው እንዴት እንደተጻፉ በተናገሩበት ወቅት፣ የአጻጻፍ ታሪካቸውን ከነገሩን ዝማሬዎች መካከ...
23/09/2025

መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ፣ ሰኔ 29፣ 2017 ዓ.ም. በ17ኛው የመካር መድረክ ተገኝተው፣ ተወዳጅ ዝማሬዎቻቸው እንዴት እንደተጻፉ በተናገሩበት ወቅት፣ የአጻጻፍ ታሪካቸውን ከነገሩን ዝማሬዎች መካከል “የአደባባይ ሰው ሆነህ” የሚለው አንዱ ነበር፡፡ ሙሉውን ይመልከቱ፡፡

መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ፣ ሰኔ 29፣ 2017 ዓ.ም. በ17ኛው የመካር መድረክ ተገኝተው፣ ተወዳጅ ዝማሬዎቻቸው እንዴት እንደተጻፉ በተናገሩበት ወቅት፣ የአጻጻፍ ታሪካቸውን ከነገሩን ዝማሬዎች መካከ.....

“የምስጋና ገጾች” የተሰኘው በወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ግለታሪክ ላይ የተመሰረተው መጽሐፍ መስከረም 04/2018 ዓ/ም በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቤተ ክርስቲያን (IEC) ከቀኑ 9፡00 ሰአት ጀ...
05/09/2025

“የምስጋና ገጾች” የተሰኘው በወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ግለታሪክ ላይ የተመሰረተው መጽሐፍ መስከረም 04/2018 ዓ/ም በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቤተ ክርስቲያን (IEC) ከቀኑ 9፡00 ሰአት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ይመረቃል፡፡
እርስዎም በዕለቱ በተጠቀሰው ሰአት እና ቦታ እንዲገኙ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል፡፡

መረመርከኝ / ካንተ ወዴት - Loma Kejela I Kenessa Bula, Dawit Getachew, Etana Disasa
14/07/2025

መረመርከኝ / ካንተ ወዴት - Loma Kejela I Kenessa Bula, Dawit Getachew, Etana Disasa

መረመርከኝ / ካንተ ወዴት - Loma Kejela I Ft. Kenessa Bula, Dawit Getachew, Etana Chemeda“ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምን....

05/07/2025

ቤተክርስቲያን ዙሪያ ገባው ላይ ለሚሆን ነገር ግድ የሚሰጣት አይደለችም። በከባቢዋ የሚከወነው ነገር የሚሞቃትም ሆነ የሚበርዳት አትመስልም። ሰዎች ቢጨፈጨፉ፣ በረሃብ የሚረግፉ ህጻናት ቢኖሩ፣ የማንነት ጥቃቶች ቢበራከቱ፣ የጦርነት ቅርሻት ቢስፋፋ፣ የኑሮ ውድነት ምግብ አጥና ቤት አልባ ቢያረግ.... ቤተክርስቲያን ግድ አይላትም። አስደንጋጭ ነገር ሰፈሯ ቢከመር ላለማየት፣ ላለመስማትና ላለመናገር የተገዘተች መስላለች።

ቤተክርስቲያን በማሕበረሰቡ መኸል መኖሯ ተዘንግቷት ከሚያዝነው ጋር ማዘን፣ ከሚያለቅሰው ጋር ማልቀስ፣ የተጠቃውን ማጽናናት ከብዷታል። ነብያዊ ድምፅ እንድትሆን የተጠራች እንባ እንኳን ማዋጣት ዳገት መቧጠጥ ሆኖባታል። ብዙዎች እየሞቱ እሷ ምንም እንዳልተፈጠረ ጉዳዮዋን ታሰናዳለች፤ business as usual ነች።

አምሳለ መለኮት የሆነው ሰው ሲገደል፣ ሲታረድ፣ ሲሰደድና ሲጠቃ ቤተክርስቲያን ድምጽ መሆን ቢያቅታት አብራ ማልቀስ ግዴታዋ ነበር። ስንት ዳገት የሆነ ተግባራዊ እርምጃ በዙሪያችን ተደርድሮ በዝማሬና በስብከት የሚደረገው ነገር እንደ አደንዛዥ ዕጽ ከእውነታው እንድንፋታ በቤተክርስቲያን ታስቦ የተደረገ ይመስለኛል።

እስኪ የአምልኮ መርኀ ግብር ሁሉ ዝም ይበል፤ እንደርሰበት የለ?! ቤተክርስቲያን ማልቀስ አሻፈረኝ ካለች ዝም ትበል። እስኪ እኛ ራሳችን ዝም እንበል። ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት አገር በዝማሬ የሚደረገው ቱማታ ጣሪያውንስ ያልፋል? ምንም እንዳልተፈጠረ መሆንስ «በመፈራረሳችን ከመሳቅ» (ሰቆ 1፥7) ይለያል? «በወይን ሸለቆ እንደተረገጠችው የይሁዳ ልጅ» ስንረገጥ አብሮ ሙሾ ከማውረድ ይልቅ የምንም አልተፈጠረም ክህደት በቁስላችን ላይ እንጨት ከመስደድ ይለያል? ሙሾ ማውረድ ባትችሉ ዝም ብትሉንስ?! እንባችን ላይ ከምትዘባበቱ ዝም በሉን! እንባችንን ተውልን!

Amanuel Assegid

28/05/2025

Address

Dembel City Center 12th Floor
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Semayawi Thought posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Semayawi Thought:

Share