Sisay Mengiste MEDIA.

Sisay Mengiste MEDIA. Sisay Mengiste Media_
(ሲሳይ መንግስቴ ሚዲያ)
በአገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ያተኮሩ መረጃዎች
በየዕለቱ መረጃዎች በማስረጃ ተሟልተው የሚቀርቡበት የሁላችንም የመረጃ ቋት!

የሐቅናማስረጃ መገኛ ቋት

''የሰው ልጅ ድካም፣ የእናት እምባ! የጋዜጠኛ ሶፎንያስ መጨረሻ''በእውነት ልብ ይነካል፣ ያሳዝናል! ቪዲዮውን ስመለከተው ውስጤ እርብሽ ነው ያለው ።እኛ ሰዎች ስንያዝ እንዲህ ነን? አቅም አ...
30/05/2026

''የሰው ልጅ ድካም፣ የእናት እምባ! የጋዜጠኛ ሶፎንያስ መጨረሻ''

በእውነት ልብ ይነካል፣ ያሳዝናል! ቪዲዮውን ስመለከተው ውስጤ እርብሽ ነው ያለው ።እኛ ሰዎች ስንያዝ እንዲህ ነን? አቅም አለን፣ ጉልበት አለን፣ ሁሉን ማድረግ እንችላለን ብለን የምንፎክርበት የጉልበታችን ቀን አልፎ፣ አቅም አጥተን የምንወድቅበት ቀን ግን ሌላ ፍጡር እንሆናለን። ይህ ድክመት የሁላችንም ነው !

እውነቱን ለመነጋገር፣ ከጋዜጠኛ ሶፎንያስ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለቀቁ ፣ ከባህላችንም ሆነ ከሃይማኖታችን ያፈነገጠውን ተግባር በተመለከተ፣ ሁላችንም አዝነናል፣ "ለምን?" ብለን ጠይቀናል፣ ተቆጥተናልም። ምክንያቱም ያ ያየነው ህይወት ፍጹም የሚገባና የማይመጥን ስለነበረ ነው።

ነገር ግን፣ ያ ጊዜ አልፎ ዛሬ ቪዲዮው ላይ እንደምናየው ሌላ እጅግ አሳዛኝ ታሪክ ይዞ መጥቷል። በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በተለይም በፌስቡክ ገጹ ላይ "ከህመሜ ተፈወስኩኝ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ አድርግልኝ" በማለት ሁላችንንም ያስደሰተ መልዕክት አጋርቶ የነበረው ሶፎንያስ፣ ዛሬ በከፋ ፈተና ውስጥ ይገኛል። በተለይ ደግሞ የወላጅ እናቱ ንግግር ልብ የሚሰብር ነው።

ይህቺ ምስኪን እናት ልጇ ባለትዳር ሆኖ፣ የልጅ ልጅ አሳይቷቸው በጥሩ ህይወት ውስጥ ለማየት እንጂ፣ እንዲህ አይነቱ አስከፊ መከራና ፈተና ላይ ይወድቃል ብለው መቼም አልጠበቁም። ሶፎንያስን ብቻዋን፣ በብዙ መከራ፣ ሊስትሮ ጠርጋ እና ፓርኪንግ ሰርታ ለቁም ነገር ያበቃች ጀግና እናት ናት! ዛሬ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ልጇን ከዚህ የከፋ ስቃይና ህመም እንዲታደግላት በሸገር ኢንፎ ቃለ-መጠይቅ ላይ በዕንባ ስትማጸን ትታያለች።

እናትየው በከፍተኛ ሃዘን፦ "እኔ ከልጄ ህይወት መትረፍ በፊት እዛ ቤት አልመለስም፣ ልጄ መጀመሪያ ህክምና አግኝቶ ይዳንልኝ፣ አድኑልኝ!" እያሉ መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ እየለመኑ ነው።

የሚመለከታችሁ የጤና ተቋማት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፤ ይህቺ ምስኪን እናትም ከስጋት ወጥታ፣ የፈሰሰው እምባዋ ታብሶ በሰላም እንድትኖር ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ ።

ፈጣሪ ለወላጅ እናት ብርታትን፣ ለጋዜጠኛ ሶፎንያስ ደግሞ አፋጣኝ ምህረትንና ሙሉ ፈውስን ይላክላቸው! አሜን🙏

በይድነቃቸው ከበደ

"ዮድ አቢሲኒያ በቦሌ ኬኬር ህንፃ"አገልግሎት መስጠት ጀመረ!- ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አላደረግንም።በባህላዊ ምግቦቹ፣ መስተንግዶውና ሃገራችንን በማስተዋወቅ ግምባር ቀደም የሆነው የዮድ አ...
24/05/2026

"ዮድ አቢሲኒያ በቦሌ ኬኬር ህንፃ"አገልግሎት መስጠት ጀመረ!
- ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አላደረግንም።

በባህላዊ ምግቦቹ፣ መስተንግዶውና ሃገራችንን በማስተዋወቅ ግምባር ቀደም የሆነው የዮድ አቢሲኒያ ጀኔራል ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ የቦሌ ቅርንጫፍ በኮሪደር ልማት ምክንያት የቀድሞ ቦታው ቢፈርስም እዚያው አካባቢ ባለ ህንጻ ስር ሰፊና የተንጣለለ አዳራሽ ውስጥ ተጨማሪ አገልግሎት ይዞ መቅረቡ ተናግረዋል።

በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ባስገነባው አዲስ ስፍራ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ሥራ የጀመረው ዮድ አቢሲኒያ ቪአይ ፒ ጨምሮ ሌሎችም የተሻሉ አገልግሎቶችን ለመስጠት ይበልጥ የሚያስችለው ስፍራ ማግኘቱን ነው የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ለመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች የተናገሩት።

ለደንበኞቹ፣ ለአጋሮቹ እና ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ፤ አዲሱ ቅርንጫፍ ቀድሞ ከነበረበት ቦታ 150 ሜትር ርቆ በሚገኝ እና 1200 ካሬ ሜትር ባረፈ ሰፊ ቦታ ላይ መዘጋጀቱን ስፋቱም ከበፊቱ ጋር ሲነጻጸር አሁን አዲስ የጀመረበት እጥፍ እንደሚበልጥ ገልጸዋል።

በአንድ ጊዜ ከ500 እስከ 700 የሚደርሱ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፣ ለግንባታውና ለዝግጅቱ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተጠቅሷል።

በ1996 ዓ.ም የተመሰረተው ዮድ አቢሲኒያ፤ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስ እና ቋንቋ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት የቆየ አንጋፋ ተቋም ነው።

ድርጅቱ በከተማዋ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ቦታውን ለመቀየር ቢገደድም፤ የተለመደውን የኢትዮጵያዊያን የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት፣ የባህላዊ ምግቦች ጣዕም፣ የሙዚቃና የውዝዋዜ ትርኢት ጥራት ሳይቀንስ በተሻለ አደረጃጀት ደንበኞቹን ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

አዲሱ የቦሌ ቅርንጫፍ በባለፈው ቅዳሜና እሁድ ማለትም ግንቦት 15 እና ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ያደረገ ሲሆን ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ያለማድረጉን የስራ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።

ዮድ አቢሲኒያ ከቦሌ በተጨማሪ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ ተጨማሪ ቅርንጫፍ የከፈተ ሲሆን ከሆቴል ባሻገር በጉዞ ወኪልና ልዩ ልዩ አልግሎቶችን እንደሚሰጥ ከተቋሙ የስራ ኃላፊዎች መግለጫ ተረድተናል።

24/05/2026

"ዮድ አቢሲኒያ በቦሌ ኬኬር ህንፃ"አገልግሎት መስጠት ጀመረ!
- ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አላደረግንም።

በባህላዊ ምግቦቹ፣ መስተንግዶውና ሃገራችንን በማስተዋወቅ ግምባር ቀደም የሆነው የዮድ አቢሲኒያ ጀኔራል ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ የቦሌ ቅርንጫፍ በኮሪደር ልማት ምክንያት የቀድሞ ቦታው ቢፈርስም እዚያው አካባቢ ባለ ህንጻ ስር ሰፊና የተንጣለለ አዳራሽ ውስጥ ተጨማሪ አገልግሎት ይዞ መቅረቡ ተናግረዋል።

በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ባስገነባው አዲስ ስፍራ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ሥራ የጀመረው ዮድ አቢሲኒያ ቪአይ ፒ ጨምሮ ሌሎችም የተሻሉ አገልግሎቶችን ለመስጠት ይበልጥ የሚያስችለው ስፍራ ማግኘቱን ነው የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ለመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች የተናገሩት።

ለደንበኞቹ፣ ለአጋሮቹ እና ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ፤ አዲሱ ቅርንጫፍ ቀድሞ ከነበረበት ቦታ 150 ሜትር ርቆ በሚገኝ እና 1200 ካሬ ሜትር ባረፈ ሰፊ ቦታ ላይ መዘጋጀቱን ስፋቱም ከበፊቱ ጋር ሲነጻጸር አሁን አዲስ የጀመረበት እጥፍ እንደሚበልጥ ገልጸዋል።

በአንድ ጊዜ ከ500 እስከ 700 የሚደርሱ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፣ ለግንባታውና ለዝግጅቱ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተጠቅሷል።

በ1996 ዓ.ም የተመሰረተው ዮድ አቢሲኒያ፤ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስ እና ቋንቋ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት የቆየ አንጋፋ ተቋም ነው።

ድርጅቱ በከተማዋ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ቦታውን ለመቀየር ቢገደድም፤ የተለመደውን የኢትዮጵያዊያን የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት፣ የባህላዊ ምግቦች ጣዕም፣ የሙዚቃና የውዝዋዜ ትርኢት ጥራት ሳይቀንስ በተሻለ አደረጃጀት ደንበኞቹን ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

አዲሱ የቦሌ ቅርንጫፍ በባለፈው ቅዳሜና እሁድ ማለትም ግንቦት 15 እና ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ያደረገ ሲሆን ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ያለማድረጉን የስራ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።

ዮድ አቢሲኒያ ከቦሌ በተጨማሪ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ ተጨማሪ ቅርንጫፍ የከፈተ ሲሆን ከሆቴል ባሻገር በጉዞ ወኪልና ልዩ ልዩ አልግሎቶችን እንደሚሰጥ ከተቋሙ የስራ ኃላፊዎች መግለጫ ተረድተናል።

በሴት ልጅ ግርዛትና ጥቃት ላይ የሚያጠነጥነው ''ህዶቴ'' ፊልም የፊታችን ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም (ፓን አፍሪካ አዳራሽ) ሊመረቅ ነው!  በሀገራችን በ...
18/05/2026

በሴት ልጅ ግርዛትና ጥቃት ላይ የሚያጠነጥነው ''ህዶቴ'' ፊልም የፊታችን ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም (ፓን አፍሪካ አዳራሽ) ሊመረቅ ነው!

በሀገራችን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃትና የሴት ልጅ ግርዛት አስከፊነት በእውነተኛ ታሪክ ላይ መስርቶ የሚያሳይ ''ህዶቴ'' የተሰኘ አዲስ ፊልም ሊመረቅ መሆኑ በዛሬዉ እለት(ግንቦት 9/2018 ዓ.ም.)በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

''ህዶቴ'' የወላይትኛ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም “ተስፋነሽ" ማለት እንደሆነ እና ፊልሙ ማህበረሰቡ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቆ እንዲቃወም የማንቂያ ደውል መሆንን ያለመ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።

ለመሥራት አንድ ዓመት የፈጀውና ከ7.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይህ ፊልም፤ 75% ቀረጻው በወላይታ ዞን እንዲሁም 25% በሀዋሳ ከተማ የተከናወነ ሲሆን ፊልሙ ለዓለም አቀፍ ዕይታ እንዲበቃ በእንግሊዘኛና በጀርመንኛ ቋንቋዎች የፅሁፍ ትርጉም (Subtitle) የተደረገለት መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ ታላቅ ስራ ላይ እነ ፅናት ተረፈ፣ ሄኖክ አለማየሁ፣ አማኑኤል የሺወንድ እና ናርዶስ አንትዋ ያሉ ተዋንያንን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ215 በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል።

ፊልሙን ከዚህ ቀደም ''ጀቢና'' እና ''ጋዜጠኛዋ'' የተሰኙ ፊልሞችን ያዘጋጀው ሳሙኤል ተሻገር (የእማዬ ልጅ) የደረሰውና የመራው ሲሆን፤ ታምራት በርሄ ደግሞ በኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲውሰርነት ሰርቶበታል፡፡

ፊልሙ ከአድዋ ሙዚየም ምረቃ በኋላ በዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎችና በሀገር ውስጥ ሲኒማዎች ለእይታ የሚበቃ ሲሆን፤ በአውሮፓ ለማሰራጨትም ከጀርመኑ ''ግሩምበርግ ፊልም'' (Grümberg Film) ኩባንያ ጋር የ3 ዓመት ስምምነት መፈጸሙ ተነግሯል።

የቀለም ፊልም ፕሮዳክሽን ስራ የሆነው ይህ ፊልም፤ የፊታችን ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11ሰአት ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም (ፓን አፍሪካ አዳራሽ) እና በጀርመን ፍራይቡርግ ከተማ በተመሳሳይ ቀን በድምቀት እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

የ15ኛ_ቀን የህፃናት_ስፖንሰርሽ_ገቢ_ማሰባሰቢያ_የማጠናቀቂያ ዝግጅት !ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፣ ከበጎ ፈቃደኛ ሴት ጋዜጠኞች፣ ደራሲያንና ምሁራን ጥምረት ጋር በመሆን "የእኔም ልጆች ናቸዉ" በሚል...
21/03/2026

የ15ኛ_ቀን የህፃናት_ስፖንሰርሽ_ገቢ_ማሰባሰቢያ_የማጠናቀቂያ ዝግጅት !

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፣ ከበጎ ፈቃደኛ ሴት ጋዜጠኞች፣ ደራሲያንና ምሁራን ጥምረት ጋር በመሆን "የእኔም ልጆች ናቸዉ" በሚል መሪ ቃል ልዩ የቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዛሬ መጋቢት 12/2018 ዓ.ም.ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ልዩ ልዩ እንግዶች በተገኙበት ቀጥታ በአባይ ቲቪ የዩትዩብ ቻናል የመጨረሻው የመዝጊያ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳል።

የታሪካዊው ምሽት ታሪካዊ እንግዶች
👉ወ/ሮ አየሁ ከበደ
የአንጋፋው አርቲስት የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ባለቤት ስለ ተማር ልጄ... ሙዚቃ አስገራሚ ነገሮች ታጫዉተናለች

👉ዶክተር ሞገስ ግርማ

ጌጅ ሰርቪስ ትሬዲንግ ሐውስ ፒኤልሲ ባለቤት
ከተቋማቶቹ መካከል
ጌጅ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣
ሶፍትኔት የሥልጠና ማዕከል፣ ኤል ኤም ኢንተርናሽናል ሆቴል ስኩል፣ ግሬስ ኮሌጅ፣
ጌጅ አካዳሚ እና የሌሎች እህት ካምፓኒዎች ባለቤትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲሆነኑ ከመምህርነት ከመምህርነት በመነሳት ዛሬ የደረሱበትን የአርዓያነት መንገድ
የህይወት ተሞክሮ ያስቃኘናል።

👉አቶ ዳንኤል በቀለ

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ አማ ከትናንት እስከ ዛሬ ያሉ ሂደቱንያጫዉተናል።ስለወደፊቱ ስትራቴጂዎች ያጫዉተናል።

👉አቶ ተስፋዬ ጋሻዉ

የብላክ ዳይመንድ አድቨርታይዚንግ እና የተለያዩ እህት ካምፓኒዎችን በመመስረትና ለስኬት የበቃበትን ሂደት ያካፍለናል።

👉አቶ ዳዊት ደረጀ
የሳኦል የሁነቶች አዘጋጅ ስለስራዎች ስለተሞክሮዉ ያካፍለናል።
👉ግራንድ ማስተር ሄኖክ ግርማ
የሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ግሩፕ እና በትዉልድ እየሰራዉ ያለዉን ግሩም ተሞክሮ እንዲሁም የማርሻል አርት የአሸናፊነት ምስጢራትን ያመላክተናል።

👉ድምፃዊ ጥላሁን አባተ

'ሰሰ በል' በተሰኘና በተለያዩ የባህል ዘመናዊ ሙዚቃዎች የሚታወቅ ሲሆን በእለቱም
ስለታዳጊዎች ስለልጅ ስለትዉልድ ስለትምርህትና ስለእዉቀት ጥበባዊ ትሩፋቶችን ተማር ልጄ ሀሁ ፊደል ማንበብና መፃፍ..የመሳሰሉ
ሙዚቃዎችን በድምፅ በማቅረብ ያዝናናል።

👉ወጣት ሰሎሞን ዓለሙና ቅድስት ዝና
እኔም ለትዉልድ ለልጆች አለን በማለት አብረዉን ያመሻሉ።

👉ጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ ላለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን እንዲሁም በሁነት አስተባባሪነት በመስራት ላይ የሚገኝ አሁንም በመስራት ላይ ያለ አንጋፋና ወጣት የሚዲያ ባለሙያ ነዉ።ጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ ከሌሎች ጋዜጠኞችና እንግዶች ጋር በመገኘት ሸጋ የሆነ ለትዉልድ ተሻጋሪ ፕሮግራም ይዞ በማቅረብ አሻራውን ያሳርፋል።

ላለፉት 15 ቀናት የዘለቀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር በአባይ ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል የቀጥታ ስርጭት ከምሽቱ 12:ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ይጠናቀቃል።

ዛሬ መጋቢት 12/2018 ዓ.ም.
ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ
በአባይ ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል የቀጥታ ስርጭት

https://www.youtube.com/live/u2InMgxug9w?si=RBm5H20guFCz_fQf
በዚህ ሊንክ LIVE ይከታተሉን

አብረዉን ይዝለቁ!!!
እናመሰግናለን!!!

እልል እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ታሪክ ተሠራ 136,000,000.00! በመጀመሪያው ቀን ብቻ ከአንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ሚሊዬን ብር በላይ ተሰበሰበ!አርብ ከምሽት 1፡00 ጀምሮየዓለም ዐይኖ...
21/03/2026

እልል እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ታሪክ ተሠራ 136,000,000.00!

በመጀመሪያው ቀን ብቻ ከአንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ሚሊዬን ብር በላይ ተሰበሰበ!

አርብ ከምሽት 1፡00 ጀምሮ
የዓለም ዐይኖች ሁሉ እንጦጦ ኪዳነምሕረት ላይ ነበሩ። የገዳሟ ወዳጆች ከአራቱም ማዕዘን ሌሊቱን ተረባረቡ። በቤተክርስቲያን የገቢ ማሰባሰቢያ ታሪክ በአንድ ቀን ሌሊት የመጀመሪያ የተባለው ሪከርድ ተይዟል። በዚህም የገዳሟ አበመኔት እና መነኮሳት ያመሰግኗችኋል።

ለአገልጋይ፣ ለሠራተኛ ዋጋ እና ክፍያ እንደሚገባ መጽሐፍ የሚያዘውና የታወቀ ቢሆንም ለእንጦጦ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም ግን ማስታወቂያውን፣ ዶክመንተሪውን እና ቀጥታ ሥርጭቱን በነፃ የሠሩት ዩቱበሮች፣ ቲክታከሮች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ይኽንን መርሐ ግብር በዚህ መልኩ እንዲሳካ ከኮሚቴው ጋር በሠተባበር ሳይንሳዊ እና መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ኹነቱነን በነፃ ያስተባበረው ሎዛ ኹነቶች -Loza Events ከገዳሙ የእመቤታችን ሥዕለ አድኅኖ እና የምስክር ወረቀት በሥጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰቡ ዛሬ ቅዳሜ 12/07/18 እና ነገ እሑድም 13/07/18 ይቀጥላል።

በቀጥታ ሥርጭቱ ላይ የምትደውሉባቸው ስልኮች
09 11 19 05 03
09 11 59 26 05
0911 44 61 44
09 57 66 39 39

ገዳሟን የምታግዙባቸው አካውንቶች
ንግድ ባንክ1000003780779
አባይ ባንክ 9841011002322017
አሐዱ ባንከ 0088911720301

https://gofund.me/401f3b995

ማሳሰቢያ
በአካውንት ቁጥሮች እያስገባችሁ
በስልኮቹ በዋትስአፕ እና በቴሌግራም ደረሰኙን ላኩልን።

እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰዳለሁ🙏ሚካኤል ማለት “ከመ እግዚአብሔር” እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?” ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚ...
21/03/2026

እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰዳለሁ🙏

ሚካኤል ማለት “ከመ እግዚአብሔር” እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?” ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው? መልሱ የለም ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነትና ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ፣ ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡

መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔርም ነግሮናል፡፡ በዘጸ.23÷20-22 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል” በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለሙሴና ለሕዝቡ ብቻ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን እስከዛሬና ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡

መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት፣ እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ የሚለው በመላእክት ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር የተሾመ ማለት ነው፡፡ መላእክት አለቆቻቸውን ያከብራሉ፤ ለእነሱም ይታዘዛሉ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት ሁሉ አለቃ ስለሆነ ከትእዛዙ አይወጡም፤ ሠራዊተ መላእክት የሚያከብሩትንና የሚታዘዙለትን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እኛም እንደ እነርሱ እናከብረዋለን እንታዘዘዋለን፡፡ቅዱስ ሚካኤል አንተዉ ጠብቀን!!!

የድምፃዊ ብስራት አለማየሁ"ደስታ ለኔ"አዲስ አልበም ለገበያ ሊቀርብ ነው👉የጥንት የጠዋቱ አምባሰል ሙዚቃ ቤት ከዓመታት በኋላ ከወጣት የሙዚቃ ባለሙዎች ጋር በመስራት በአዲስ አደረጃጀት መጥቷል...
26/02/2026

የድምፃዊ ብስራት አለማየሁ"ደስታ ለኔ"አዲስ አልበም ለገበያ ሊቀርብ ነው

👉የጥንት የጠዋቱ አምባሰል ሙዚቃ ቤት ከዓመታት በኋላ ከወጣት የሙዚቃ ባለሙዎች ጋር በመስራት በአዲስ አደረጃጀት መጥቷል።

በኤንቢሲ ኢትዮጵያ ታለንት ሾው ተሸላሚዉና በባላገሩ አይዶል ፈርጥና'እደግ ተመንደግ'የተባለዉ ባለተሰጥኦ ወጣት ድምፃዊ ብስራት አለማየሁ የበኩር አልበሙን"ደስታ ለኔ"በሚል መጠሪያ በአምባሰል የዩቲዩብ ቻናል በዚህ ሳምንት ለህዝብ ሊያደርስ እንደሆነ ተነገረ።

የአንጋፋዎቹን የነጥላሁን ገሰሰን አለማየሁ እሸቴን የምኒሊክ ወስናቸዉን የሙሉቀን መለሰና የቴዎድሮስ ታደሰንና የሌሎች የወጣት ድምፃዊያንን ሙዚቃዎች በተለያዩ መድረኮች እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት ሲዘፍን ባለተሰጥኦነቱን አይተዉ አድናቆታቸዉን የለገሱት የተስረቅራቂ ድምፅና ቅላፄ ባለፀጋ የሆነዉ ድምፃዊ ብስራት አለማየሁ "ደስታ ለኔ" የተሰኘ አልበሙን በስቱዲዮ ቅንብር በቀጥታ መድረክ በምስልና በግጥም ፁሁፍ ዲዛይን አዋህዶ በዘመናዊ የአዘፋፈን ዘዬ የተዘጋጀ በአምባሰል ሪከርድስና በአምባሰል የዩቲዩብ ቻናል በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ለህዝብ እንደሚያደርስ ተናግሯል።

🎼10ትራኮችን የያዘዉ ደስታ ለኔ አዲስ አልበም በማህበራዊ በፍቅር በሀገራዊ በአንድነትና በመከባበር ዙሪያ ያተኮሩ ሀሳቦችንና ጭብጦች ላይ በማተኮር የተዘጋጀ ሲሆን በተሐይም በግጥምና በዜማ ከሽኖ በጆሮ ገብ ድምፅ በማይጎረብጥ ቅላፄ መዘጋጀታቸዉ ተብራርቷል።
የወጣቱ ድምፃዊ ብስራት አለማየሁ "ደስታ ለኔ"የመጀመሪያ አልበምበሙዚቃ ቅንብር
እዮብ ባልቻ፤ማቲ ማን፤
ሳሚ ዮባል በተለያዩ ስቱዲዮዎች ሲያቀናብሩት
የቀጥታ የሙዚቃ መሳሪያ
ፍራኦልተመስገን(ሳክስፎን)
ዮናስ ለማ(ሊድ ጊታር)
ፍሬህይወት ቴዎድሮስ(ሊድ ጊታር)ሳሚ ዮባል (ሳክስፎን) በመጫወት አሳምረዉታል።
☑️በግጥምና ዜማ ኤፍሬም አበበ(ከፍ ከፍ)፤
መስፍን ከበደ፤ዜና ታደሰ እንዲሁም ድምፃዊዉ ብስራት አለማየሁ የደረሱት ሲሆንበሚክሲንግና ማስተሪንግ ተድላ ማንያህልሃል(Big t) ጥበባዊ አሻራቸዉን አስቀምጠዋል።
ፕሮዲዩሰር ዮናታን ዘካሪያስ
ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር ኤፍሬም አበበ(ከፍ ከፍ) የቀረበዉ ደስታ ለኔ አልበም
በቤቴልሄም ጠቅል ግራፊክስዲዛይንበይድነቃቸው ፈከነ(አድርያኖ) ፕሮዳክሽን ማኔጀርነት እንደሆኑና ሁሉም በደስታ ለኔ አልበም የሚቻላቸዉን እንዳበረከቱ ወጣቱ ድምፃዊ ብስራት አለማየሁጠቁሟል።ከልጅነቱ ጀምሮ በብስራተ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት በዝማሬ በማገልገልና በማደግባለተስረቅራቂ ድምፅ ባለቤት ለመሆን የቻለዉ ድምፃዊ ብስራት አለማየሁ 10 የተመረጡ ሙዚቃዎች "ደስታ ለኔ" አልበም በአምባሰል የዩቲዩብ ቻናል በያዝነዉ ሳምንት መጨረሻ እንደሚለቀቅ ተነግሯል።

አምባሰል _የጥንት የጠዋቱ

👉ላለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያ የሙዚቃና የጥበብ ኢንዱስትሪ ደማቅ አሻራ ማስቀመጥ የቻለዉ አንጋፋው አምባሰል ሙዚቃ ቤት በአምባሰል ሪከርድስና በአምባሰል ቲዩብ ተመልሶ በአዲስ አደረጃጀት የመጣሲሆን"ደስታ ለኔ "አልበምምበአምባሰል ዩቲዩብ ቻናል ደስታን ለራስዎ ያገኙበታል።

👉አዳዲስ እና ዘመን ተሻጋሪ አልበሞችን ለማግኘትና ሌሎች የአምባሰል ሪከርድስን የግማሽ ክፍለዘመን ጥበባዊ ስራዎችን ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት Ambassel tube

https://youtube.com/?si=6Njeqmte4lCnB7Nm

ይጎብኙ።

አምባሰል
የጥንት የጠዋቱ!!!

  ነገ በአራዳ ፓርክ ይካሄዳል !ነገ እሁድ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀመረው "ብስክሌት በአዲስ" ወርኃዊ ፌስቲቫል እንዳያመልጥዎ !​ሳይክል ፌስቲቫል ፦      📅 ቀን ፦ ነገ እሁድ...
07/02/2026

ነገ በአራዳ ፓርክ ይካሄዳል !

ነገ እሁድ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀመረው "ብስክሌት በአዲስ" ወርኃዊ ፌስቲቫል እንዳያመልጥዎ !

​ሳይክል ፌስቲቫል ፦
📅 ቀን ፦ ነገ እሁድ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት ፦ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 5:00
📍 ቦታ ፦ ፒያሳ አራዳ ፓርክ



ሳይክል ፌስቲቫል ለህጻናት እና ለቤተሰብ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመዝናኛ አማራጭ ነው።

​ብስክሌት የለኝም ብለው አይጨነቁ። ለእርሶ ያዘጋጀናቸው ብስክሌቶች አሉ።
Henok Adane

የመታሰቢያ ጥሪ፡ ለአርቲስት ነፃነት ወርቅነህበቅርቡ በሞት የተለየን ድንቅ የጥበብ ሰው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ተወልዶ ባደገበትና የልጅነት ትዝታዎቹ ባሉበት በደብረ ፅጌ ቅዱሥ ዑራኤል ቤተ...
22/01/2026

የመታሰቢያ ጥሪ፡

ለአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ

በቅርቡ በሞት የተለየን ድንቅ የጥበብ ሰው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ተወልዶ ባደገበትና የልጅነት ትዝታዎቹ ባሉበት በደብረ ፅጌ ቅዱሥ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ታላቅ የመታሰቢያ እና የጸሎት መርሐ-ግብር ተሰናድቷል።

የአካባቢው ወጣቶች በጋራ ባዘጋጁት በዚህ መንፈሳዊ መድረክ ላይ፤ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት የሚከናወን ሲሆን ብፁሃን አባቶች፣ መምህራነ ወንጌል፣ ዘማሪያን እንዲሁም የስራ ባልደረቦቹና ቤተሰቦቹ ይታደማሉ።

የአርቲስቱ አድናቂዎች፣ የጥበብ ቤተሰቦችና ወዳጆች ሁሉ በዚህ የክብር መርሐ-ግብር ላይ በመገኘት አብራችሁን እንድትሆኑ የዑራኤል አካባቢ ወጣቶች ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።

መርሐ-ግብሩ የሚከናወንበት፦
* ነገ ቀን፦ አርብ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም
* ሰዓት፦ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ
* ቦታ፦ ደብረ ፅጌ ቅዱሥ ዑራኤል ቤተክርስቲያን (ዑራኤል)

ለወንድማችን ነፃነት ወርቅነህ የዘላለም እረፍትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር!

ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት መረጃውን ያድርሱ።

Via የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል አካባቢ ወጣቶች መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ነን።

Address

Nifas Silik
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sisay Mengiste MEDIA. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share