
05/07/2025
ለፋንትሽ በቀለ ሽልማት እንጂ ስም ማጥፋት አይገባትም !
ሁለገቧ አርቲስት ፋንትሽ በቀለ በውዝዋዜ ፣ በድምፃዊነት ፣
በውዝዋዜ አሰልጣኝነት ሀገሯን ያገለገለች አመለ ሸጋ
አርቲስት ነች።
መቼም በማይደገመው ዓለምን የዞሩበት ሕዝብ ለሕዝብ የኪነጥበብ ጉዞ ላይ በውዝዋዜና በድምፃዊነት
በተለይ ከአንጋፋው ድምፃዊ ማሕሙድ አህመድ ጋር
እየተቀባበለች በመዝፈን ለኪነጥበቡ ትልቅ አሻራ ያስቀመጠች ክብር የሚገባት አርቲስት ነች።
በአሜሪካ ሀገር ተወልደው ያደጉ ልጆችን የሀገራቸውን
ባህል እንዳይረሱ የሁሉንም ብሔረሰብ ውዝዋዜ
እያሰለጠነች የምትገኝ ሽልማት የሚገባት አርቲስት
እንጂ ለዓመታት በመልካም ስራ የገነባችውን ስሟን
ለመናድ የተሄደበት ርቀት ልክ አይደለም።
ሰሞኑን ድምፃዊ ፋሲል ደመወዝ አሜሪካ ሀገር በሚዘጋጀው
ዓመታዊ ውድድር ላይ ፋንትሽ እንዳልዘፍን አድርጋኛለች
የሚል ወቀሳ በቲክቶክ ገፁ ላይ በቀጥታ ስርጭት ላይ
ሲናገር ተመልክተነዋል።
ፋንትሽም በዚህ ዙሪያ ተጠይቃ ስትመልስ ፦
በፍፁም የተወራው ሁሉ ውሸት ነው። እንዲያውም ፋሲል ደመወዝ ይቅርታ ሁሉ ጠይቆኛል። ካላመናችሁ አብሮት
ስራው ላይ የነበረውን ድምፃዊ አሸብር በላይ ይመስክር
በማለት ምላሿን ሰጥታለች።
የፋንትሽም የፋሲልም ጓደኞች የሆኑት
ተወዛዋዥ ታደለ እና ተወዛዋዥ ጌጤነሽ
ፋንትሽ ላይ የተወራው ፍፁም ስህተት መሆኑን መስክረዋል።
ሁለገቧ አርቲስት ፋንትሽ በቀለ አሜሪካ ሀገር ላይ
አንድም ቀን ስሟ በመጥፎ ጎን ሳይነሳ ፣ አርቲስቶችም
ሆኑ የአርቲስቶች ቤተሰቦች አሜሪካ ሲመጡ ኤርፖርት ድረስ
እየሄደች የምትቀበል ፣ በሀዘኑም ሆነ በደስታው ጊዜ
ከሌሎች አርቲስቶች ጋር ቦታው ላይ በመገኘት ሀዘንና
ደስታቸውን የምትጋራ ፣ እጅግ ሰው አክባሪ እንደሆነች
በተደጋጋሚ ጊዜ በርካቶች ምስክርነት ሲሰጡ ተመልክተናል።
የቪዲዮ ምስሎቹንም አይተናል።
ፋንችሽ አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተወልዳ ያደገች
የአራድዬ ልጅ ናት። ፈረንሳይ ለጋሲዮን አንዳንድ እርዳታ
የሚያስፈልጋቸው ወገኖቿን በተለይ የኮረና በሽታ ጊዜ
ገንዘብ ከራሷም ኪስ እንዲሁም ከሌሎች እያስተባበረች
የረዳች ከዘ*ረኝ*ነት የፀዳች ንፁህ ኢትዮጵያዊት ናት።
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራም ተለይቷት አያውቅም።
ለዓመታት አብረው በልተው ጠጥተው በሀዘኑም በደስታውም የሚገናኙ ሰዎች ናቸው ፋንትሽና ፋሲል።
ፋንትሽ በኪነጥበቡም ሆነ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለዓመታት ድምጿ በመጥፎ ሳይነሳ የሰራችውን
መልካም ስራ እና የገነባችውን መልካም ስብእና ያልሆነ ወሬ አስወርቶ ስሟን ለማጥፋት መነሳት ተገቢ አይ*ደ*ለም።
ዘሪሁን ተዝናኑ
ከማይነበብ ፊርማ ጋር !!!
ይህ ጽሁፍ የተወሰደው Zerihun Teznanu ከሚል Facebook
#ፍንትሽበቀለ 💚💛❤
#ኢትዮጵያ ❣️❣️