Gurage limat

Gurage limat የጉራጌ ስነ ልቦና ይኑርህ

10/06/2026

ፍርድ የታወረ ቀን ሕግ ይደናበራል
መግደል አስከብሮ መሞት ያሳስራል
በገዳዮች ዛቻ የደመቀው ዓለም
ሲያጠፋ ይውላል እየዋለ የሟቾችን ቀለም።
ሚዛኑ ሲጎድል ሕግ ደም ሲጠጣ
ሟች ተከሰሰና ገዳይ ነጻ ወጣ

22/05/2026

ለፋይዳ - ሲባል አካውንት መዝጋት?!

እስቲ አስቡት!.. እንደእኔ ከልደታ - ቂርቆስ (ከ1 - 15) የማታደርስ፤ ከእጅ ወደአፍ ደመወዙን ባንክ አስቀምጦ ለሽሮና በርበሬ አስቤዛ ጭምር የሚመነዝር ሰው በድንገት ውሃ በማያነሳ ምክንያት አካውንቱ ሲዘጋ ምን ይባላል?

የፋይዳ ቁጥርን ከባንክ ጋር ማስተሳሰር የሚኖረውን ፋይዳ ጊዜ ሰጥቶ ማስተማር፣ ኀ/ሰቡ ይጠቅመኛል እንዲል ማድረግ እንጂ እንደሰፈር ጎረምሳ "ካላያያዝክ እቀጠሃለሁ" ብሎ መነሳት በምንም መመዘኛ ትክክል ነው ሊባል አይችልም። በዚህ ላይ ባንኮች ይኸን ብቻ ምክንያት አድርጎ አካውንት ማገድ የሚያስችል የሕግ መሰረት አላቸው ወይ የሚለው ጥያቄም ፈጣን መልስን የሚሻ ነው።

በግል የእኔን ለየት የሚያደርገው ባንክ ድረስ ሄጄ አያይዙልኝ ብዬ "ተከናውኗል" ከተባልኩ በኋላ የተከሰተ መሆኑ ነው። እርግጥ ነው፤ የባንክ ባለሙያውም ቴክኖሎጂው አዲስ ስለሆነ መሳሳት ሊያጋጥም የሚችል ነው።

በዚያም ተባለ በዚህ "ፋይዳ ቁጥርን አላያያዝክም" በሚል ምክንያት አካውንት ማገድ እጅግ ሲበዛ ጡር ነው። ደንበኛንም ምን ያመጣል ብሎ መናቅ ነው። አለፍ ሲልም ሕዝብ በመንግስት አሰራር ላይ እንዲያመር መግፋት ነው።

በአጭሩ አዛዡ ብሔራዊ ባንክም ይሁን ታዛዦቹ ባንኮች ያስነሳችሁትን አቧሯ አረጋጉት። ይኸው ነው!!
(ፍሬው አበበ)

Address

Kolfe
Addis Ababa

Telephone

+251910999188

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage limat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gurage limat:

Shortcuts

Share