
13/09/2023
ስለ ክብር Dr ጥላሁን ገሰሰ ንጉሴ አስገራሚ እውነታዎች !!
====================================
ክቡር አርቲስት ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ የተወለደው ኦሮሚያ ክልል ወሊሶ አመያ የሚትባል አከባቢ መሆኑና አዲስ አበባ እንደተለወለደ የምነገረውና የተፃፈው መረጃ ስህተት መሆኑ።
ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ በሁለት ስምና በሦስት የተለያዩ የአባት ስሞች ይጠራ ነበር። ወላጅ አባቱ አያኖ ጉዴታ እና ወላጅ እናቱ ወ/ሮ ጌጤ ጉርሙ ያኢ ይባላሉ።
የመጀመሪያ ስሙ :- ደንደና አያኖ ጉዴታ ከወላጅ አባቱ ያገኘ ሲሆን እናቱ ወ/ሮ ጌጤ ጉርሙ ያኢ ከወላጅ አባቱ ጋር ባለመግባባት ትዳራቸው ሲፈርስ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቱሉ ቦሎ በመሄድ ከሌላ ሰው ጋር ትዳር መስርተው መኖር ጀመሩ።
ሁለተኛ ስሙ :- ደንደና አሰፋ ይህን ስም ያገኘው ወላጅ እናቱ ቱሉ ቦሎ ላይ ከአቶ አሰፋ ፊጣ የሚባል ሰው ጋር በትዳር ሲጣመሩ በእንጀራ አባቱ ስም መጠራት ጀመረ። ስለዚህ ስሙ ከደንደና አያኖ ወደ ደንደና አሰፋ ተቀየረ ። 4ኛ ክፍል እስኪያጠናቅቅ ድረስ ደንደና አሰፋ በሚል ስም ይጠራ ነበር።
ቱሉ ቦሎ አከባቢ ጥላሁን ገሰሰ Nickname ያለው ሲሆን ካለው የሙዚቃ ብቃት ተነስተው " Shubbisa " ሹቢሳ በሚል ይጠሩት ነበር።
ሦስተኛ ስም:- ጥላሁን ገሰሰ ንጉሴ ሲሆን ይህን ስም ያገኘው የእንጀራ አባቱ በመሬት ግጭት ከነበሩት ሹማምንት ጋር ተጋጭተው በመጨረሻም በዚህ ምክንያት ሽፍታ ተብሎ በመገደሉ ወላጅ እናቱ ከአመያ ወደ ቱሉ ቦሎ በእድገት ተቀይሮ አስተዳዳሪ ሆኖ የተመደበ ገሰሰ ንጉሴ የተባለ ሰው ጋር በአጋጣሚ ተገናኝተው ችግራቸውን ስታወጋው ቱሉ ቦሎ ላይ ከሚስቱ ወ/ሮ ስመኝ ብዙነህ ጋር በጋራ በከፈቱት ጠጅ ቤት ወ/ሮ ጌጤ ጉርሙና ልጃቸው ደንደና አሰፋ ተቀጥረው እንዲሰሩ ስራ በተሰጣቸው ጊዜ ነው። እናትና ልጅ ሦስት ዓመት ከሰሩ በኃላ ወ/ሮ ጌጤ ጉርሙ ልጃቸው ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄድላቸው ለአሰሪያቸው አቶ ገሰሰ ንጉሴ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ሲያገኝ የደንደና አሰፋ ስም ወደ ጥላሁን ገሰሰ ንጉሴ ተቀይሮ ዳግም ወደ ትምህርት ገበታው ተመልሷል።
በመጨረሻም ጥላሁን ገሰሰ/ደንደና አሰፋ/ደንደና አያኖ እንደ ማንኛውም ኦሮሞ ወጣት በግዳጅ Imperial Bodyguard "IBG" ክቡር ዘበኛ በውትድርና በኃላም በድምፃዊነት ያገለገለ ሲሆን ከ 12 ዓመት በኃላ በድምፃዊነት የሀገር ፍቅር ቲያትር መቀላቀል ችሏል።
እውነት ትቀጥናለች እንጅ አትበጠስም !
ታሪክን የኃሌት !