liyumedia.net

liyumedia.net Media/News National Company which circulates its news and programs worldwide via Liyumedia page.

Liyumedia.com is Broadcasting & Media Production Company ¡ founded on july,8 2013.

15/01/2025
 Discussion on the next phase of money mining & how to dollar digging 🙄
18/12/2024


Discussion on the next phase of money mining & how to dollar digging 🙄

አሰባውያን ተቆጥተዋል።ኢትዮጵያ የሱማሌ ችግሯን ስለፈታች ወደእኛ ፊቷን ታዞራለች በማለት ኢሳያስ ከዓመታት በኋላ አሰብ ሄዶ ከህዝብ ለመወያየት ሰሞኑን አሸዋ ላይ ተቀምጧል። በአካባቢው ያሉ የ...
14/12/2024

አሰባውያን ተቆጥተዋል።

ኢትዮጵያ የሱማሌ ችግሯን ስለፈታች ወደእኛ ፊቷን ታዞራለች በማለት ኢሳያስ ከዓመታት በኋላ አሰብ ሄዶ ከህዝብ ለመወያየት ሰሞኑን አሸዋ ላይ ተቀምጧል። በአካባቢው ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአፋር ዜጎች ይሄ ሰውዬ ያሾፋል ብለው ቀልደውበታል። ሲመቸው ጠፍቶ እና ሲጨፈጭፈን ብሎም ሲያደኸየን ኖሮ ሀገራችንን ህዝብ አልባ አድርጎ አሁን ደግሞ ለጦርነት ተዘጋጁ ይለናል። እኛ አሰባውያን ደግሞ እያልን ያለነው የዶክተር አብይ ኢትዮጵያ በመጣችና በገላገለችን በሚል ውስጥ ለውስጥ ሲነጋገሩ ተደመጠዋል። ወዲ አፎም መሄዱ፣ ለጦርነት ተዘጋጁ ማለቱን እንደ ህዝባዊ ውርደት አሰባውያን ወስደውታል። እዚያ ያለው የአፋር ህዝብ ከምንግዜውም በላይ ተበሳጭቷል። በብዙ መልክ ህዝባችንን ጨርሶ፣ ጨፍጭፎ፣ አደህይቶ ሽማግሌው በአፋር ህዝብ ላይ ያላግጣል። አሁን ደግሞ አንከባክቦ ያስቀመጠው ህዝብ ያለ ይመስል ለዘመናት ሄዶ የማያውቀውን ድንገት መጥቶ ለጦርነት ተዘጋጁ ይላል፤ ይህ ቆሻሻ ነው። ልክ እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ የሚፈሰው የኢሳያስ አፈወርቂ ዘመን at least በአሰብ አብቅቷል።

መክሸፍ እንደ ሽፍታዉ ፋኖበኦሮሚያ ክልል ሰላሌ ዞን አሰቃቂና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በሰው ልጅ ላይ ሲፈጸም የሚያሳየውን ቪድዮ ተመልክተናል። እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ነገር እየፈጸሙ በቪዲዮ ደግሞ...
20/11/2024

መክሸፍ እንደ ሽፍታዉ ፋኖ
በኦሮሚያ ክልል ሰላሌ ዞን አሰቃቂና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በሰው ልጅ ላይ ሲፈጸም የሚያሳየውን ቪድዮ ተመልክተናል። እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ነገር እየፈጸሙ በቪዲዮ ደግሞ ቀርጾ ሕዝብ እንዲመለከተው መላክ፣ ሕዝብን በሕዝብ ላይ ለማስነሳት የተደረገ ሴራ እንደሆነ ማንም አያጣውም። ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አካባቢዎች እንደዚህ ዓይነት አሳፋሪ ድርጊቶች በቪድዮ እየተቀረጹ ሲለቀቁ እንደነበር እናስታውሳለን። ድርጊቱ አስጨናቂም አሳፋሪም ነው፣
ነፍስ ይማር!

ፍትህ ፍትህ ፍትህ ለመምህራን የዚህን መንግስት መጨረሻ ያሳየኝ  አሁንም እጮሃለዉ ፍትህ ፍትህ ለመምህራን  አሁን አሁን እየናፈኩት ያለሁት ቀን የዚህን መንግስት መጨረሻ የማይበትን ቀን ነዉ ...
03/11/2024

ፍትህ ፍትህ ፍትህ ለመምህራን

የዚህን መንግስት መጨረሻ ያሳየኝ አሁንም እጮሃለዉ ፍትህ ፍትህ ለመምህራን አሁን አሁን እየናፈኩት ያለሁት ቀን የዚህን መንግስት መጨረሻ የማይበትን ቀን ነዉ ፡፡ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ኑሮ እሳት ይሆናል ተብለን ጆሯችን አስኪደነቁር ድራማ ሰሩብን ፡፡ እንደተጠበቀዉ ባይሆንም ግን እሳቱም ባይሆን ወላፍኑ የነካቸዉን የማህረሰብ ክፍሎች ደገፍ ደገፍ አድርጎ ግራ እያጋባን ዘለቀ ፣ አሁን ደግሞ የተማሪዎች ምገባ ይቆማል ፣ በጀት የለም ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ተማሪ በየቀኑ መመገብ አይቻልም ፣ ወዘተረፈ ምክንያቶች ተደርድሮ ይቆማል ብለን ስንጠብቅ ጭራሽ ይዉጣላችሁ ብሎ የቀለም አባቶች የእዉቀት ማዕዶች የጥበብ ሀይቆች መምህራንን እኔዉ እራሴ እመግባቸዋለዉ እያለን ነዉ ፡፡

አስባችሁታል በየትምህርት ቤቱ የነበሩ የመምህራን ካፍቴሪያዎች ዋጋ ከዉጭ ዋጋ እጅግ ቅናሽ እንደሆኑ ታዉቃላችሁ እሱስ ለማን ሲባል ተብሎ በነፃ መምህራኖቻችን ጥራት ያለዉ ምግብ ሲቀርብላቸዉ ጉድ ነዉ … የአዉርቶ አደሮች ጉሮሮ ላይ መቆም ግን Fair አይደለም ፡፡ መምህራን ተሰቃዩ ሲሉ ከርመዉ አሁን ምን ሊሉ ይችላሉ ያዉ የህልዉና ጉዳይ ስለሆነ የመምህራን ልጆች ተሰቃዩ ማለታቸዉን ይቀጥላሉ ፣ ልጆቻቸዉም መፍትሄ ሲያገኙ የልጅ ልጆቻቸዉ …. ብቻ ጉዱን ለማየት ጓጉቻለዉ

በአዲስ አበባ የሚኖሩ አንድ ባለሀብትን በማገት 20 ሚሊዮን ብር የተቀበሉ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ አጋቾቹ 20 ሚሊዮን...
02/08/2024

በአዲስ አበባ የሚኖሩ አንድ ባለሀብትን በማገት 20 ሚሊዮን ብር የተቀበሉ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ
አጋቾቹ 20 ሚሊዮን ብር የተቀበሉት 100 ሚሊዮን ብር ካልከፈላችሁ በሚል ከብዙ ድርድር በኋላ እንደነበር አገልግሎት መስሪያ ቤቱ አስታውቋል

-----------------------ዝርዝር መረጃዎ እንደሚከተለው ቀርቧል ----------------
አቶ እንግዳው ውዱ የተባሉት ግለሰብ ቡና ወደውጭ በመላክ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሀብት ናቸው፡፡ ግለሰቡ ያላቸውን የሀብት ሁኔታ ሲያጠኑ የቆዩት በእገታው የተሳተፉ ግለሰቦች፤ ስለባለሀብቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለማጥናት አንድ መኪና በቀን እስከ 1300 ብር ተከራይተው በአዲስ አበባ ውስጥ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡
አጋቾቹ ሲያደርጉት የነበረውን ጥናት አጠናቀው ባለሀብቱ እንዲታገቱ ውሳኔ ላይ ከደረሱ በኋላ፤ ግለሰቡን በአዲስ አበባ በተለምዶ ቦሌ ቡልቡላ 93 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲወጡ መንገድ በመዝጋት አግተው ከአዲስ አበባ ወደ አዋሽ መልካሳ በመውሰድም በታጋቹ ስልክ ለቤተሰብ በመደወል 100 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ መደራደራቸውን የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ መረጃ ይጠቁማል፡፡
ይህ ጥቆማ የደረሰው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፤ ታጋቹን በሙሉ ጤንነት፣ እንዲከፍል ከተጠየቀው ገንዘብ ጋር ለመመለስ እና አጋቾችን በቁጥጥር ስር በማዋል በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የመረጃ ኦፊሰሮችን ክትትል እንዲያደርጉ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ኦፕሬሽን እንዲያካሂዱ ስምሪት መስጠቱን አመልክቷል፡፡

ይህ በህቡእ ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰባት አባላት ያሉት የአጋቾች ስብስብ፤ የታጋቹን የአቶ እንግዳው ውዱን ቤተሰቡ 100 ሚሊዮን ብር እንደኪፈል በተደጋጋሚ በሞባይል ስልክ በመደወል ሲወተውት መቆየቱንና አንከፍልም ካሉ ግን ግለሰቡን በመግደል ሬሳውን በር ላይ እንደሚጥሉ ማስጠንቀቃቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ ይጠቁማል፡፡
ይሁንና የታጋቹ ቤተሰቦች 100 ሚሊዮን ብር መክፈል እንደማይችሉ፤ የቤተሰቡን አባወራ ሕይወት ለመታደግ ሲሉ 20 ሚሊዮን ብር እንደሚከፍሉ ያሳውቃሉ ይላል መግለጫው፤ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተል የአጋቾችን መውጫ እና መግቢያ እንዲሁም የግንኙነት መረብ በሚስጥር ሂደቱን ይከታተል እንደነበር በማመልከት፡፡

ታዲያ በዚህ መሀል አጋቾቹ የገንዘብ ቅብብሉ በዲጂታል አልያም በባንክ ከሆነ እንያዛለን በሚል ታጋቹን ለመልቀቅ የተስማሙበትን 20 ሚሊዮን ብር ለአያያዝ እንዲመች በሚል በወርቅ እና በዶላር ቀይረው እንዲያቀብሏቸውእና ታጋቹን ለመልቀቅ ይስማማሉ፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አክሎም፤ ይህን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ኦፊሰሮች አጋቾችና የታጋች ቤተሰብ ገንዘቡን በምሽት ሲቀባበሉ በቅርበት ሆነው ካረጋጋጡና ታጋቹ ከአዋሽ መልካሳ አዳማ ከተማ ድረስ እንዲመጡ ተደርገው መለቀቃቸውን እና ከቤተሰብ ጋር መቀላቀላቸውን ካረጋገጡ በኋላ ከኦሮሚያ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በዚህ የአጋች ታጋች የወንጀል መረብ ውስጥ ያሉትን በሙሉ በቁጥጥር ስር ውል እንዲውሉ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር እንዲውሉና በህግ እንዲጠየቁ ያደረጋቸው በአጋችና ታጋች ወንጀል ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ይበልጣል ካኻሊ ግሩም፣ጎሳዬ ወንድሙ አባተ፣ ስንታየሁ ሞገስ ገብረየሰ፣ አብርሃም ታደሰ ማሞ ፣ደነቀው ቢታው ተገኝ፣ ሙሉቀን ከበደ ታዬ እና የሺዋስ ደበበ ደግፈው የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን መረጃው ጠቁሟል፡፡
አጋቾቹ እራሳቸውን ለመደበቅ እና ከሕግ ተጠያቂት ለማምለጥ ከሶስት በላይ ሓሰተኛ ስሞችና መታወቂያዎችን ለመጠቀም ቢሞክሩም፤ ከፀጥታና ደኅንነት አካላታ መሰዋር እንዳላስቻለቸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በመረጃው አመልክቷል፡፡
የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ መግለጫ አክሎም፤ በዚህ አጋች ታጋች ወንጀል ውስጥ ተሳትፈው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች ጋር ለዚሁ እኩይ ዓላማቸው የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ፣ተተኳሾች እና የተለያዩ ሰነዶች መያዛቸውን አስታውቋል፡፡ የወንጀሉ ተሳታፊዎች ቀደም ሲል በተመሳሳይ የአጋች ታጋች ወንጀሎች ንፁሃንን በማስገደድ በግፍ የሰበሰቡት በርካታ የኢትዮጵያ ብር እና የአሜሪካ ዶላሮች ጭምር መያዛቸውንም አመልክቷል፡፡

በአጋቾቹ ተይዘው የነበሩት በቡና ላኪነት የሚተዳደሩት እና 100 ሚሊዮን ብር ቤተሰቦቻቸው የተጠየቁት አቶ እንግዳው ውዱ በሰላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሲቀላቀሉ፤ አጋቾቹ የተቀበሉት የ20 ሚሊዮን ብር ግምት ወርቅና 30 ሺ ዶላርም በቁጥጥር ስር ውሎ ለቤተሰቡ እንዲመለስ መደረጉን አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በመረጃው ጠቁሟል፡፡

በቁጥጥር ሥር የዋሉት አጋቾች ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ እገታ በመፈፀም ገንዘብ መቀበል እንዲሁም በቤተሰብ በኩል ተጠይቀው እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉ የህብረሰተብ ክፍሎች ለፀጥታና ደኅንነት አካላት ጥቆማ በማስጠት ወንጀለኞችና ግፈኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆን ለማድረግ የፀጥታና ደኅንነት አካላት እያደረጉ ያሉትን የተቀናጀ ኦፕሬሽን መረጃ በመስጠት እንዲደግፉና አንዲተባበሩ ጥሪ ያቀረበው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፤ በኦፕሬሽኑ ለተሳተፉ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ እርምጃው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አረጋግጧል፡፡

“የልብ በሽተኛ ነኝ መሞቴ አይቀርም እዚህ አሜሪካ ከምሞት በትግል ስም ኢትዮጵያ ሄጄ ትንሽ ብረብሽ ይሻላል”
21/05/2024

“የልብ በሽተኛ ነኝ መሞቴ አይቀርም እዚህ አሜሪካ ከምሞት በትግል ስም ኢትዮጵያ ሄጄ ትንሽ ብረብሽ ይሻላል”

የከንቲባዋ ምስል በጨረታ 2 ሚሊዮን ብር ተሸጠ
11/05/2024

የከንቲባዋ ምስል በጨረታ 2 ሚሊዮን ብር ተሸጠ

እስክንድር ነጋ የጠየቀው የምህረት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል===========================እስክንድር ነጋ በሸዋ እና ጎጃም አንድ አንድ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ "የአማራ ህዝባዊ ...
14/04/2024

እስክንድር ነጋ የጠየቀው የምህረት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል
===========================
እስክንድር ነጋ በሸዋ እና ጎጃም አንድ አንድ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ "የአማራ ህዝባዊ ግንባር" በሚል ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በርግጥ የእስክንድር እንቅስቃሴ ከመንግስት እይታ የተደበቀ ባይሆንም ወደ ጫካ ከገባ በኋላ የማፈንገጥ ባህሪዎችን ሲያሳይ ቆይቷል። ይሁንና በአሁን ወቅት እስክንድር በላከው ሽምግልና እና የምህረት ጥያቄ መሰረት በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ይቅርታ ሊደረግለትና ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት መሆኑ ተሰምቷል።

ቅርፅ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ነገር ግን ማንም ያቦካው ጭቃ ሁለ ቅርፅ አይደለም ።ጠሚ.ዐቢይ አሕመድ በኮሪደር ልማት ላይ ባደረጉት ንግግር ።
28/03/2024

ቅርፅ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ነገር ግን ማንም ያቦካው ጭቃ ሁለ ቅርፅ አይደለም ።
ጠሚ.ዐቢይ አሕመድ በኮሪደር ልማት ላይ ባደረጉት ንግግር ።

ዝግጁነት
09/03/2024

ዝግጁነት

አዲስአበቤ የዐቢይንና የአዳነችን ዉለታ መቼ ከፍለህ አትጨርስም !
06/03/2024

አዲስአበቤ የዐቢይንና የአዳነችን ዉለታ መቼ ከፍለህ አትጨርስም !

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when liyumedia.net posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to liyumedia.net:

Videos

Share