
20/11/2023
ሼር አድርጉት 🙏
ልጃችን ከተወለደች ከዘጠኝ ቀኗ ጀምሮ አተነፋፈሷ ልክ ስላልመሰለን ወደ ህክምና ወስደናት ነበረ። ሀኪሞቹ ምንም እንዳልሆነችና ይኼ የሁሉም ህጻናት ባህሪይ መሆኑን ነግረውን መለሱን።
ከቆይታ በኋላም ነገሩ እረፍት ስለነሳን ወደ ሌላ ሀኪም ሄድን በተደጋጋሚም ለማሳከም የሞከርነው ሙከራ በተመሳሳይ መልስ የታጀበ ሆነ።
ነገር ግን ከቀን ወደቀን ነገርየው እየባሰ ሰውነቷም እየቀነሰ ሲመጣ ___ ሆስፒታል ስንሄድ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ነግረውን ወደ ጥቁር አንበሳ የልብ ህሙማን ማዕከል ሪፈራል ተጽፎልን ስንሄድ ስድስት ወር ሳይሞላት መታከም እንደነበረባት ነገሩን።
የልቧ ህመም ሳንባዋ ላይ ተጽዕኖ በማሳደሩ አሁን ያለችበት ሁኔታ በጣም አስጊና ቶሎ ከሀገር ወጥታ ህክምና ልታገኝ የሚገባው ደረጃ ላይ መድረሷን አረዱን።
ለህክምናውም ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል።
ይኼ ደግሞ በኛ አቅም የማይቻል በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የአቅሙን እንዲረዳን ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም እንማጸናለኔ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ
0965655869
0912361232
0929293322
የእናት ስም ሰላም ማዘንጊያው
1000458987282