12/11/2025
“ግብፅ እጇን አጣጥፋ አትቀመጥም” አብዱል ፈታህ አል ሲሲ
የኢትዮጵያ ችግርም ሆነ በረከት በአብዛኛው ከአባይ ይፈልቃል።ኢትዮጵያ አባይን ብታለማም ባታለማም ከግብፅ ትንኮሳ አታመልጥም። ግብፅ በግልፅ በህገ መንግስቷ የአባይ ጉዳይ የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑንም አስቀምጣለች።የውሀአ ጉዳይ በህገመንግስት ያካተተች ብቸኛዋ ሀገር ሳትሆን አትቀርም።
ፕሬዝደንት አል ሲሲ በካይሮ የውሃ ኮንፍረንስ ላይ በግልፅ እንደተናገሩት ግብፅ ሁሉም በአባይ ላይ ያላትን የበላይነት ለማስጠበቅ ትሰራለች።በቀጥታም በእጅ አዙርም።
ዋናው ጉዳይ የግብፅ እጇን አጣጥፋ አለመቀመጥ አይደለም።ግብፅ እጇን አጣጥፋ የተቀመጠችበት ሰከንድ እንኳን የለም።በጦርነት ሞክራ ሶስት ጊዜ ተሸንፋለች።ያልሞከረችው ጉዳይ ያልቆፈረችው ጉድጓድ የለም።ግብፅ የተሳካላት የሀገር ውስጥ ግጭትን በመደገፉና ኢትዮጵያ ለብዙ አመታት እርስ በእርስ የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንድትከርም በማድረጉ ብቻና ብቻ ነው።
እኛ ደግሞ አባይን በመገደባችን ተሳክቶልናል።ለብዙ አመታት አንገታችን ላይ ቆም አላስተነፍስ ያለችንን ሀገር አሁን ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንድተገባ አድርገናታል። ያልተሳካልን ግብፅ ተጠምቆ ኢትዮጵያ የሚጠጣውን ግጭት ማስቆም ነው።
ለአባይ ገባር እንኳን የሆነውን የመገጭ ወንዝ ማልማት ፈተና ሆኖብን ቆይቷል። ይህ ሊቆጨን ይገባል። ኢትዮጵያን ከገናና ስሟ ጋር ለማስታረቅ አባይ ሽማግሌያችን ነው።
ግብፅ እጇን አጣጥፋ እንደማትቀመጠው እኛም እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም የሚልና ከአዙሪቱ መውጫው አባይ መሆኑን የሚገንዘብ ሆነን መቆም አለብን።
አባይ የኢኮኖሚ ችግራችን ይፈታል።የኢኮኖሚ ችግራችን ሲፈታ እንደ ዳንቴል የሚተረተረው ግጭት ይቆማል።
#አባይ #ኢትዮጵያ