
07/10/2024
#መልዕክት
ከደቂቃዎች በፊት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 ተመዝግቧል።
ይህ ክስተት ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በ165 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ አካባቢ የተከሰተ ነው።
ሆኖም የዚህ መሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በደሴ መስመር እስከ ኮምቦልቻ፣ አዲስ አበባ፣ መተሃራ እና ሌሎችም ቦታዎች ድረስ ተሰምቷል። ባለፉት ቀናት አነስተኛ መጠን ያላቸው ተመሳሳይ አይነት የመሬት ንዝረቶች ሲያጋጥሙ መቆየታቸውንም ባለሙያዎች አመልክተዋል።
በዛሬው ሁኔታ አዲስ አበባ ላይ ከዚህ የከፋ ሁኔታ ሊያጋጥም እንደማይችልም ባለሙያዎቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዜጎች የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥምበት ወቅት ባለመደናገጥ ራሳቸውን ከአደጋ ሊጠብቁ ስለሚችሉባቸው መንገዶች መረጃ ሊይዙ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የጥንቃቄ መልእክቶቹን እና የዘርፉን ባለሙያዎች ምክረ ሃሳቦች ከመገናኛ ብዙሃን እንድትከታተሉ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።