Prime Media - አማርኛ

Prime Media - አማርኛ Prime Media is an East African regional media organization that aims to educate, entertain, &inspire
Voice of Reason

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ  ጳጉሜን 4 ''የህብር ቀን''ን ምክንያት በማድረግ በባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ  ለሚገኙ 230 ተማሪዎችና አቅመ ደካሞች የትምህርት ቁሳቁስና ዱቄ...
09/09/2026

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ጳጉሜን 4 ''የህብር ቀን''ን ምክንያት በማድረግ በባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ለሚገኙ 230 ተማሪዎችና አቅመ ደካሞች የትምህርት ቁሳቁስና ዱቄት ድጋፍ አድርጓል።
ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 4,2018

ድጋፉ ተማሪዎች በትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና ለአቅመ ደካማ ወገኖች ተስፋ ለመስጠትና ለመደገፍ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።

በስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የሥርዓተ-ፆታ ዳይሬክተር ወይዘሮ ዱሬ ይማም እንደተናገሩት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከፍተኛ ሰብዓዊ ነጸብራቅ ከመሆኑም በላይ የልማት ሥራ ምሰሶና የማህበራዊ ችግሮች ቁልፍ ነው።

ኤጀንሲው ከተሰጠው ተልእኮ የግብርና ምርትና ምርታማነትንበማሳደግ፣የግብርና ግብአት አቅርቦትን ለማዘመንና ጎን ለጎን በሰብአዊ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ጳጉሜን 4 ''የህብር ቀን''ን ምክንያት በማድረግ በባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ለሚገኙ 230 ተማሪዎችና አቅመ ደካሞች የትምህርት ቁሳቁስና የምግብ እህል ድጋፍ አድርጓል።

ለአቅመ ደካሞች የተደረገው ድጋፍ 400 ዳርዛና ደብተር፣50 ፓኬት እስክሪብቶ ጨምሮ እንዲሁም በነፍስ ወከፍ 25 ኪሎ ግራም ዱቄት ለ230 ሰው የተበረከተላቸው ሲሆን በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ልገሳ መደረጉንም ገለጸዋል ።

የባሌ ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አወል ኢብራሂም በበኩላቸው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰብዓዊነትን፣ ሀገር ወዳድነትንና ቁሳዊ ጥቅም-አልባ አገልግሎትን የሚያስተምር ትልቅ የትውልድ መቅረጫ መድረክ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ለኅብረተሰቡ አፋጣኝ ማኅበራዊ መፍትሔዎችን ከመስጠት ባሻገር፣ የመንግሥትን የፋይናንስ ጫና በመቀነስ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ይህንን በጎ እሴት በተደራጀ መንገድ ማስቀጠልና የሥራዎቹን የጥራት ደረጃ የበለጠ ማሳደግ፣ የሀገራችንን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጉዞ በእጅጉ ያፋጥነዋል በማለት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በዞኑ ወረዳዎች ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።

የዲንሾ ወረዳ አስተዳደር አቶ መሀመድ እዲሪስ በበኩላቸው የማኅበራዊ ድጋፍ ማድረግ አብሮነትንና ማኅበራዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድም የራሱን ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊ ፋይዳው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር የመንግሥትን በጀት በመታደግ በኩል የሚያበረክተው አስተዋጽዖ እጅግ ከፍተኛ ነው። የመንግሥትን ውስን ሀብትም በሌሎች ልማቶች ላይ እንዲያውል ትልቅ ዕድል መፍጠር ችሏል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ሰዎች በበኩላቸው
የማህበረሰቡን ችግር ለማቃለል ላተደረገላቸዉ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

ዘገባው የባሌ ዞን ኮምንኬሽን ነዉ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና ዳሽን ባንክ በፋይናንስ አቅርቦት በትብብር ለመስራት ተስማሙፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 4,2018የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ዳሽን ባንክ በጆይንት ቬንቸ...
09/09/2026

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና ዳሽን ባንክ በፋይናንስ አቅርቦት በትብብር ለመስራት ተስማሙ

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 4,2018

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ዳሽን ባንክ በጆይንት ቬንቸርና ኢንቨስትመንት የቤት ልማት ሥራዎች በፋይናንስ አቅርቦት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ተፈራርመዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው ሰፊ የቤት ልማት መርሐ ግብር አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት ለመፍጠር ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ትብብሩን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በስምምነቱ መሠረት በጆይንት ቬንቸር አሰራር ስልት አዋጭ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ዳሽን ባንክ የፋይናንስ አማራጮችን ያቀርባል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቤት ልማት መርሐ ግብር የፋይናንስ አቅርቦት ከዳሽን ባንክ ለማግኘት ስምምነት ላይ መደረሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ረገድ ተቋማቱ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡

በጤናው ዘርፍ  የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት "በጎነት ለጤናችን" በሚል መርህ ቃል ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን ተጠቆመ ።ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 3,2018በባሌ ዞን በዘንድሮው ...
08/09/2026

በጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት "በጎነት ለጤናችን" በሚል መርህ ቃል ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን ተጠቆመ ።

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 3,2018

በባሌ ዞን በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጤናው ዘርፍ ውጤታማ ስራ መከናወኑ ተገለጸ።

የባሌ ዞን ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሴይፉዲን መሐመድ በበኩላቸው በዞኑ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የደም ልገሳን ጨምሮ በጤና ግንዛቤና ነፃ የምርመራና የምክር አገልግሎት ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘንድሮው በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለይም በጤናው ዘርፍ ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገለጸውል።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተከናወኑት ተግባራት የአይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ቀዶ ጥገና መስጠት የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ እና የካንሰር ቅድመ ምርመራዎችን ለችግረኛ ወገኖች በነጻ ማቅረብ፣ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች በየቤታቸው በመሄድ የህክምና ክትትል በማድረግ

በክረምት ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን የደም እጥረት በመቅረፍ ሰፊ የደም ልገሳ ፕሮግራሞችን ማስተባበር፣የክረምት ዝናብን ተከትሎ የሚፈጠሩ የቆሙ ውሃዎችን ማድረቅ እና የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ማውደም፣የወባ በሽታን ለመከላከል የፀረ-ትንኝ ኬሚካል መርጨት

የአልጋ አውታር ማሰራጨት፣አቅም ለሌላቸው ወገኖች ነጻ መድሃኒቶችን ማሰራጨት፣ለጤና ኬላዎች እና ለጤና ጣቢያዎች የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ በተሰራው ስራ ውጤታማ ተግባራት መከናወኑንም ገልፀዋል ።

በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ድረስ 70 ሺህ ተገልጋዮች ከ1 .3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ የክረምት በጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶና የጤና ባለሞያዎች ህሙማንን በመንከባከብ፣ ታካሚዎችን በተለያየ መልኩ እገዛና ድጋፍ በማድረግ የነበራቸው ሚና የጎላ ነበር ነው ያሉት።

የበጎ ፈቃድ ስራ በገንዘብ የማይገዛ ነገር ግን በርካታ ስራዎች እየተሰሩበት ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በጎ ተግባር መሆኑንም አቶ ሴይፈዲን ተናግረዋል።

የበጎ ፍቃድ ስራ ሰዎችን ያለገንዘብ ክፍያ በመርዳት የህሊና እርካታ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው የሰዎች ጥሩነትና ደግነት የሚገለጽበት በመሆኑ "በዚህ ተግባር የተሳተፋችሁ ወጣቶችና በየደረጃው የሚተገኙ የጤና ባለሞያዎች ልትኮሩ ይገባል" ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመሆኑም የበጎ ፈቃድ ስራ የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት ኖሮት ወገኖቻቸውን በሁሉም መስክ በማገዝ ወጣቶችና የጤና ባለሞያዎች እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

ዘገባው የባሌ ዞን ኮምንኬሽን ነዉ

የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግ የተጀመረው ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ አመራሮች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የባሌ ዞን አስተዳደሪ አቶ ...
07/09/2026

የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግ የተጀመረው ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ አመራሮች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የባሌ ዞን አስተዳደሪ አቶ አብዱልሃኪም አልይ ጥሪ አቀረቡ።

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 02,2018

በባሌ ዞን ፅዱና ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶችን ለአርሶና አርብቶ አደሩ ለመገንባት የተቀረጸውን ኢንሼቲቭ ለማሳካት በየደረጃው ያሉ የወረዳና የዞን አመራሮች የስራ ሂደት ብድን መሪዎች ባላቸው ሚና ላይ ውይይት አካሄዷል።

ስልጠናው ዘመናዊ የገጠር ቤቶች የአኗኗር ዘይቤ ጽንሰ ሃሳብ በመረዳት የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው።

ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የልማት ግቦችን ከግብ ለማድረስ የልማት ሥራዎችን ክህሎት፣ ቅንጅትና ውጤታማነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑንም ተገልፀዋል ።

የባሌ ዞን አስተዳደሪ አቶ አብዱልሃኪም አልይ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ በዞኑ የቤተሰብ ብልጽግናን ማረጋገጥ የምንችለው አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የተሻለ ሕይወት መኖር ሲችሉ ነው።

በገጠር ያለውን ማህበረሰብ ሕይወትና የአኗኗር ዘይቤ ሳንለውጥ ብልጽግናችን ሙሉ አይሆንም ያሉት አቶአብድልሀኪም፤ ለዚህም አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ጥሪት እንዲያፈራና የገቢ አቅሙ እንዲያድግ መንግስት ዘርፈ ብዙ ኢንሼቲቭ ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የገጠር ኢኮኖሚን ተለዋዋጭነት እና የመቋቋም አቅም ከማረጋገጥ በተጨማሪ የከተማ ፍልሰትን የበለጠ ይቀንሳልም ብለዋልበመሆኑም ገጠር ወጣቶች በስራ እድል እጦት የሚሰደዱበት አካባቢ አይሆንም ብለዋል።

አክለውም ጤናማና በቂ ዕረፍት ያገኘ አምራች ኃይል በግብርናው ዘርፍ ላይ ያለውን ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚጨምር የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግ የተጀመረው ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ አመራሮች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የዞን አስተዳደረ ጥሪ አቅረበዋል ።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የዉይይት ጽሁፍ ያቀረቡት በብልጽግና ፓርቲ የባሌ ዞን ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብራሃኑ አርፋሳ በበኩላቸው
እንደተናገሩት የሰው ልጅ ለመኖር ከሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮች መካከል አንዱ ቤት መሆኑን በመግለጽ ለዝህም በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች በገጠሩ አካባቢዎች እየተገነባ ነው። ይህም ከገጠር ወደ ከተማ የሚኖረውን ፍልሰት እንዲቀንስ ያግዛል ብለዋል።

የእያንዳንዱን ቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥ እና የገጠር ነዋሪዎችን ሕይወት ለማሻሻል በዞኑ የተለያዩ አሰራሮችንና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እየተሠራ መሆኑም ተናግረዋል።

በገጠር አካባቢ ያሉ ቤቶች ከደረጃ በታች ስለሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከፍጥነት፣ ከጥራት እና ከበጀት ጋር በተያያዘ ተመጣጣኝ በማድረግ እየተሰራ ሲሆን በየደረጃው ያሉ የሰራ ሃላፊዎች በተኩረት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ዘመናዊ ቤቶቹ የአኗኗር ዘይቤን ለማሳደግ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀው፤ ሁሉም አቅም ያለው አካል የገጠር ዘመናዊ መንደር ግንባታን በማገዝ የበኩሉን እንዲወጣ አቶ ብረሃኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘገባው የባሌ ዞን ኮምንኬሽን ነዉ

ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን በባሌ ዞን አጋርፈ ወረዳ በመስክ ጉብኝት ተከበር ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 1,2018በባሌ ዞን አጋርፋ  ወረዳ ጳጉሜ 1 “የእመርታ ቀን“ከተረጅነት ወደ ምርታ...
06/09/2026

ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን በባሌ ዞን አጋርፈ ወረዳ በመስክ ጉብኝት ተከበር

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ጳጉሜ 1,2018

በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ ጳጉሜ 1 “የእመርታ ቀን“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት”በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በአጋርፋ ወረዳ በአሊ ቀበሌ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት ኢኒሸቲቭ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኘውን የስንዴ ሰብልና ዝርያቸው የተሻሻሉ የወተት ላሞችን በመጎብኘት የተጀመረው የጳጉሜ 1 “የእመርታ ቀን” በዓል፣ የህዝባችንን የድካም ውጤት እና የብልጽግናን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ተገለፀ ።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በብልጽግና ፓርቲ የባሌ ዞን ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብራሃኑ አርፋሳ በበኩላቸው በወረዳውና፣ በዞን እና በግብርና ቤተሰቦች ተሳትፎ የሚካሄደው ይህ ጉብኝት ያለፉትን የልፋት ውጤቶች የምንመዝንበት ብቻ ሳይሆን፣ አምራችነታችንን በማስቀጠል የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ያለንን ጽኑ አቋም የሚያሳይ ትልቅ ኢኒሼቲቭ ነውም ብለዋል

አክለውም በዞኑ በግብርናው ዘርፍ የተሰራው አማርቂ ዉጤቶች የተረጅነትን አስተሳሰብ ሰብሮ በላብና በዕውቀት በመገንባት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚቻል በተግባር እየታየ ይገኛል።

ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና ለኢኮኖሚ እድገት የለፉትን አርሶ አደሮችና የሙያ ባለሙያዎች ጥረት እያመሰገንን፣ የነገዋ ኢትዮጵያ ብልጽግና አስተሳሰብ በምርታማነታችን ታንጻ እውን እንደምትሆን ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ገልፀዋል ።

የባሌ ዞን ግብርና ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ አልይ መሀመድ በበኩላቸው በዞኑ በግብርናዉ ዘርፍ የተመዘገበዉ እመርታ ሀገራችን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋጥ የምታደርገዉ ጥረት ተጨባጭ ዉጤት ማምጣቱ የማይቀር መሆኑን የሚያስረግጥ ሀቅ ነዉም ብለዋል።

የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነት ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ውጤት መገኘቱን በመግለፅ

በዞኑ መንግሥት በቁርጠኝነት በመስራት፣ግብርናን ማሻገር እንዲሁም ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በተከናወኑ ስራዎች ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል።

ከለውጡ መንግሥት ስኬቶች አንዱ የበጋ ስንዴ ልማት መሆኑን ጠቁመው፤ለዘመናት በሚሊዮኖች በሚቆጠር ወጪ ከውጭ ይገባ የነበረው ስንዴ ራስን በመቻል ሀገር ውስጥ ለማምረት ተችሏል ብለዋል።

በዞኑ በ2018/2019 የምርት ዘመን ከ 5 መቶ 80 ሺ ሄክታር በላይ በሰብል ተሸፍኖ እየለማ ሲሆን ከዚህም 19 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ጠቅመዋል ።

የአጋርፋ ወረዳ አስተዳደር አቶ አብድልቃዲር ኡስማን በበኩላቸው በወረዳው በግብርናው ዘርፍ በተሰራው ስራ በግብርናው ዘርፍ በምግብ ራስን የመቻል ግብን ለማሳካትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል ፈጣን የምርታማነት ሽግግር ላይ መደረሱን በመግለጽ።

የግብርና ዘርፍ ከነበረበት ከእጅ ወደ አፍ ልምምድ በማላቀቅ አሁን ላይ ከእርሻ ወደ ንግድ እና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ወደሚያስችል ጠንካራ መሠረት እየተሸጋገረ ነው ብለዋል።

ዘገባው የባሌ ዞን ኮምንኬሽን ነዉ

የዘመን መለወጫ በዓልን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የምርት እጥረት እንዳይፈጠርና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ለመከላከል  የዞኑን ማህበረሰብ የኑሮ ጫና ለማቃለል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች...
05/09/2026

የዘመን መለወጫ በዓልን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የምርት እጥረት እንዳይፈጠርና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ለመከላከል የዞኑን ማህበረሰብ የኑሮ ጫና ለማቃለል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የባሌ ዞን ንግድ ጽፈት ቤት አስታወቀ።

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ነሐሴ 30,2018

በባሌ ዞን ከሚመለከታቸው አካላቶች ጋር በመቀናጀት ለመጪው የአዲስ ዓመት በዓል የምርት እጥረት እንዳይፈጠርና የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት ተጣናቆ ወደ ስራ መገባቱን ተገለፀ ።
የባሌ ዞን ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሙሲና አብደላ እንደገለፁት በዞኑ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት እጥረት እንዳይፈጠርና መሰረታዊ ሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጡ በየደረጃው ለሚገኙ የንግድ መስሪያ ቤቶች መዋቅር መመሪያ በመሰጠት ወደ ስራ እንዲ ገቡ መደረጉንም ገልጸዋል ።

የህዝብ በዓላትና የዘመን መለወጫ የዋጋ ንረትን ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረትና ህገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል ሰፊ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

እነዚህ ምርቶች በቀጥታ ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርሱ ከአከባቢው ነጋዴ ማህበራት፣የህብረት ስራ ማህበራት፣ኢንዱስትሪ አምራቾች እና ከአርሶ አደሮች ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የገበያ መረጋጋትን የማስፈን ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስታውሰዋል።

ከበዓል ፍጆታዎች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ ለትምህርት የሚሆኑ ግብዓቶች እና የተለያዩ አልባሳቶች እንደሚቀርቡም ወይዘሮ ሙሲና አስረድተዋል፡፡

ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል በየወረዳው ባሉ የንግድ ጸፈት ቤቶች የገበያ መረጋጋት ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስቶች ተቋቁመው ስራ መጀመራቸውን ሃላፊዋ አክለው ገልጸዋል።

ምርቱን በሚያከማቹና በሚሸሸጉ ተጨማሪ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የተለያዩ የመጋዘን ፍተሻዎች እንደሚደረጉም ጠቁመዋል።

የበዓሉን ምክንያት በማድረግ የዋጋ ንረትን ለመከላከል የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ አርቴፊሻል የሆነ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የህገ-ወጥ ንግድ መከላከልና የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዞኑ ከ10,000 በላይ ነጋዴዎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰቷቸዉ በንግ ስራ ላይ ተሰማርተው እየሰሩ መሆናቸውን ከዞኑ ንግድ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

ዘገባው የባሌ ዞን ኮምንኬሽን ነዉ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሌ ሮቤ ዲስትሪክት ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በሮቤ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አከናወነ ።‎‎ዲስትሪክቱ የ2019 ዓ.ም ...
04/09/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሌ ሮቤ ዲስትሪክት ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በሮቤ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አከናወነ ።
‎
‎ዲስትሪክቱ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን በማስመልከት “አዲሱን ዓመት በአገልጋይነትና በበጎነት” በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካሞችና ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሂዷል።
‎
‎የዲስትሪክቱ ማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር በዓሉን ከመቀበል ባሻገር የማህበራዊ ኃላፊነትና የአብሮነት መንፈስን ለማጠናከር እንደ ሆነ ተገልጿል ።
‎
‎ለመርሐ-ግብሩ ዲስትሪክቱ ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለእያንዳንዱ 25 ኪሎ ግራም ዱቄት፣ 5 ሊትር ዘይት እና 2 ሺህ ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ለበዓሉ መዋያ ድጋፍ አድርጓል።
‎
‎የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ የአዲስ ዓመትን በዓል በመልካም ተግባር ለመቀበልና በተለይም ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲቀበሉ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

የባሌ ሮቤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሙዲን ገመዳ እንደገለጹት፤ ባንኩ ከሚሰጠው የባንክ አገልግሎት ጎን ለጎን እንዲህ ባሉ ሀገራዊ ፣ባህላዊና የሃይማኖታዊ በዓላት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመርዳት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሌ ሮቤ ዲስትሪክት ከመደበኛ አገልግሎቱ ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የሚያደርገው በጎ ተግባር አርዓያነት ያለው መሆኑን በመገለጽ አንጋፋው ተቋም ከመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎቱ ባሻገር ማህበራዊና ሀገራዊ ግዴታውን በመረዳት ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ደጋፊና ጠዋሪ ላጡ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን አቶ ሙህዲን ገልፀዋል ።

የሮቤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቱሉ በበኩላቸው፤ የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራት፣ በተለይም ለአቅም ደካሞች የሚደረጉ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራሞች የአብሮነት እና የመደጋገፍ እሴቶቻችንን በተግባር የምናሳይባቸው ታላላቅ መድረኮች ናቸው።

እነዚህ መርሃ ግብሮች የተቸገሩ ወገኖችን ከመደገፍ ባለፈ የማህበረሰቡን አንድነት ያጠናክራሉ ብለዋል።

ይህን የተቀደሰ አላማ ይበልጥ ውጤታማ እና ተደራሽ ለማድረግ በከተማዋ ትላልቅ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገለጸዋል ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረዳዳት ባህልንና ሀገራዊ፣ባህላዊና የሃይማኖታዊ እሴቶችን በማክበር ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ይህ ተግባር ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን በመሆኑ፣ ተመሳሳይ ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የማዕዱ ተጠቃሚ የሆኑ አቅመ ደካሞች በበዓል ዋዜማ ባንኩ ላደረገላቸው የጎላ ድጋፍ የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ በመግለጽ ምስጋና ማቅረባቸውን የባሌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

ደንበል ኮሌጅ በተለያዮ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ። ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ነሐሴ 24,2018በሸገር ክፍለ ከተማ ለገጣፎ እንዲሁም በሰንዳፋ በኬ ከ2009 አመተ ...
30/08/2026

ደንበል ኮሌጅ በተለያዮ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ነሐሴ 24,2018

በሸገር ክፍለ ከተማ ለገጣፎ እንዲሁም በሰንዳፋ በኬ ከ2009 አመተ ምህረት ጀምሮ ማስተማር የጀመረው ደንበል ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቁ እና ተወዳዳሪ ሙያተኞችን እያፈራ ያለ ተቋም ነው።

ኮሌጁ በዘንድሮው አመትም በሁለተኛ እና በመጀመሪያ ድግሪ እንዲሁም በቴክኒክ እና ሙያ ያሰለጠናቸውን ከ5መቶ በላይ ተማሪዎቹን አስመርቋል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን መስራች እና ባለቤት አቶ ተሾመ በቀለ ኮሌጁ በዘንድሮው አመት በ13 የትምህርት ዘርፎች ማለትም በጤና በቴክኖሎጂ በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ዘርፎች በእውቀት እና በክህሎት የበለፀጉ ብቁ ተማሪዎችን አስመርቋል ብለዋል።

ተመራቂዎች ሰፊውን አለም የሚጋፈጡበት ጥንካሬን ችግር ፈቺነትን ከኮሌጁ መቅሰም የቻሉ ናቸው። ይህም ሀገራቸውን እና ማህበረሰባቸውን በአግባቡ እንዲያገለግሉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ ከፍለው መማር ያልቻሉ ከ1600 በላይ ተማሪዎችን በነፃ አስተምሮ ማስመረቅ መቻሉንም ተናግረዋል አቶ ተሾመ በቀለ ተናግረዋ።

ይህም ኮሌጁ የሚጠበቅበትን ማህበራዊ ሀላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ማሳያ ነው።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ዴስክ ሀላፊ ትምህርት ሚኒስቴር እንደሀገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ እንደ ደንበል ኮሌጅ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል።

ኮሌጁ የሚገጥሙ ፈተናዎችን በፅናት በመወጣት ሁሌም በየአመቱ ብቁ ተወዳዳሪ ሙያተኞችን ማፍራት መቻሉም የሚያስመሰግነው ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ሳሬም ፈርኒቸር 3ኛ ቅርንጫፉን በቦሌ ቡልቡላ በይፋ ከፈተ​ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ነሐሴ 23,2018የሀገር ውስጥ አቅምን በማጎልበት ረገድ የሚጠቀሰው ሳሬም ፈርኒቸር ጥራታቸውን የጠበቁ ...
29/08/2026

ሳሬም ፈርኒቸር 3ኛ ቅርንጫፉን በቦሌ ቡልቡላ በይፋ ከፈተ

​ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ነሐሴ 23,2018

የሀገር ውስጥ አቅምን በማጎልበት ረገድ የሚጠቀሰው ሳሬም ፈርኒቸር ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቹን ለደንበኞች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ያለመውን 3ኛ ቅርንጫፉን ዛሬ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በቦሌ ቡልቡላ በይፋ ከፈተ።

በዚሁ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የንግድ አጋሮች፣ የስራ አመራሮች፣ የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎችና የይዘት ፈጣሪዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

​ተቋሙ የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱን አስመልካች በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የአዲሱ ቅርንጫፍ መከፈት ተራ የንግድ ማስፋፊያ ሳይሆን የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ የፈርኒቸር ምርቶችን በሀገር በቀል ምርት ለመተካት የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ትልቅ ማሳያ ነው። ሳሬም ፈርኒቸር ጥንካሬን፣ ዘላቂነትን፣ ምቾትን እና ፍትሃዊ ዋጋን መለያው በማድረግ የደንበኞቹን ፍላጎት በጥራት ለማሟላት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።

​ድርጅቱ ቀደም ሲል በቃሊቲ የመጀመሪያውን እንዲሁም በለቡ ሁለተኛውን ቅርንጫፍ ከፍቶ ለአገልግሎት ያበቃ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት በቡልቡላ ያስመረቀው ሶስተኛ ቅርንጫፉ የዚሁ የማስፋፊያ እቅድ አካል ነው። አሰራሩን አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይ አራተኛ እና አምስተኛ ቅርንጫፎቹን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

​ከውጪ የሚመጡ የተጠናቀቁ የፈርኒቸር ውጤቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት ዋነኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለው ድርጅቱ፣ በዚህ እንቅስቃሴው ለበርካታ ዜጎች አዲስ የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል። ድርጅቱ በንግድ ጉዞው ለደረሰበት ስኬት ትልቁ ሀብቱ ደንበኞቹ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ በቀጣይም ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን በታማኝነት ማቅረቡን እንደሚቀጥል ተነግሯል። #ቢዝነስ

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕ...
25/08/2026

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው፥ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአንድነት ይሆን ዘንድ እመኛለሁ ብለዋል።

1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prime Media - አማርኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share