
14/11/2024
ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር የተመሰረተበትን 30ኛ አመት በስካይ ላይት ሆቴል እያከበረ ይገኛል
በፕሮግራሙ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ :የአካል ጉዳተኛ ማህበራት አመራሮች :የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ወላጆች:የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች እንዲሁም በጎ ፈቃደኞች ተገኝተዋል ።
የፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ እንዳሉት ስኬቶቻችንን ስናከብር ብዙ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉም እንገነዘባለን። በየቤቱ በሰንሰለት የታሰሩ የፀሀይ ብርሃን የሚናፍቁ ወገኖቻችንን በልባችን ይዘን፤ ይህ በዓል ጥረቶቻችንና ተልእኳችን እንደሚቀጥል ለማስታወስ ይሁን።
የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችንና ቤተሰቦቻቸውን መብት፣ ብቃት፣ ሙሉ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለመደገፍ ቁርጠኞች ነን። በጋራ ጥንካሬያችን፣ ገደቦችንና እንቅፋቶችን መግፋታችንን እንቀጥላለን በዚህም ለሁሉም ብሩህ፣ እኩልና አካታች ዓለም ወደፊት እንፈጥራለn