17/08/2024
እስኪረፋፍድም አይጠብቅም ፡ በቃ በጠዋት ከመኝታው እንደተነሳ ፡ ቁርሱን እንኳን በደንብ ሳይበላ ይወጣና አዘውትሮ አልኮል ወደሚጠጣበት ባር በመሄድ
ቀኑን ሙሉ ሲጠጣ ውሎ ፡ መጠጥ በቅቶት ሳይሆን ፡ ብርጭቆ የማንሳት አቅም ሲያጣ ፡ እንደምንም እየተንገዳገደ ወደቤቱ ይመለሳል ።
ይህ ከላይ ያለው ኑሮ ፡ የዝነኛው የእግር ኳስ ኮከብ ፡ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ታላቅ ወንድም የሆነው የ hugo dos santos aveiro ለአመታት የኖረበት ህይወት ነው ።
የሮናልዶ እናት እና ራሱ ሮናልዶ ጭምር ሁጎን ከዚህ ከመጠጥ ሱሱ ለማዳን ለአመታት ሞክረዋል ።
በተለይ ሮናልዶ ፡ የመጠጥ ሱስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፡ በአባቱ ያውቀው ነበርና ፡ ወንድሙን በዚህ ምክንያት እንዳያጣ ይሰጋል ።
እና አንድ ቀን ወንድሙን እንደሚፈልገው ነግሮት አንድ ሬስቶራንት ይዞት ሄደ ፡ ምሳ እየበሉ ሊመክረው ፡ ከዚህ የመጠጥ ሱስ እንዲያቆም እንደሁልጊዜው ሊማፀነው ነው ያሰበው ።
እና አስተናጋጇ መጣች ፡ ምን ይምጣላችሁ ስትል ጠየቀች ፡ ቀልደኛው የሮናልዶ ወንድም ለኔ የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሲል ቀለደ ። በዚህ ከተሳሳቁ በኋላ የሚበላ አዘው ማውራት ጀመሩ ፡ እና ሮናልዶ ፡ ቀንደኛ የማድሪድ ደጋፊ ለሆነው ወንድሙ ይሄን ያህል ዋንጫ ርቦሀል እንዴ ሲል ጠየቀው ።
" አዎ በጣም ፡ በተለይ የሻምፒየንስ ሊግ " ሲል መለሰለት
በቃ አይዞን በዚህ አመትማ እንበላዋለን ፡ ግን ቃል ግባ
" ምን ብዬ " አለ ሁጎ
በዚህ አመት ማድሪድ የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ካነሳ መጠጥ ታቆማለህ ?
" አዎ "
ፕሮሚስ ?
" ፕሮሚስ !!! " ባንዳፍ ! እንግዲህ ቃል ገብተሀል እንዳትረሳ ። ተባብለው ተለያዩ ።
ከወራት በኋላ ሮናልዶ ያሰበው ተሳካ , እናም ትልቅ ሪከርድ ሊባል በሚችል በአንድ የሻምፒየንስ ሊግ 2013-2014 ሲዝን በድምሩ 17 ግቦችን በማስቆጠር ማድሪድና ፡ ወንድሙ የፈለጉትን ድል ማሳካት ቻለ ።
እና ልክ የዋንጫው ጫዋታ እለት ማድሪድ አሸንፎ ዋንጫውን ሲያነሱ ፡ የማድሪድ ደጋፊ ወንድሙ ሲሮጥ ወደ ሜዳ መጣ ፡ ከሮናልዶ ጋር ተቃቀፉ ፨
እና ሮናልዶ ያሸነፈበትን ማልያ ለወንድሙ ከሰጠው በኋላ በጆሮው ፡ እኔ ቃሌን ጠብቂያለሁ ፡ አሁን ደግሞ ተራው ያንተ ነው አለው ።
ለአመታት በመጠጥ ሱስ ተይዞ ቤተሰቡን ሲያሰቃይ የነበረው ሁጎም የማድሪድን ዋንጫ ማግኘት ተከትሎ ቃሉን ጠበቀ ፨
መጠጥ እርግፍ አድርጎ ተወ ።
ዛሬ ላይ ሁጎ ትልቅና የተከበረ ሰው ነው ። በፖርቹጋል የሚገኘውን የሮናልዶን ሙዚየምና ሌሎች ቢዝነሶቹንም የሚቆጣጠርለት እሱ ነው ።
በወንድሙ የአመታት ምክርና ጥረት ሁጎ አሁን የቤተሰቡ መኩሪያ ሆኗል ።
Wasihun Tesfaye