
25/06/2025
ከ8:00 እስከ 10:00 ለሁለት ሰዓታት!
ሰላምና ጤና ይስጣችሁ ውድ አድማጮቻችን!
ረቡዕ ከሠዓት ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም የ"ሔሎ ኢትዮጵያ" ተወዳጅ የሬድዮ ፕሮግራም ይዘቶች የሚከተሉት ናቸው!!
☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ
በሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ ለሀገር ፣ለወገን ታላቅ ስራ የሰሩ ኢትዮጵያዊያንን እናስታውሳለን።በዛሬው ማስታወሻችን አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄን እናስታውሳለን።
☑️የሔሎ ኢትዮጵያ አቨንቶች
በሔሎ ኢትዮጵያ ኤቨንቶች የተመራረጡ ልዩ ልዩ የኤቨንት መረጃዎችን እንጠቋቁማችዋልን።
☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ልዩ እንግዳ
በሔሎ ኢትዮጵያ ልዩ እንግዳ በከተማችን ስለሚካሄደው ኦርጋናይዜሽን ኦፍ ሳውዘርን ኮፕሬሽን ፌስቲቫል ከአዘጋጆች ጋር አጭር የስልክ ቆይታ እናደርጋለን።
☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ሰሞነኛ ጉዳይ
1.የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የግእዝ ቋንቋን በ3ኛ ዲግሪ(PHD) ደረጃ ለማስተማር ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተናገረ።ስለጉዳዩ በዝርዝር ትሰማላችሁ።
2.የመገናኛ ብዙሃን(ቴሌቪዥንና ሬድዮ ጣቢያዎችን ጨምሮ) ለሚያጫውቱት ሙዚቃ ክፍያ የሚፈጽሙበት የሮያሊቲ ክፍያ ቀመርን ተግባዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መምጣታቸው ተነግሯል። በትላንትናው ዕለትም የሮያሊቲ ክፍያ ቀመርን በተመለከተ የተሰራጭ መረጃ አለ።ስለጉዳዩ እንነግራችኋለን።
☑️በሔሎ ኢትዮጵያ ማለፊያ
በዛሬው የሔሎ ኢትዮጵያ ማለፊያ ሠዓት
* አንድ ሺ 340 ዓመቴ ነው የሚሉ ሰው ተገኙ
*አውሮፕላን የጠለፈው ኢትዮጵያና ኢዲ አሚን
* ኢትዮጵያ እንግሊዝን የረዳችበት አጋጣሚ
የሚሉ ርዕስ የተሰጣቸውና ከዓመታት በፊት አነጋጋሪ የነበሩ የታሪክ ማስታወሻዎችን እናቀርብላችኋለን።
☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት
በሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት እናንተ ውድ አድማጮቻችን በቀጥታ ስልክ መስመራችን ላይ በመገኘት አካባቢያችውን የምታስጉብኙበት ሰዓታችን እንደተጠበቀ ነው።
☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች
በሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች ስለ ሙዚቃ የተሰሩ ሙዚቃዎችን እንጋብዛችኋለን።
በመስተንግዶው ማናዬ እውነቱ፣ ናትናኤል ደበና (ናቲ ማናዬ) አብረናችሁ ቆይታ እናደርጋለን።
አጋሮችን አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ነው።
"ሔሎ ኢትዮጵያ" ዘውትር ረቡዕ ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00 ለሁለት ሰዓታት በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ይደመጣል።
ውብ ህዝብ ፤ ውብ ሀገር ፤ ኢትዮጵያ!