Ethio Newsflash

Ethio Newsflash ኢትዮ ኒውስፍላሽ በጋዜጠኞች ሚዛናዊ፣ አዳዲስ እና ፈጣን መረጃዎችን ለአንባቢዎች ያደርሳል።

 #ኒውስፍላሽ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ) ያቀረበውን የምዝገባ ፈቃድ ከለከለ! ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በእነአቶ ዮሐንስ ታደሰ በቁጥር 0...
23/08/2022

#ኒውስፍላሽ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ) ያቀረበውን የምዝገባ ፈቃድ ከለከለ!

ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በእነአቶ ዮሐንስ ታደሰ በቁጥር 001/ምቦ/01/14 በተጻፈ ደብዳቤ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የሀገር ዐቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ እንዲሰጣቸው አመልክተው ነበር።

በዚህም መሠረት ቦርዱ ኢ.ሠ.ፓ በሚል ስያሜ ሀገራዊ ፓርቲ ለማስመዝገብ የቀረበለትን ጥያቄ በምርጫ ዐዋጁ አንቀጽ 69(1) ለ መሠረት ክልከላውን አሳውቋል። ለዝርዝሩ ደብዳቤው ተያይዟል።

“የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” ከሚል ፅሁፍ ጋር በስፋት የተጋራው ምስል በቅንብር የቀረበ ነው። (በኢትዮጵያ ቼክ የቀረበ)ከ865 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ...
22/08/2022

“የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” ከሚል ፅሁፍ ጋር በስፋት የተጋራው ምስል በቅንብር የቀረበ ነው።

(በኢትዮጵያ ቼክ የቀረበ)

ከ865 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና "Mereja TV" የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ “የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” የሚል መረጃ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ከመረጃው ጋር የፈተና ቡክሌት አብሮ የተያያዘ ሲሆን የፌስቡክ ገጹ መረጃውን ያገኘው ከመ/ር ዘመድኩን በቀለ መሆኑን ጠቅሷል። መረጃውን ከ3,700 በላይ ሰዎች ላይክ ያደረጉት ሲሆን 838 ጊዜ ሼር ተደርጓል። በተመሳሳይ ሌሎች የፌስቡክ ገጾችና የቴሌግራም ቻናሎች ይህንኑ መረጃ በስፋት ማጋራታቸውን አስተውለናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማጣራት የተጋራውን ቡክሌት የመረመረ ሲሆን መረጃው ሀሠተኛ መሆኑን አረጋግጧል፣ ለዚህም የተጋራውን ቡክሌት በንጽጽር መርምሯል። በተጨማሪም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን አነጋግሯል።

በንጽጽሩም “የዘንድሮ” ነው ተብሎ የተጋራውን የታሪክ ፈተና ቡክሌት በ2013/14 ዓ.ም የተሰጠ እንጂ አዲስ አለመሆኑን ተመልክተናል። በቡክሌቱ ላይ የሚታዩት ጥያቄዎችም ከ2013/14 ዓመተ ምህረቱ ፈተና ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ መሆናቸውን አይተናል።

ሀሠተኛውን መረጃ ያሰራጩት አካላት በፈተናው ቡክሌት ግርጌ ላይ የሚገኘውን ዓመተ ምህረት ኤዲት በማድረግ ከ2013/14 (2021) ወደ 2014/15 (2022) የቀየሩት ሲሆን በዓመተ ምህረቶቹ መሃል መቀመጥ የነበረበት የእዝባር ምልክት (/) ካለመጠቀም ጀምሮ ግልጽ የመነካካት ስራ መስራታቸው ይታያል።

ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የተሰራጨውን መረጃ መመልከታቸውን ገልጸው ሀሠተኛ መሆኑንና የተጋራው የፈተና ቡክሌት በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል።

በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠን የታሪክ ፈተና ለንጽጽር ይረዳ ዘንድም ለኢትዮጵያ ቼክ አሳይተዋል። ዋና ዳሬክተሩ በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ የኬሚስትሪ ፈተናም በተመሳሳይ ሁኔታ ዓመቱ ኤዲት ተደርጎ ሲሰራጭ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ዶ/ር እሸቱ ተፈታኝ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መሰል መረጃዎችን ከማመናቸው በፊት የአሰራጩን ታማኝነት እንዲያጣሩና ትክክለኛነቱን እንዲመረምሩ መክረዋል።

ፈተናን የተመለከተ መረጃ ሲፈልጉም የፌስቡክ ማረጋገጫ ሰማያዊ ምልክት ባለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፌስቡክ ገጽ በግልም ሆነ በቡድን መልዕክት እንዲልኩ አበረታተዋል።

የአገር አቀፍ ፈተናን የተመለከቱ ሀሠተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትም “ፖለቲካን ከታዳጊዎች ህይዎት ቢለዩ መልካም ነው” ሲሉ አሳስበዋል።

28/05/2022

#ኒውስፍላሽ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ዛሬ ናይሮቢ፣ ኬንያ እየተከናወነ ባለ የአየር ትርኢት ላይ ለመታደም ሲገኙ።

©️ EthioNewsflash

 #ኒውስፍላሽ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በኬንያ ተገኝተው የሀገሪቱን አየር ሀይል ትርኢት እየታደሙ ይገኛል! ጠ/ሚሩ ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በስፍራው ተገኝተው ይህንን አመታዊ የአ...
28/05/2022

#ኒውስፍላሽ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በኬንያ ተገኝተው የሀገሪቱን አየር ሀይል ትርኢት እየታደሙ ይገኛል!

ጠ/ሚሩ ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በስፍራው ተገኝተው ይህንን አመታዊ የአየር ሀይል ትርኢት እየታደሙ መሆኑን በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን መረጃ አድርሶናል፣ ከቀናት በፊት ደግሞ በናይጄርያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ተገኝተው ነበር።

 #ኒውስፍላሽ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያንዳንዳቸው ከ350 ሚልዮን ዶላር በላይ ግምት ያላቸው አምስት የጭነት አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ አዘዘ። ኢትዮ ኒውስፍላሽ ዛሬ የደረሰው መረጃ ...
25/05/2022

#ኒውስፍላሽ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያንዳንዳቸው ከ350 ሚልዮን ዶላር በላይ ግምት ያላቸው አምስት የጭነት አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ አዘዘ።

ኢትዮ ኒውስፍላሽ ዛሬ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው አየር መንገዱ ያዘዘው 777 የተባለውን እጅግ ዘመናዊ የጭነት አውሮፕላን ነው። አውሮፕላኑ በአለም ላይ ካሉ የጭነት (cargo) አውሮፕላኖች ትልቁ እና ዘመናዊው ሲሆን ከሌሎች አውሮፕላኖች በ17% የቀነሰ የነዳጅ ፍጆታ ያለው ነው።

25/05/2022

#ኒውስፍላሽ የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ትናንት ድርጅቱን እንዲመሩ በድጋሜ ሲመረጡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተቃውሞ አሰምተው ነበር!

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር የሆኑት ማህሌት ሀይሉ በቪድዮው ላይ በሚታየው መልኩ የአፍሪካ ቡድን ለዶ/ር ቴድሮስ በቦትስዋና አማካኝነት እንዳይቀርብ ጠይቀው ነበር። በመጨረሻ ግን ምርጫው ተካሂዶ ዶ/ር ቴድሮስ ድርጅቱን በቀጣይ አመታት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

24/05/2022

#ኒውስፍላሽ ፋና፣ ኢቢሲ፣ ዋልታ፣ ኢፕድ እና ኢዜአ ትናንት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በታይም መፅሄት "ተፅእኖ ፈጣሪ ሆነው ተመረጡ" ብለው ያቀረቡትን ዜና ሁሉም አጥፍተውታል።

 #ኒውስፍላሽ የጠ/ሚር ፅ/ቤት የታይም መፅሄትን በስም ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ! ትናንት ከአለም ተፅእኖ ፈጣሪዎች አንዱ ብሎ መፅሄቱ የመረጣቸው ጠ/ሚር አብይ ላይ "ሆን ተብሎ የስም ማጥፋት እ...
24/05/2022

#ኒውስፍላሽ የጠ/ሚር ፅ/ቤት የታይም መፅሄትን በስም ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ!

ትናንት ከአለም ተፅእኖ ፈጣሪዎች አንዱ ብሎ መፅሄቱ የመረጣቸው ጠ/ሚር አብይ ላይ "ሆን ተብሎ የስም ማጥፋት እና ስብእናን የማጉደፍ ስራ ተሰርቷል" ይላል በቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ተፅፎ ከደቂቃዎች በፊት ለሚድያዎች የተሰራጨው ደብዳቤ።

ለዚህም አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ መፅሄቱ ተጠይቋል። በትናንትናው እለት የመንግስት ሚድያዎች ጉዳዩን እንደበጎ ነገር በሰበር ዜና ሲያራግቡት እንደነበር ይታወሳል።

ግንቦት 30 በካፒታል ሆቴል በሚካሄደው የጣፋጭ ሕይወት ሽልማት ላይ የእርሶ ማህበራዊ ሚድያውን ለመልካም ምግባር የተጠቀመው ማን ነው?ኮሜንት ያድርጉ ግንቦት 30 በካፒታል ሆቴል በደማቅ ስነ ...
23/05/2022

ግንቦት 30 በካፒታል ሆቴል በሚካሄደው የጣፋጭ ሕይወት ሽልማት ላይ የእርሶ ማህበራዊ ሚድያውን ለመልካም ምግባር የተጠቀመው ማን ነው?
ኮሜንት ያድርጉ ግንቦት 30 በካፒታል ሆቴል በደማቅ ስነ ስርዓት ሽልማቱ ይሰጣል።
#ቅን ልባዊ ድርጊት
ለጣፋጭ ህይወት

 #ኒውስፍላሽ የመንግስት ሚድያዎች ችኩልነት ወይስ አንባቢን መናቅ? በፋንታሁን ወርቁ ለኢትዮ ኒውስፍላሽ ታዋቂው 'ታይም' መፅሄት ጠ/ሚር አብይ አህመድን ከአመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መሀል ማካተ...
23/05/2022

#ኒውስፍላሽ የመንግስት ሚድያዎች ችኩልነት ወይስ አንባቢን መናቅ?

በፋንታሁን ወርቁ ለኢትዮ ኒውስፍላሽ

ታዋቂው 'ታይም' መፅሄት ጠ/ሚር አብይ አህመድን ከአመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መሀል ማካተቱ በመንግስት ሚድያዎች በስፋት ቢዘገብም የተመረጡበት መስፈርት ተብሎ በመፅሄቱ የቀረቡት ነጥቦች ግን ከፍተኛ ወቀሳ ያዘሉ ናቸው።

የጠ/ሚር አብይ አህመድን ክፍል መፅሄቱ ላይ ያሰፈረው ታዋቂው የታይም ዘጋቢ አርያን ቤከር ሲሆን በርካታ ነጥቦችን አንስቷል።

ለምሳሌ:

- የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች የሰላም ስምምነት በቀጠናው ተስፋ ጭሮ የነበረ ቢሆንም ለኢትዮጵያው እርስ በርስ ጦርነትም ዘር ዘርቷል።

- ይህ 19 ወር ያስቆጠረ ጦርነት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ ግድያዎች፣ የፆታ ጥቃቶች እና የዘር ማጥፋት ምክንያት ሆኗል።

- ጠ/ሚሩ "አረም" ብለው የጠሯቸው ታጣቂዎች ላይ ዘመቻ አካሂደዋል። የአፍሪካ ሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች በርዋንዳ የተከሰተው አይነት እልቂት እንዳይከሰት ተመድን እየተማፀኑ ይገኛል።

- የኖቤል የሰላም ድርጅት የዛሬ አራት ወር ባልተለመደ መልኩ የኮነነ ሲሆን "ጠ/ሚሩ ጦርነቱን የማስቆም ሀላፊነት አለባቸው" ብሏል።

ከላይ የተቀመጡት ነጥቦች በመፅሄቱ ላይ ቢሰፍሩም አንዱንም ነጥብ ያላነሱት የመንግስት ሚድያዎች ግን ዜናውን እንደበጎ ነገር በስፋት ዘግበውታል። ታድያ ይሄ ችኩልነት ነው ወይስ አንባቢን መናቅ?

 #ኒውስፍላሽ የጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬን እስር/አፈና በተመለከተ ኢትዮ ኒውስፍላሽ ከእህቱ ትግስት ሹምዬ ጋር ያረገው አጭር ቃለመጠይቅ ትናንት ጠዋት ምን ነበር የተከሰተው?ትግስት: ጠዋት ላይ ...
21/05/2022

#ኒውስፍላሽ የጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬን እስር/አፈና በተመለከተ ኢትዮ ኒውስፍላሽ ከእህቱ ትግስት ሹምዬ ጋር ያረገው አጭር ቃለመጠይቅ

ትናንት ጠዋት ምን ነበር የተከሰተው?
ትግስት: ጠዋት ላይ ለሰለሞን እንደሁሌው ቁርስ ላደርስለት ስሄድ በር የሚያንኳኳ ሲቪል የለበሰ ሰው አገኘሁ። ምን እንደሚፈልግ ስጠይቀው ሊነግረኝ አልፈለገም፣ ከዛም ሄደ። እኔም ወደቤቴ ተመልሼ ኋላ ላይ ቆየት ብዬ ሰለሞን ቤት ስመለስ ሌሎች ሲቪል የለበሱ ሰዎችን አገኘሁ። በግድ ቤቱን ክፈቺ አሉኝ፣ እኔ ደግሞ ስለተጠራጠርኩ ለጎረቤቶች ፖሊስ እንዲጠሩ ነገርኳቸው። መታወቂያ እንኳን ሊያሳዩኝ አልፈለጉም። ፖሊሶች ሲመጡ ግን እያመናጩቁኝ ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱኝ።

ሰለሞን እንዴት ተያዘ?
ትግስት: ሰለሞንን ፖሊስ ጣብያ ነው ያገኘሁት። ስልኩን ቀምተው ከዛም ቤቱ ፍተሻ አርገዋል። ምንም ነገር አላገኙም። ሰለሞን ከመጣ በኋላ ሁለት ሰአት አቆይተው እኔን ለቀቁኝ።

ሰለሞን አሁን የት ነው?
ሶስተኛ ፖሊስ ጣብያ ነው። ምግብ እና ልብስ አድርሼለታለሁ።

ፍርድ ቤት ዛሬ ምን ተባለ?
ትግስት: ዛሬ ጠዋት ሶስተኛ አካባቢ ያለው ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ቃል በቃል ባላስታውሰውም ብጥብጥ እንዲፈጠር አነሳስተሀል ምናምን የሚል ክስ አንብበዋል፣ ክሱ ለብቻው ሳይሆን ሌሎችን ስዎችን ያካተተ ነበር።

Address

4 Kilo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Newsflash posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share