Dire Midia

Dire Midia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Midia, Digital creator, Addis Ababa, Addis Ababa.

12/09/2025

Jewe

14/07/2025

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ መከላከያ ሀይል (ቲዲኤፍ) በዛሬው እለት ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመርቋል፡፡ ባለፉት ተከታታይ ቀናት ምልምል ወታደሮቹን እያስመረቀ ያለው ቲዲኤፍ በዛሬው እለት ደግሞ በራማ አዲ የአርሚ 42 ኮር 423 አባል የሆኑ በርካታ ኮማንዶዎችን አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የአርሚ 42 ዋና አዛዥ ሌተና ጄኔራል ተስፋዬ አብርሀ(ድንኩል) ‹‹ትግራይ አሁን የሰላምና የቀይ መስመር ምርጫ መሀል ትገኛለች›› ብለዋል፡፡ ተመራቂዎቹ የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን ማሳየታቸውን ከስፍራው የተሰራጩ መረጃዎች ገልፀዋል፡፡
______
በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከዕለቱ ዜናችን ላይ ይመልከቱ | ሊንክ ኮመንት ላይ አለ።

31/05/2025
የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ወ/ሮ አይሻ ለኤርትራው መሪ ይፋዊ ማስጠንቀቂያመከላከያ ሰራዊታችን የተዘጋጀው ቤታችን ላሉ የሌሎችን ምክር እየሰሙ እዚም እዛም ላሉ ለሰፈር  ትናንሽ ቡድኖች ሳይሆ...
31/05/2025

የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ወ/ሮ አይሻ ለኤርትራው መሪ ይፋዊ ማስጠንቀቂያ

መከላከያ ሰራዊታችን የተዘጋጀው ቤታችን ላሉ የሌሎችን ምክር እየሰሙ እዚም እዛም ላሉ ለሰፈር ትናንሽ ቡድኖች ሳይሆን በተሳሳተ ስሌት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ክብር ለሚዳፈሩ ሀገራት ነው ለእነዚህ ትናንሽ የሰፈር ቡድኖች ሚሊሻው በቂ ነው

ኤርትራን ሀገር ነው ብሎ ለመጥራት የማይቻል ህዝቡ በፍርሃት ተሸብቦ ሚኖርበት ተሰዶ ያለቀበትን ሀገር መሪ ነኝ የሚለው (ኢሳያስ) በዚህ ልክ ስለ ኢትዮጵያ ለመናገር መድፈሩ የተለመደ የነሱ ባህሪ ነው።

ሲሉ የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ወይዘሮ አይሻ መሀመድ ተናግረዋል።

በጌታቸዉ ረዳ የሚመራው አዲሱ ዴሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ መመስረቻ ጉባኤውን በዚህ ዓመት በትግራይ ክልል እንደሚያካሄድ ገለጸ 👉 የፓርቲው መሥራች አባል ከሆኑት ውስጥ 100 ያህሉ ከህወሓ...
31/05/2025

በጌታቸዉ ረዳ የሚመራው አዲሱ ዴሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ መመስረቻ ጉባኤውን በዚህ ዓመት በትግራይ ክልል እንደሚያካሄድ ገለጸ

👉 የፓርቲው መሥራች አባል ከሆኑት ውስጥ 100 ያህሉ ከህወሓት የወጡ ናቸው ተብሏል

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው አዲሱ 'ዴሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ'፤ መመስረቻ ጉባኤውን በዚህ ዓመት በትግራይ ክልል እንደሚያካሄድ አስታውቋል፡፡

ፖርቲው ዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የመጀመሪያውን ጋዜጣዊ መግለጫውን በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ያካሄደ ሲሆን፤ በመግለጫውም ግዜያዊ ፍቃድ ከምርጫ ቦርድ ማግኘቱን ገልጿል፡፡

አዲሱ ፖርቲ 'በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ አካሄድ ወደ ተሳሳተ መንገድ በመሄዱና ለውጥ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ በመሆኑ፤ አዲስ እና የተለያየ ሀሳብ ያለው ፖርቲ ለመመስረት እንዳስፈለገ' ገልጿል።

መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ እና የአደራጅ ኮሚቴ አባል አቶ ረዳኢ ኀለፎም፤ የፖርቲው መስራች የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በሕመም ምክንያት መግለጫው መስጠት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ዴሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ 'ክልሉ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ ይገኛል' የሚል ሀሳብ በሁሉም ለውጥ ፈላጊ ላይ በማደሩ ምክንያት እንዲሁም፤ 'ትግራይ አዲስ ለውጥ ያስፈልጋታል' የሚል እምነት በመኖሩ የተፈጠረ አዲስ ፖርቲ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

ማንኛውም 'ሀሳብ አለኝ' የሚል ትግራዋይ የፖርቲውን ደንብና መተዳደሪያ የሚቀበል ከሆነለ ስምረትን መቀላለቀል የሚችል መሆኑንም በመግለጫው ተናግረዋል።

ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ፖርቲው ከክልል እስከ ቀበሌ አደረጃጀቶችን የመመስረት ሥራዎችና የአባላት ምልመላ ሥራዎች እንደሚሰራ የገለጹት አቶ ረዳኢ፤ "ከዚህ ቀደም የህወሓት አባል ሁኖ ለውጥ የሚፈልግ ካለም አባል መሆን ይችላል" ብለዋል።

"ከዚህ ውጪ የህወሓት አባል የሆኑ ወጣቶችን እንዲሁም ከትግራይ ውጪ ያሉ የትግራይ ተወላጆችም የፖርቲው አባል እንዲሆኑ ይሰራል" ሲሉም ገልጸዋል።

አክለውም "በህወሓት ውስጥ ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ አራት ግለሰቦች 'ሠራዊቱን እናዛለን' የሚል ዕምነት እንዳላቸው ስለሚያምኑ፤ ትግራይን ሰላም የነሷት መላው የህወሓት አባላት ሳይሆኑ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ውጪ ያሉና ሕገ-ወጡን ጉባኤ ያካሄዱት ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአሁን ወቅት የፓርቲው መሥራች አባል ከሆኑት ውስጥ 100 ያህሉ ከህወሓት የወጡ መሆናቸውና፤ ከእነዚህ ውስጥም ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት በትግራይ እንደሚነገኙም አቶ ረዳኢ ገልጸዋል፡፡

ፖርቲው በትግራይ የተለያዩ መድረኮች እንደሚካሄዱ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ክረምት ሳይወጣ በትግራይ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚካሄድም በመግለጫው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአቶ ጌታቸው ረዳ ለተመሠረተው አዲሱ የትግራይ ፓርቲ "ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ" (ስምረት) ፓርቲ፤ ጊዜያዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ፈቃድ ባሳለፍነው ሳምንት መስጠቱ ይታወቃል።

(አቤል ደጀኔ - አሐዱ)

Ezaga yisemal kkkkkk
22/05/2025

Ezaga yisemal kkkkkk

በሲዳማ ክልል ዲግሪና ከዚህ በላይ ከመንግሥት ከፍተኛ ተቋማት ተመርቆ ሥራ አጥቶ በየጥላ ስር ወድቆ ተኝቶ የሚውሉ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል።ዘመድ ያለው ሥራ ዕድል የሚያ...
19/05/2025

በሲዳማ ክልል ዲግሪና ከዚህ በላይ ከመንግሥት ከፍተኛ ተቋማት ተመርቆ ሥራ አጥቶ በየጥላ ስር ወድቆ ተኝቶ የሚውሉ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል።ዘመድ ያለው ሥራ ዕድል የሚያገኙበት ዘመን፣ዘመድ የሌላው መግቢያው መውጫው አጥቶ ቀንም ሌሊትም ጨለማ ሆኖ በየመሄዳ ተራግፎ የሚውልበት ክፉ ዘመን ነው።
ቀጣይ የምርጫ ዘመን ብልፅግና ፓርቲ ምርጫውን ተወዳድሮ የማለፍ ሁኔታ ግመል በነርፌ ቀዳዳ እንደሚያልፍ ይሆናል።በተጨማሪ ዳቦ ያጣ ወጣቶች ቀስ በቀስ ሰውን ለመብላት ጭምር ወደኃላ አይሉም።መንግሥት ሰካን ብሎ ራሱን መፈተሽና ማጤን ይገባል።

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ሁለት ግብ አስቆጠረዛሬ የፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች እና የክሮሺያ ከ15 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ባደረጉት ጨዋታ ላይ የክርስቲያኖ ልጅ የሆነው ሮናልዶ ጁኒየር 2...
18/05/2025

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ሁለት ግብ አስቆጠረ

ዛሬ የፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች እና የክሮሺያ ከ15 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ባደረጉት ጨዋታ ላይ የክርስቲያኖ ልጅ የሆነው ሮናልዶ ጁኒየር 2 ግብ ማስቆጠር ችሏል::

ፖርቹጋል ጨዋታውን 3 ለ2 ማሸነፍ ችላለች::

በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ለ50 ዓመታት በመቆየት አንጋፋ የሆነው ህወሓት ለሁለተኛ ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲነት ዕውቅናው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰርዟል።ሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገ...
18/05/2025

በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ለ50 ዓመታት በመቆየት አንጋፋ የሆነው ህወሓት ለሁለተኛ ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲነት ዕውቅናው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰርዟል።

ሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገሪቱ የሥልጣን መንበር ላይ ዋነኛው ኃይል ሆኖ የቆየው ህወሓት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ከተከሰተው ጦርነት ጋር በተያያዘ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሽብር ቡድን ብሎ በመሰየም ሕገወጥ አድርጎት ነበር።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ህወሓት ከሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ወጥቶ በኃይል በተገዘ የአመጻ ተግባር ላይ በመሣተፉ ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ሕጋዊ ሰውነቱን አጥቶ እንዲሰረዝ መወሰኑን አስታውቆ ነበር።

ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በመንግሥት እና በህወሓት መካከል በተካሄደ ድርድር ተቋጭቶ ህወሓት ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲመለስ የሽብር ቡድንነት ፍረጃው ተነስቶለታል።

ነገር ግን ባለፉት ሁለት ዓመታት ህወሓት የነበረን ዕውቅናው በማስመለስ እና እንደ አዲስ በመመዝገብ ጉዳይ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ሲወዛገብ ቆይቶ፤ በልዩ ሁኔታ እንዲመዘገብ የቀረበውን ሃሳብ ባለመቀበል እንዲሁም ማሟላት ያለበትን ሂደት ባለመፈጸም በድጋሚ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ከፓርቲነት ተሰርዟል።

https://bbc.in/4ksCIQ8

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Midia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share