09/05/2025
ሰበር ዜና - ሼር ⚠️
በየመን ሻብዋ ግዛት በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ታግተው የነበሩ 25 ኢትዮጵያዊያን ተለቀቁ ፡፡ የሻብዋ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ዓጠቕ ምስራቃዊ ክፍል ላይ የአገራቸው ልጆች በሆኑ በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከታገቱ ቡኋላ ወንጀለኞቹ እጅግ ዘግናኝ የሆነ የማሰቃያ ዘዴዎችን ተጠቅመው ተጎጂዎቹ ከእስር እንዲፈቱ ገንዘብ ለማዘዋወር ከባለቤቶቻቸው ጋር ለመነጋገር ይገደዳሉ።
ከእያንዳንዱ ታሳሪ እስከ አስር ሺህ የሳውዲ ሪያል የገንዘብ ዝውውሮች እየተቀበሉ፣ እንዲሁም በተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ላይ ጫና ለመጨመር ሲሉ የማሰቃያ ቭድዮዎችን እየቀረፁ ሲልኩ እንደነበር ተናግረዋል።
ይህ መረጃ የደረሰው የሻብዋ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታጋቾቹ ያሉበትን ቦታ ከደረሰ ቡኋላ በወሰደው እርምጃ 4 ሴቶችን ጨምሮ በጠቅላላ 25 ኢትዮጵያዊያን ማስለቀቅ መቻሉንም አስታውቋል፡፡
በአጋቾቹ ቤት ውስጥ ከታገቱት ከእነዚህ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ 15 ሚሊዮን 54,00 የየመን ሪያል 55 ሺህ 920 የሳኡዲ ሪያል እና 130 የአሜርካን ዶላር ተገኝቷል፡
ሌተናል ካሚስ ጠላፊዎቹ እና ዘራፊዎቹ ላይ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወሰድ እና ወደ አቃቤ ህግ እንደሚመሩ አረጋግጠዋል ።
ምንጭ»Brex Habeshawi