ኢትዮ SPORT

ኢትዮ SPORT የተለያዩ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ እግር ኳሳዊ መረጃዎች
?

♨ ማንችስተር ዩናይትድ በወራጅ ቀጠና ቡድን ተሸንፏል!- ወደ ሞኒሊዩ ስቴዲየም አምርተው በወራጅ ቀጠና የሚገኘውን ዎልቭስን የገጠሙት ማንችስተር ዩናይትዶች 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈው ወጥተዋ...
26/12/2024

♨ ማንችስተር ዩናይትድ በወራጅ ቀጠና ቡድን ተሸንፏል!

- ወደ ሞኒሊዩ ስቴዲየም አምርተው በወራጅ ቀጠና የሚገኘውን ዎልቭስን የገጠሙት ማንችስተር ዩናይትዶች 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈው ወጥተዋል።

- በጨዋታው ብሩኖ ፈርናንዴዝ በሰራው ጥፋት ሁለት ቢጫ በመመልከቱ በቀይ ካርድ ከሜዳው ተሰናብቷል።

- ማንችስተር ዩናይትዶች ባደረጓቸው የመጨረሻ ሶስት ጨዋታዎችን ሶስቱንም በሽንፈት አጠናቀዋል።

♨ ቼልሲ እና ቶተንሃም ተሸንፈዋል!- በ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ ፋልሀምን አስተናግዶ በፓልመር ጎል እስከ 84ኛው ደቂቃ ቢመራም ለፋልሀም ሀሪ ዊልሰን እና ሙኒዝ ባ...
26/12/2024

♨ ቼልሲ እና ቶተንሃም ተሸንፈዋል!

- በ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ ፋልሀምን አስተናግዶ በፓልመር ጎል እስከ 84ኛው ደቂቃ ቢመራም ለፋልሀም ሀሪ ዊልሰን እና ሙኒዝ ባስቆጠራቸው ጎሎች ሰማያዊዎቹ ጨዋታውን 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

- በሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ በኤላንጋ ጎል ቶተንሀም በኖቲንግሀም ፎረስት ጋር 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፋል።

- ቼልሲ ተከታታይ ሁለት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

- በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ኒውካስል ዩናይትድ አስቶንቪላን 3ለ0 እንዲሁም ዌስትሀም ዩናይትድ ሳውዛምፕተንን 1ለዐ ማሸነፍ ችለዋል።

♨ የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ አሁንም ማሸነፍ አልቻለም! - በ 18 ኛው ሳምንት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከኤቨርተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋ...
26/12/2024

♨ የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ አሁንም ማሸነፍ አልቻለም!

- በ 18 ኛው ሳምንት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከኤቨርተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- ማንችስተር ሲቲን በርናርዶ ሲልቫ ግብ መምራት ቢችልም ንዲዬን ለኤቨርተን ባስቆጠራት ጎል ሲቲ ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

- በጨዋታው ኤርሊንግ ሀላንድ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀም ቀርቷል።

- ማንችስተር ሲቲ ካለፉት 13 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ጨዋታ ሲሆን በ 9 ጨዋታዎች ሽንፈት ቀምሷል።

♨ ማንችስተር ሲቲ ዛሬም ተሸንፏል!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወደ ቪላ ፓርክ ስቴዲየም አምርተው አስቶንቪላን የገጠሙት ማንችስተር ሲቲዎች 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈው ወጥተዋል።- ለአ...
21/12/2024

♨ ማንችስተር ሲቲ ዛሬም ተሸንፏል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወደ ቪላ ፓርክ ስቴዲየም አምርተው አስቶንቪላን የገጠሙት ማንችስተር ሲቲዎች 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈው ወጥተዋል።

- ለአስቶን ቪላ ጎሎቹን ዱራን እና ሮጀርስ ሰሲያስቆጥሩ ለሲቲ ብቸኛዋን የማስተዛዘኛ ግብ ፎደን አስቆጥሯል።

- የፔፕ ጋርዲዮላው ሲቲ ባለፋት 11 ተከታታይ ጨዋታዎች በ 9 ጨዋታዎች ሲሸነፍ ማሸነፍ የቻለው 1 ጨዋታ ብቻ ነው።

- ሲቲ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ27 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

® የፔፕ ጋዲዮላው ማንችስተር ሲቲ በዚህ ሲዝን በ TOp 4 መጨረስ የሚችል ይመስላችኋል?

♨ BREAKING: ዩክሬናዊው የቼልሲ ኮኮብ ማይካሂሎ ሙድሪክ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ባደረገበት የአበረታች ንጥረ ነገር ምርመራ Positive ሆኖ በመገኘቱ ተጫዋቹ ከየትኛው የእግር ኳ...
17/12/2024

♨ BREAKING: ዩክሬናዊው የቼልሲ ኮኮብ ማይካሂሎ ሙድሪክ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ባደረገበት የአበረታች ንጥረ ነገር ምርመራ Positive ሆኖ በመገኘቱ ተጫዋቹ ከየትኛው የእግር ኳስ ውድድሮች እንዳይሳተፍ መታገዱ ይፋ ተደርጓል።

- ሙድሪክ በቀጣይ Sample 'B' ተመርምሮ ውጤቱ Negative ከሆነ ውሳኔው የሚነሳለት ሲሆን ነገር ግን የሳምፕሉ ምርመራ በድጋሚ Positive ሆኖ ከተገኘ ተጫዋቹ ምናልባትም እስከ 4 አመት ድርስ ወደ እግር ኳስ ዝር እንዳይል እገዳ ሊጣልበት እንደሚችል መረጃዎች ያመላክታሉ።

"እኔ የምከተለው አሰልጣኛችንን ሲስተም ነው። እሱ በከፍተኛ መጠን ፕሬስ እንድናደርግ ከኛ ይጠብቃል። እኔም ፕሬስ ሳደርግ በ 100% አቅሜ ነው ከጎኔ ሌላ ተጫዋች ይኑር አይኑር ግድ አይሰጠኝ...
16/12/2024

"እኔ የምከተለው አሰልጣኛችንን ሲስተም ነው። እሱ በከፍተኛ መጠን ፕሬስ እንድናደርግ ከኛ ይጠብቃል። እኔም ፕሬስ ሳደርግ በ 100% አቅሜ ነው ከጎኔ ሌላ ተጫዋች ይኑር አይኑር ግድ አይሰጠኝም።" - አማድ ዲያሎ

♨ ሩበን አሞሪም ቴን ሃግ በሁለት አመት ተኩል በላይ ቆይቶ ማድረግ ያልቻለውን አድርጓል!- በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነት ከተቀጠረ ገና ጥቂት ሳምንታት የቆየው ሩበን አሞሪም በእንግሊዝ ...
15/12/2024

♨ ሩበን አሞሪም ቴን ሃግ በሁለት አመት ተኩል በላይ ቆይቶ ማድረግ ያልቻለውን አድርጓል!

- በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነት ከተቀጠረ ገና ጥቂት ሳምንታት የቆየው ሩበን አሞሪም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ቴን ሃግ ግን በዩናይትድ አሰልጣኝት ከሁለት አመት ተኩል በላይ ቆይቶ በሊጉ ከሜዳው ውጪ አንድም የ Top 6 ቡድን ማሸነፍ አልቻለም!

- ሩበን አሞሪም ከ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ የመጀመሪያ የማንችስተር ደርቢ ጨዋታቸውን ያሸነፉ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆነዋል።

♨ ማንችስተር ዩናይትድ በአማድ ዲያሎ ምትሀታዊ ብቃት ኢትሀድ ላይ ማንችስተር ሲቲን አሸንፏል!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ተጠባቂው የማንቹሪያን ደርቢ ኢትሀድ ስቴዲየም ላይ ማንችስተር ዩናይት...
15/12/2024

♨ ማንችስተር ዩናይትድ በአማድ ዲያሎ ምትሀታዊ ብቃት ኢትሀድ ላይ ማንችስተር ሲቲን አሸንፏል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ተጠባቂው የማንቹሪያን ደርቢ ኢትሀድ ስቴዲየም ላይ ማንችስተር ዩናይትድ የፔፕ ጋዲዮላውን ማንችስተር ሲቲ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ወጥቷል።

- ማንችስተር ሲቲዎች በግቫርዲዮል ብቸኛ ግብ እስከ 87ኛው ደቂቃ ድረስ ምራት ችለው የነበረ ቢሆንም 88ኛው ደቂቃ ላይ አማድ ዲያሎ ላይ በተሰራች ጥፉት የተገኘችውን ፍፁም ቅጣት ምት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሲያስቆጥር እንዲሁ 90ኛው ደቂቃ ላይ አማድ ዲያሎ በአስደናቂ አጨራረስ ሁለተኛዋን ግብ በማስቆጠር ዩናይትድን አሸናፊ አድርጓል።

♨ ሊቨርፑል እና አርሰናል ነጥብ ጥለዋል! - በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ከፉልሀም ጋር 2ለ2 እንዲሁም አርሰናል ኤቨርተን 0ለዐ በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። -,የፉ...
14/12/2024

♨ ሊቨርፑል እና አርሰናል ነጥብ ጥለዋል!

- በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ከፉልሀም ጋር 2ለ2 እንዲሁም አርሰናል ኤቨርተን 0ለዐ በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

-,የፉልሀምን ግቦች ፔሬራ እና ሙኒዝ ሲያስቆጥሩ ጋክፖ እና ጆታ ለ ሊቨርፑልን አስቆጥረዋል።

- አርሰናል በዘንድሮው የውድድር አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ተጫውቶ ግብ ሳያስቆጥር ወጥቷል።

- ፕሪሚየር ሊጉን ሊቨርፑል በ 36 ነጥብ ሲመራ ቼልሲ በ 31 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ አርሰናል በ 30 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

♨ ሩበን አሞሪም ኦልትራፎርድ ላይ የመጀመሪያ ሽንፈት ቀምሷል!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታ ኖቲንግሀም ፎረስትን ኦልትራፎርድ ላይ ያስተናገዱት ማንችስተር ዩናይትዶች 3ለ2 ...
07/12/2024

♨ ሩበን አሞሪም ኦልትራፎርድ ላይ የመጀመሪያ ሽንፈት ቀምሷል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታ ኖቲንግሀም ፎረስትን ኦልትራፎርድ ላይ ያስተናገዱት ማንችስተር ዩናይትዶች 3ለ2 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

- ለ ኖቲንግሀም ሶስቱን ጎሎች ሚሌንኮቪች፣ ጊብስ ዋይት እና ዉድ ሲያስቆጥሩ ለዩናይትድ ሆይሉንድ እና ፈርናንዴዝ አስቆጥሯል።

- አሞሪም በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነቱ በ 4 ቀናት ውስጥ በተከታታይ ሁለት የሊግ ጨዋታዎችን ተሸንፏል።

"ፔፕ ጋርዲዮላ ትላንት ስለ እኔ የሆነ ነገር ብሎ ነበር.... እሱ ስድስት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል እኔ ደግሞ ለሶሰት ጊዜ ዋንጫውን አሸንፌያለሁ ነገር ግን እኔ እነዛን ዋንጫዎች ፍትሀዊ...
06/12/2024

"ፔፕ ጋርዲዮላ ትላንት ስለ እኔ የሆነ ነገር ብሎ ነበር.... እሱ ስድስት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል እኔ ደግሞ ለሶሰት ጊዜ ዋንጫውን አሸንፌያለሁ ነገር ግን እኔ እነዛን ዋንጫዎች ፍትሀዊ በሆነ እና በግልፅ ሁኔታ ነው ዋንጫዎቹን ያሸነፍኩት።

እኔ ከ 150 ክሶችን እያስተናገድኩ ዋንጫ ማሸነፍ አልፈልግም

ከተሸነፍኩ ተጋጣሚዬን ለድልህ እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ።" - ጆዜ ሞሪንሆ

ፔፕ ጋርዲዮላ በሊቨርፑሉ ጨዋታ በእጃቸው 6 ጊዜ ያህል የሊጉን ዋንጫ ማሸነፋቸውን ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ማሳየታቸውን ተከትሎ በጋዜጣዊ መግለጫ ስማቸው ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር ተመሳሳይነት እንደዳለው ጥያቄ ተነስቶ ፔፕ ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል። በዚህም አወዛጋቢው ጆዜ ለፔፕ ንግግር አስገራሚ አስተያየት ሰጥተዋል። [Via: Mail Sport]

♨ አርሰናል ዩናይትድን ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ነጥብ ጥሏል!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን አስተናግዶ በቲምበር እና ሳሊባ ጎሎች 2ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።...
04/12/2024

♨ አርሰናል ዩናይትድን ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ነጥብ ጥሏል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን አስተናግዶ በቲምበር እና ሳሊባ ጎሎች 2ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።

- ሊቨርፑልን ከኒውካስትል ጋር ሶስት አቻ ሲለያይ ለሊቬ ግቦቹን መሐመድ ሳላህ 2x እና ጆንስ ሲያስቆጥር ለኒውካስል አይሳክ ፣ ሻር እና ጎርደን ከመረብ አሳርፈዋል።

- ማንችስተር ሲቲ ኖቲንግሃምን አስተናግዶ በዴብሮይን ፣ ዶኩ እና ሲልቫ ግቦች 3ለ0 አሸንፏል።

- ቼልሲ በ ዲሳሲ ፣ ንኩንኩ ፣ ማዱኬ ፣ ፓልመር እና ሳንቾ ጎሎች ሳውዝሀምፕተንን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

በሌላ ጨዋታ ኤቨርተን ከዎልቭስ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 4ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

- ሊቨርፑል ሊጉን 35 ነጥብ ሲመራ አርሰናል እና ቼልሲ በ 28 ነጥብ ይከተላሉ።

" ኮል ፓልመር እና ጆዋኦ ፌሊክስ ሰዎች የትኬት ክፍያ ከፍለው እግር ኳስን እንዲመለከቱ የሚያደርጉ አይነት ተጫዋቾች ናቸው። ይሄንን ስል ሌሎች ጥሩ ተጫዋቾች አይደሉም እያልኩ አይደለም ነገር...
02/12/2024

" ኮል ፓልመር እና ጆዋኦ ፌሊክስ ሰዎች የትኬት ክፍያ ከፍለው እግር ኳስን እንዲመለከቱ የሚያደርጉ አይነት ተጫዋቾች ናቸው። ይሄንን ስል ሌሎች ጥሩ ተጫዋቾች አይደሉም እያልኩ አይደለም ነገር ግን ሁለቱ ተጫዋቾች የተለዩ ናቸው። ይህ ግልፅ ነው።" - ኤንዞ ማሬስካ

♨ አርኔ ስሎት በዚህ ሲዝን ፔፕ ጋርዲዮላን፣ ካርሎ አንቼሎቲን፣ ዣቢ አሎንሶን እና ኤሪክ ቴንሃግን አሸንፏል። እነዚህን አሰልጣኞች እያንዳንዱ ሲያሸንፍ አንድም ጎል አልተቆጠረበትም! 😳እነሆ ...
01/12/2024

♨ አርኔ ስሎት በዚህ ሲዝን ፔፕ ጋርዲዮላን፣ ካርሎ አንቼሎቲን፣ ዣቢ አሎንሶን እና ኤሪክ ቴንሃግን አሸንፏል። እነዚህን አሰልጣኞች እያንዳንዱ ሲያሸንፍ አንድም ጎል አልተቆጠረበትም! 😳

እነሆ እውነተኛው መላጣ ወደ መድረኩ መጥቷል! 🫡

♨ አርኔ ስሎት በእውነቱ ክብር ይገባዋል! 🫡 - በአለማችን ትልቁ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገና በመጣበት የመጀመሪያ ሲዝኑ ይህንን አይነት ክስተታዊ ቡድን አደራጅቶ ሊጉን በሰፊ የነጥብ ...
01/12/2024

♨ አርኔ ስሎት በእውነቱ ክብር ይገባዋል! 🫡

- በአለማችን ትልቁ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገና በመጣበት የመጀመሪያ ሲዝኑ ይህንን አይነት ክስተታዊ ቡድን አደራጅቶ ሊጉን በሰፊ የነጥብ እርቀት እየመራ ይገኛል። ይሄንን የውድድር ሲዝን ጨምሮ ባየናቸው ተከታታይ ሶስት ሲዝኖች የፔፕ ጋርዲዮላውን ማንችስተር ሲቲ በሊጉ በቅርበት ሲፎካከር የነበረው አርሰናል የነበረ ቢሆንም አሁን ምን እንደተፈጠረ ተመልከቱ። በቻምፒዮንስ ሊጉም ሪያል ማድሪድን ጨምሮ ከ 5 ጨዋታ 5 በማሸነፍ ብቸኛው ቡድን ነው! አስቡት ለዛውም በመጀመሪያ ሲዝኑ! 😳

Just a WOW 😳👌👏

♨ ሊቨርፑል ሲቲን በማሸነፍ ብቻውን እየተጓዘ ነው!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ ማንችስተር ሲቲን አስተናግዶ በጋክፖ እና ሞሀመድ ሳ...
01/12/2024

♨ ሊቨርፑል ሲቲን በማሸነፍ ብቻውን እየተጓዘ ነው!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ ማንችስተር ሲቲን አስተናግዶ በጋክፖ እና ሞሀመድ ሳላህ ጎሎች 2ለ0 በሆነ ውጤት አሽንፏል።

- የ ፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ 4ኛ ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

- አስደናቂው አርኔ ስሎት በሊቨርፑል አስደማሚ ጉዞ እያደረገ ሲገኝ የፕርሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ከሁለተኛ ደረጃ ካለው ክለብ በ9 ነጥብ ርቆ በ34 ነጥብ ብቻውን እየገሰገሰ ይገኛል። ሲቲ ወደ 5ኛ ደረጃ ተንሸራቷል።

♨ ከረጅም አመታት በኋላ ማንችስተር ዩናይትድ እንደ ቡድን አሳማኝ ብቃት አሳይቶ አሸንፏል! - በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን ኦልትራፎርድ ስቴዲ...
01/12/2024

♨ ከረጅም አመታት በኋላ ማንችስተር ዩናይትድ እንደ ቡድን አሳማኝ ብቃት አሳይቶ አሸንፏል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን ኦልትራፎርድ ስቴዲየም ላይ አስተናግዶ በማርከስ ራሽፎርድ እና ዚርክዚ ሁለት ሁለት ግቦች 4ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።

- አስደናቂው ሩበን አሞሪም ከዘመናት በኋላ በኦልትራፎርድ ደጋፊዎችን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ አስደስቶ እና አይደንቲቲ ያለው ቡድን አሳይቶ በአሳማኝ የቡድን ብቃት በሰፊ ጎል አሸንፎ ወጥቷል።

- በብዙ የክለቡ ደጋፊዎች የሚወቀሰው ማርከስ ራሽፎርድ እስከነ ድክመቶቹ ወደ ግብ አስቆጣሪነቱ ተመልሷል።

- በአሞሪም ዘመን በዩናይትድ ቦታ አይኖረውም፣ ቀርፋፋ ነው ምናምን እየተባለ ሲወቀስ የኖረው ዚርክዚ ብቃቱን አውጥቶ ማሳየት ችሏል።

- አማድ ዲያሎ በሩበን አሞሪም ዘመን ታላቅ ተጫዋች ለመሆን ነገሮች የሰመሩለት ይመስላል።

- ቀጣዩ ጨዋታ ከአስደናቂው የሚኬል አርቴታው አርሰናል ጋር ነው። አሞሪም ትልቁን ፈተና በብቃት የሚወጣው ይሆናል? ወይስ?

♨ አማድ ዲያሎ ምን አይነት ድንቅ ተጫዋች ነው!? አንቶኒን በዛ ሁሉ ገንዘብ መጥቶ የአማድን ግማሽ ያህል ብቃት ማሳየት አልቻለም!
01/12/2024

♨ አማድ ዲያሎ ምን አይነት ድንቅ ተጫዋች ነው!? አንቶኒን በዛ ሁሉ ገንዘብ መጥቶ የአማድን ግማሽ ያህል ብቃት ማሳየት አልቻለም!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ SPORT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share