Efa Entertainment

Efa Entertainment Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Efa Entertainment, Broadcasting & media production company, Hirnoye, Addis Ababa.

Efa Entertainment is a full service International Entertainment, Promotion, Printing and Publication works company, established in 1997 EC, by Addis Ababa University Theatre Arts and Film making graduate called Efabas Abdulwhab.

05/05/2025
04/05/2025

ዓሊ ሸቦ እና ፍለጋው
----
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
----
ባልሳሳት ዘመኑ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1978 ይመስለኛል፡፡ በዚሁ ዓመት ዓሊ ሸቦ ፍቅረኛው ጠፋችበት፡፡ እናም በአንድ አስደናቂ ዜማ እየተመራ በእግር በፈረስ ይፈልጋት ጀመር፡፡ በቆላውና በደጋው ሁሉ ሲንከራተትላት ከረመ፡፡ በመጨረሻም አጥቷት ልቡ እንደተሰበረ ወደቤቱ ሊገባ ሲል በአንዲት ከተማ ውስጥ አገኛትና በደስታ ፈነጠዘ፡፡ ከዚያም የልቡን አደረሰ፡፡ ለመሆኑ ዓሊ ሸቦ ጉዞውን እንዴት ነበር ፈጸመው? ፍቅረኛውን የት ነው ያገኛት? እስቲ አብረን እንየው፡፡
*****
ዓሊ ሸቦ እንዲህ እያለ ነበር ፍለጋውን የጀመረው (በቅንፍ ውስጥ ያለው ተቀራራቢ የአማርኛ ትርጉም ነው)፡፡

Diimtuu too bareedduu tanin yaadu halkuu (የኔ ቀይ ዳማ ጉብል ሁሌ እምናፍቃት)
Obsu waa hindandayuu bikka isin jirtuu (እንዲህ ጠፍታብኝስ እኔስ አልታገሳት)
Hamman deemee arguu (ካለችበት ፈልጌ እስከማገኛት)
ትንሽ ወረድ ብሎም እንዲህ በማለት ጨመረበት፡፡
Teeyso isidhaa hinbeyne bikka itti argamtu (አድራሻዋን አላውቅም የተደበቀችበትን)
Mee nin iyyaafadha oliifi gadittuu (እኔስ ላስሳት ነው ሄጄ ታቹን ላዩን)
Barbaadu waa hindhabu Hararguma haataatu (ከሀረርጌ ምድር አገኛት እንደሆን)

ታዲያ ዓሊ ፍለጋውን ከየት የጀመረ ይመስላችኋል? ከሀረር ነው፡፡ በጥንታዊቷ የአባድር ከተማ ላይ ከትሞ ነው እንዲህ በማለት ለፍለጋ መቁረጡን ያሰማው፡፡

Khara shanan Harar, laale seenee bahe (በአምስቱም የሀረር በሮች ገብቼ ወጥቼ)
Qalbiin na rifatus meeqa isii sehee (ልቤ እየደነገጠ ስንቷን ቆንጆ አይቼ)
Wa hin arganne dhiiroo himilaalin tahe (ለፍቶ መና ሆንኩኝ አድራሻዋን አጥቼ)

ሀረር የቆንጆዎች መናኸሪያ በመሆኗ ወደየትም ከመሄዱ በፊት ፍለጋውን ከእርሷ መጀመሩ ተገቢ ነበር፡፡ ከዚያስ ወዴት ቀጠለ? ድምጻዊው እንዲህ ይለናል፡፡
Dirree Dhawaas bu’ee mana gaggaafadhe (ድሬ ዳዋ ወርጄ ጠያይቄ ቤቷን)
Tanin shakke cufa suuta akheekadhe (በጥንቃቄ እያየሁ እርሷ ትሆን ያልኳቸውን)
Dhiiroo barbaada isii oow’i waan nagodhe (ወበቅ ብቻ ተረፈኝ ወይ እኔን ወይ እኔን)

ዓሊ ሸቦ ቀዳሚ ጉዞውን ወደ ድሬ ዳዋ ማድረጉ ልክ ነበር፡፡ ምክንያቱን “ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ” በተሰኘው መጽሐፌ በሰፊው አብራርቼ ጽፌአለሁ፡፡ ለክለሳ ያህል ደግሞ ድሬ ልዩ የሆነችባቸውን አንዳንድ ነገሮች እንዲህ እናወሳቸዋለን፡፡

ድሬ ዳዋ ከምሥራቁ ክፍል ልዩ ልዩ መንደሮች የተሰባሰቡ ሰዎች መኖሪያ ናት፡፡ የዚያ ዘመን ወጣት በድሬ የተጧጧፈው የኮንትሮባንድ ንግድ ስለሚያስጎመጀው እንደምንም ብሎ በከተማዋ ላይ ከትሞ እየሸቀለ ኑሮውን መሙላት ይፈልጋል፡፡ በአነስተኛ ከተሞች የከበረው ነጋዴም የመጨረሻ ዓላማው ድሬዳዋ ገብቶ ስሙን እነ ሐሰን ፎርሳ፣ ባሻንፈር፣ ሐምዳኢል፣ ሙሐመድ አብዱላሂ ኦግሰዴን ከመሳሰሉ የዘመኑ ዲታዎች ተርታ ማሰለፍ ነው፡፡ በድሬ ዳዋ ዘመድ ያላቸው ኮረዳዎችም “ቫኬሽን”ን እያሳበቡ ከቤተሰቦቻቸው ያፈተልኩና ክረምቱን በዚያች ውብ ከተማ ለማሳለፍ ወደዚያው ያቀናሉ፡፡ ታዳጊዎችም የሐሺሚን ሓላዋና ባቅላዋ በዝናው ስለሚያውቁት እዚያ ሄደው ካልበሉት የሚረኩ አይመስላቸውም፡፡ ስለዚህ ቤተሰቦቻቸው ወደ ድሬዳዋ የሚሄዱ ከሆነ ከናንተ ጋር ካልሄድን ብለው ያስቸግራሉ፡፡

በአንጻሩ ደግሞ ከሀረርጌ ወደ ሌሎች ቦታዎች መጥፋት የሚፈልግ ሰው ለመነሻው ድሬዳዋን ነው የሚመርጣት፡፡ ምክንያቱም በባቡር ወደ ጅቡቲ፣ በአውሮፕላን ወደ አዲስ አበባና ወደ ሌላም ቦታ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ የሀገር አቋራጭ አውቶቡስም ቢሆን በብዛት ከድሬዳዋ ነበር የሚነሳው፡፡ ለዚህ ለዚህ ድሬ በጣም ምቹ ነበረች፡፡

በዚህ ስሌት መሰረት ነው እንግዲህ ዓሊ ሸቦ ፍቅረኛውን ለማሰስ ወደ ድሬ ዳዋ የወረደው፡፡ ከዚያም ሄዶ ፈለጋት! አስፈለጋት፡፡ የጠረጠራቸውን ቦታዎች ሁሉ ፈተሸ፡፡ ነገር ግን ትርፉ የድሬ ዳዋ ሀሩርና ወበቅ ሆነና አረፈው፡፡ ከዚያስ ወዴት አመራ? እንዲህ ይለናል ዓሊ ሸቦ፡፡

Jijjiga hindabartu kharaa Gursum khana (ከጅጅጋስ አታልፍ ከዚያም ከጉርሱም)
Xuuxxisaa dhagayeetin itti-fufe amna (እያልኩ በጥርጣሬ ተይዤ ብሄድም)
Way garaa jalalaa laalaa laala gowwomina (እዩት የኔን ፍቅር ሞኝነቴን ሲያስቀድም)

አዎን! ልጅቷ ከድሬ ከጠፋች በቀጥታ ወደ ጅጅጋ ልታመራ ትችላለች ብሎ ማሰብ ደግ ነው፡፡ ጅጅጋ የድሬን ያህል ባትሆንም በንግድና በስራ ሰበብ ብዙ ሰው ይጎርፍባታል፡፡ ደግሞም ለሶማሊያ ድንበር ቅርብ ስለሆነች በሀገር ውስጥ መኖር ያስመረረው ሰው ወደርሷ ይሄድና ለውጪ ጉዞው መንደርደሪያ ያደርጋታል፡፡

ዓሊ ሸቦም ፍቅረኛው ከሀገሬ ሳትጠፋብኝ ቶሎ ልድረስባት ብሎ ወደዚያ በማቅናቱ ጥሩ መላ ዘይዷል፡፡ ነገር ግን ትርፉ ድካም ብቻ ሆነበትና ሆደ ባሻነቱን አባባሰበት፡፡ “ለመጽናኛዬ ወደ ጉርሱም ጎራ ብዬ ልፈልጋለት” ቢልም አልተሳካለትም፡፡ ታዲያ እንዲያ ለፍቶ ቢያጣት ጊዜ ምነው አይከፋ? ማልቀስ እንኳ ሲያንሰው ነው! ግን ምን በጀው? ወዴትስ ይሂድ? እንዲህ በማለት ይናገረዋል፡፡

Kharaa baddaa khanaa hindhabamtu laata (ከወደ ደጋው በኩል ምናልባት አትጠፋም)
Je’e numan dhaqe ani Gaara Mul’ataa (እያልኩኝ በጉጉት ጋራሙለታ ብወጣም)
Arguu waa hindandeenye waan isii fakkaataa (እርሷን የምትመስል ጭራሽ አልታየችም)

አሁን ዓሊ ሸቦ በአዕምሮው ተደናበረ፡፡ “ምን ይውጠኛል?” ማለትንም አመጣ፡፡ ስለዚህ ጀርባውን አዙሮ ሸመጠጠ፡፡ መቼም “ፍቅረኛዬ ከሀረርጌ ውስጥ አትውጣ እንጂ ፈልጌ አላጣትም” ብሎ የለ? ስለዚህ ጀርባውን ሰጥቶ ያለፋቸውን ቦታዎች ማሰስ ነበረበት፡፡ በዚህም መሰረት ነው እንግዲህ ወደ ደጋማው የጋራሙለታ አውራጃ የወጣው፡፡ ነገር ግን በለስ ሊቀናው አልቻለም፡፡ እርሷን የምትመስል ሴት በጭራሽ አልታየችውም፡፡ በመሆኑም ለፍቶ መና ሆኖ ተመለሰ (እርሱ ባይገልጸውም የግራዋ ብርድ በሀይለኛ ሁኔታ እንደጠለዘው ይታየኛል)፡፡
*****
ዓሊ ትንፋሽ ወስዶ እንደመቆዘም አለ፡፡ ፍቅረኛው የት ገባችበት? ሰማይ ላይ ወጣች? ወይንስ ወደ ምድር ሰረገች? ብቻ አሁንም መንገዱን አላቆመም፡፡ እናም እንዲህ አለ፡፡

Oborraa fi Ciroo hunda kehysa dhaqe (ኦቦራና ጭሮን በአካል አሰስኩት)
Miilaa fi makinaan barbaadeetin dhabe (በእግር በመኪና በፍለጋ አዳረስኩት)
Arguu koo waa hin oolu je’etin of sobe (“ጭራሽ አላጣትም” ለሆዴ እያልኩት)

ከጋራ ሙለታ አውራጃ ያጣትን ፍቅረኛውን ለማግኘት ፍጥነት ጨመረ፡፡ ወደ ምዕራብ ገስግሶ “ኦቦራ” (ወበራ) እና ጭሮን (ጨርጨርን) በፍለጋ አዳረሰ፡፡ ነገር ግን ሊያገኛት አልቻለም፡፡ እንዲያውም እርሷን ሳያገኛት የሀረርጌ ምድር ሊያልቅበት ሆነ፡፡ ቢሆንም ተስፋ አልቆረጠም፡፡ ከዚያስ ምን ተከተለ? እንዲህ በማለት ያስረዳል፡፡

Sa eedaan qalbiin tuni wahayyuma beyti (ለካስ ይህቺ ቀልቤ የፊቱን ትገምታለች)
Baddeeysa ol kunnaan khate gammachutti (በዴሳን ሳልፈው በደስታ ተብከነከነች)
Jaalalleen tiyya tun intala Habrootii (ፍቅረኛዬ ለካንስ የሀብሮ ልጅ ነች)

አዎን! ዋናው ተስፋ አለመቁረጥ ነው፡፡ ችግር መከራውን ከታገሱት ያሰቡትን ያሳካሉ፡፡ ተስፋን ይዞ ሲባዝን የከረመው ዓሊ ሸቦም ድካሙን ሁሉ ቻለው፡፡ እናም ከውስጡ የተስፋ እንጥፍጣፊ ሳያልቅ የደስታ መዓዛ አወደው፡፡ ከጭሮ ታጥፎ በዴሳን እልፍ እንዳለ ፍቅረኛው ከሩቅ ሸተተችው፡፡ ለካስ ውቃቢው ነው ዝም ብሎ ፈልግ ያሰኘው እንጂ ልጅቱ ቀድሞውንም ቢሆን አልጠፋችበትም? እንደተፈጠረች እትብቷ ከተቀበረባት ቦታ ሆና ትጠብቀው ነበር፡፡ “የት?” ብትሉ “ሀብሮ” ነው መልሱ!

የዓሊ ሸቦ ፍቅረኛ የሀብሮ ልጅ ሆና ተገኘች፡፡ ታዲያ “ሀብሮ” ሰፊ አውራጃ ነው እንጂ አንድ ከተማ ወይንም መንደር አይደለም፡፡ ከቁኒ እስከ ባሌ ጠረፍ ድረስ ያለው ተራራማ ምድር ሁሉ የሚካተትበት ክልል ነው፡፡ ስለዚህ የልጅቱ ትክክለኛ አድራሻ መታወቅ አለበት፡፡ ዓሊ ሸቦ የመጨረሻውን ውጤት እንዲህ በማለት ያበስረናል፡፡

Jaalallen gar meeqaan barbaadaan of rakkee (ስንት ሀገር በፍለጋ ያዳረስኩላት ፍቅረኛዬን)
Tanin deemee dhabe baakkan itti shakkee (ከሁሉም ቦታዎች ያጣኋት ጉብልዬን)
Walakkaa magaalaa Galamsottiin arke (ገለምሶ መሀል ላይ አገኘኋት ወዳጄን)

እንዲህ ነው ዓሊ ሸቦ! ብራቮ ዓሊ ሸቦ! እርሱ ከቆላ ደጋ የተንከራተተላት ጉብል የገለምሶ ልጅ ሆና ተገኘች! የወንዜ ልጅ! ግዳዩም በድል ተጠናቀቀ! ዓሊ ሸቦ በሐሴት ባህር ዋኘ፡፡ ነፍሲያውም በደስታ ረካች! በመጨረሻም ዓሊ እንዲህ አለና አጠቃለለ፡፡

Arkadhe qal’o too diimtuu tiyya dheertuu (አገኘሁ የኔን አለንጋ ያላት የደስ ደስ)
Isii barnootarra kharaa gala deemtu (ከትምህርት ቤት ወደ ቤቷ ስትመለስ)
Gammadeen bahaa mee ree dheebuu tootuu (ዛሬ ጥማቴን ልወጣው የልቤ እንዲደርስ)
-----
ዘፈኑን በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ፡፡ በቪዲዮው ላይ ካሉት አምስት ዘፈኖች የመጀመሪያው እርሱ ነው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=How9bBrPeo4
*****
አንድ የሚነደኝ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? በሸዋ ከተሞች (አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ ወዘተ..) “የገለምሶ ልጅ ነኝ” ከተባለ በሳቅ የሚያውካኩ ሰዎች አሉ፡፡ ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል? አንዳንድ “ውሪ ውሪ” ነጋዴዎች የከተማዬን ስም ከዚያ “ቅጠል” ጋር በማያያዛቸው ነው፡፡ በመሆኑም ገለምሶ ሲባል ብዙዎቹ የሚታያቸው ያ ጫት የሚባለው ቅጠል ብቻ ነው፡፡ ደግሞ እኮ የሚያሳዝነው ቅጠሉ ከዚያ አይደለም የሚጫነው፡፡ አብዛኛው “ከራ ዱለቻ”፤ “ዴፎ”፣ “ቢዮ”፤ “ሚሊሎ” እና “ዳሎ” ከሚባሉ ትንንሽ የገጠር ከተሞች ነው የሚጫነው፡፡ ነጋዴዎቹ ጫቱ “ዳሎ” ወይንም “ሚሊሎ” ቢባል የማይታወቅ ሰለመሰላቸው ነው በከተማዬ ስም የጠሩት፡፡ እነዚህ ከይሲዎች! ጂንኒ ጀቡቲ ሁላ!

እርግጥ ጫት በገለምሶም አለ፡፡ ግን ብዙዎች እንደሚያስቡት ገለምሶ በጫት የናወዘች ከተማ አይደለችም፡፡ የዛሬን አያድርገውና ዓሊ ሸቦን እንዲህ በፍለጋ ያንከራተተች “ቀሽቲ” ከተማ ነበረች፡፡ በሀረርጌ ምድር ከሀረርና ከጉርሱም (ፉኛን ቢራ) በስተቀር በእድሜ የሚቀድማት ከተማ የለም፡፡ የወያኔ “በዘበዛ” መጥቶ አደከሟት እንጂ፡፡

ግድ የለም! አንድ ቀን ትነሳለች፡፡ አንድ ቀን ገለምሶም፣ ሀረርም፤ ድሬዳዋም፣ አዳማም፣ ሸገርም፣ ኦሮሚያም፣ አማራም፣ ትግራይም፣ ኢትዮጵያም ሁሉም ይነሳሉ፡፡ ዋናው ተስፋ አለመቁረጥ ነው ጓዶች፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጡ፡፡
-----
አፈንዲ ሙተቂ
ነሐሴ 2005
በሀረር ከተማ ተጻፈ፡፡
-----
ትክክለኛዎቹ የሶሻል ሚዲያ አድራሻዎቼ የሚከተሉት ናቸው።

= የፌስቡክ ፔጅ (My New page)

https://www.facebook.com/AfendiEthno2018

=> የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel)

https://t.me/afandishaHarar
-----
Thank you..

02/05/2025
25/04/2025

Zariihuun Wadaajoo Yomiyyu sii yaadanna.

Send a message to learn more

25/04/2025

Zariihuun Wadaajoo
Rabbiin Jannataan sii haaqananiisu

21/04/2025
18/04/2025

የዛሬ ሰባት አመት ወደኃላ-ድምፃዊ ታምራት ደስታ (ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)

"በፍቅር መዝገብ ላይ ቀድሞ ቢፅፈንም
አንድ ሁኑ ብሎናል ማንም አይለየንም
ታድያ ምን አስፈራን ትህዛዙን ሰው ላይሽር
ከ ላይ ከተሰጠን የማይናድ ፍቅር"…

| ጊዜ የመሮጡ ትርጉም እንዲህ አይነት ትውስታዎች ሲኖሩ ነው ትናንት በታምራት ደስታ ዘፈኖች የተዝናና እና በታምራት ደስታ የፍቅር ዘፈኖች እራሱን ያከመ ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ታሜ በሕይወት ባይኖር😢💔 ሙዚቃዎቹ ትኩስ ሆነው አዲሱ ትውልድ ተፅኖ ማሳደሩን አላቆመም፡፡

ድምፃዊ የዜማ እና ግጥም ደራሲ ድምፃዊ አርቲስት ታምራት ደስታ ማይክ በእጁ ስትገባ እጅጉ የሰው ስሜት በንፁህ ፍቅር ይረበሻለ ይህ የታሜ ገፅ ነው፡፡ የታሜ ግኝቱ ከ ሐዋሳ እስከ አዲስ አበባ ግንቦት 25/1971 ዓ.ም የፍቅር ከተማ ከሆነችሁ አዋሳ ልዩ ስሙ ጥቁር ውሀ የተሰኘ ቦታ ተወለደ ፡፡

ተወዳጁ ድምፃዊ ታምራት ደስታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በ ሀዋሳ ታቦር ት/ቤት እንዲሁም በካቶሊክ ሚሽን ት/ቤት የተከታተለው የሁለተኛ ደረጃ ደሞ ትምህርቱን በሻሸመኔ በመጓዝ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል ተከታትሏል፡፡

ገና ለጋ እያለ በሙዚቃ ፍቅር ይነደፋል ሙዚቃ ይሰማል አብሮም ያቀነቅን ነበር ይንን የሙዚቃ ፍቅር እውን ለማድረግ ወደ ድሬዳዋ በማቅናት በኮተኒ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የሙዚቃ ቡድን ጋር በመቀላቀለ በዛም ሳለ ችሎታው እጅግ ያስገርም ነበር በኮተኒም ጨርቃጨርቅ "150" ብር እየተከፈለው ስራ ጀመረ ፡፡

በኃላም በሙዚቃ ጉሮሮውን ካሟሸ በኃላ በ 1990 ዎቹ መግቢያ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በተለያዩ የምሽት ክበቦች ሰፊ ጊዜውን በመሰራት ሀዋሳ የነበረውን ችሎታ እጅግ አበልፅጎት በአዱ ገነት ምሽቶች ተወዳጅነትን አተረፈ።

እንዲህ እንዲያ እያለ ወደ ራስ ማወቅ እራስ ማሳየት ቦታ ሲደርስ በስሙ የሰየመውን ''ታሜ'' የተሰኘ አልበም በማራቶን ሙዚቃ ቤት ያተመውን ብዙም አድማጭ ዘንድ ጆሮ ያልገባውን አደረሰን በመቀጠል በ 1994 አ.ም ሀኪሜ ነሽ ሲል እንደ ገና ሪአሬንጅ በማድረግ አደረሰን በ1996 አ.ም አንለያይም ከ ዳግማዊ አሊ ጋር ሰሩ በ2000 ተወዳጅነትን አትርፎ '' ካንቺ አይበልጥም'' ሲል በ2006 አዲስ አልበም አበረከተ 2006 ''ከዛ ሰፈር "የተሰኙ አልበሞችን አደረሰን ፡፡

ድምፃዊዊ ታምራት ደስታ ለሰው ተራፊ ነበር ተወዳጅ ሙዚቃዎችን አሻግራል ለ ገረመው አሰፋ ፣ ለወንድሙ ጅራ ፣ ለጥበቡ ወርቅዬ፣ጌድዮን ዳንኤል፣ገረመው አሰፋ፣ጎሳዬ ተስፋዬ፣መሰሉ ፋንታሁን፣ ይርዳው ጤና ፣ታደለ ገመቹ ፣ሄለን በርሄ ግጥም እና ዜማ በመስጠት አይተኬ ሚናውን ተወቷል ፡፡

ግጥም ዜማ ስራ አብሮ ከሰራቸው መሀከል ፣ ማትያስ ተፈራ፣ ጌትሽ ማሞ ፣ አብታሙ ቦታለ ፣ ኃይለእየሱስ እሸቱ ፣እና የመሳሰሉት በቅንብሩ ኤልያስ መልካ ፣ ዳግማዊ አሊ ፣ ካሙዙ ካሳ፣ ሚካኤል ሀይሉ ባወጣቸው አልበም ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው ፡፡

ሚያዚያ 10 /2010 አም ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡

ስለ ሰጠከን ሙዚቃዎች ሁሉ እናመሰግናለን ውዱ ታምራት ደስታ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

03/04/2025
02/02/2025

Poem

I refuse to talk to you,
leave you feeling lost and blue,
your heart in pain, and still you push through—
but at least I didn’t hit you.

I lied to you, twisted facts,
changed the story behind your back,
still, I say this as if it’s true—
but at least I didn’t hit you.

I made you doubt what’s real inside,
played with your mind till you cried,
I broke your trust but blamed it on you—
but at least I didn’t hit you.

I told everyone it’s all your fault,
turned your world upside down, by default,
I blamed everything on you—
but at least I didn’t hit you.

I spread lies, ruined your name,
made sure you carried all the shame,
yet I say this to justify my view—
but at least I didn’t hit you.

I stopped showing love and care,
left you wondering if I was ever there,
in your confusion, I stand proud and new—
because at least I didn’t hit you.

I refuse to look your way,
ignore the words you try to say,
leaving you feeling torn in two—
but at least I didn’t hit you.

I broke the promises that I made,
watched your trust in me fade,
yet I stand here, still arguing with you—
but at least I didn’t hit you.

I guilt-tripped you to get my way,
made you feel like you had to stay,
kept control without you having a clue—
but at least I didn’t hit you.

I compared you to someone new,
made you feel you had to prove,
worked harder just to earn my view—
but at least I didn’t hit you.

I chipped away at your self-worth,
convinced you nothing you did had worth,
and watched as you tried to pull through—
but at least I didn’t hit you.

I used your secrets to make you small,
tore you down until you’d fall,
and laughed while you lost your view—
but at least I didn’t hit you.

I pushed your friends and family away,
left you alone, made you obey,
your world became what I construe—
but at least I didn’t hit you.

I played the hero in the crowd,
while you stayed quiet, never loud,
and watched as no one ever knew—
but at least I didn’t hit you.

I made you feel like you're to blame,
kept you stuck inside my game,
and still, I claim I’m good to you—
because at least I didn’t hit you.

E.S.

Address

Hirnoye
Addis Ababa
2957

Telephone

+251911476364

Website

http://www.efaentertainment.com/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Efa Entertainment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Efa Entertainment:

Share