Gordena Online

Gordena Online # a media that provides news and information about the culture and history of societies .

 # እጅግ የሚደነቅ ውሳኔ !****> የጉራጌ ዞን የአስተዳደር ምክር ቤት ጉራጊኛ የዞኑ የስራ ቋንቋ እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል ።
29/07/2025

# እጅግ የሚደነቅ ውሳኔ !
****
> የጉራጌ ዞን የአስተዳደር ምክር ቤት ጉራጊኛ የዞኑ የስራ ቋንቋ እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል ።

27/07/2025

< < ወልቂጤ>>
⭐️⭐️⭐️
# ግጥም የጉራጌ መዲና ስለሆነቺው ወልቂጤ ከተማ !
😘😘😘
# ግጥሙ ስለወደድነው አጋራናቹ !

< ጎርደናዎች ነን >

27/07/2025

# አለም ብሬ ነይ ነየ !
🧡🧡🧡
# የጋሽ አርጋው በዳሶ ልጅ ግዛቸው አርጋው አንድ መድረክ ላይ ከድሞጻዊት ፍቅራዲስ ጋር የተጫወተው !!

🤔🤔🤔
የአንጋፋው አርቲስት አርጋው በዳሶ ልጅ

 # የረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ የነበረው የአልምገና ቡታጅራ የመንገድ ግንባታ በይፋ መጀመሩ ታውቋል ።+++ዶ/ር እንደሻው ጣሰው ዳግማዊ ጀነራል ይልማ ሺበሺ ብለናቸዋል ፥ በእርሳቸው የስልጣን...
25/07/2025

# የረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ የነበረው የአልምገና ቡታጅራ የመንገድ ግንባታ በይፋ መጀመሩ ታውቋል ።
+++
ዶ/ር እንደሻው ጣሰው ዳግማዊ ጀነራል ይልማ ሺበሺ ብለናቸዋል ፥ በእርሳቸው የስልጣን ዘመን በርካታ የሀዝብ ጥያቄዎቸ በየደረጃው እንደሚፈቱ ባለ ሙሉ ተስፈኞች ነን ።
🤔🤔🤔
ጎርደናዎች ነን

23/07/2025

# ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚዲያ ቋንቋ እየሆነ የመጣው ጉራጊኛ !
💡💡💡
🔶🔶🔶

 # ከጉራጌ ልማት ማህበር (ጉልባማ ) ለአንጋፋው ድምፃዊ ጋሽ አርጋው በዳሶ በጉራጌ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋፆ የክብር ማስታወሻ የምስክር ወረቀት ለቤተሰቦቻቸው አበርክቷል...
22/07/2025

# ከጉራጌ ልማት ማህበር (ጉልባማ ) ለአንጋፋው ድምፃዊ ጋሽ አርጋው በዳሶ በጉራጌ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋፆ የክብር ማስታወሻ የምስክር ወረቀት ለቤተሰቦቻቸው አበርክቷል ::
===
# ይህ እጅግ የሚበረታታና ለአንጋፋው አርቲስት ጋሸ አርጋው በዳሶ አንድ ትውልድ ተሻጋሪ የማስታወሻ ሀውልት ሊሰራላቸው ይገባል እንላለን ::
⛱⛱⛱
# ጎርደናዎች ነን !!
❤❤❤

16/07/2025

# ጉራጊኛን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዲያ ቋንቋ አንዲሆን ያድርገው obn horn of africa ነው ። ይህ ብቻ ሳይሆን እንዴት ጉራጊኛን አንድ ላይ አጣምሮ አነዴት ሚዲያ ላይ ማስኬድ እንድሚቻል ያየንበት ሚዲያ ነው ። obn አልማመስገን ንፉግንት ነው።
---
# የኦቢኤን ጉራጊኛ ጋዜጠኞቻችን ልናብረታታቸው ይገባል ።
በዚህ እጋጣሚ ጋዜጠኛ አሻግሬ ኮርማ የሚገርም የቋንቋ ችሎታ ስላየንብት በርታ ልንለው ወደድን ።

ክስታኔ ባንድ !💖💖💖ታዋቂ አርቲስቶች እንደነ ቴዲ አፍሮ : አብነት አጎናፈር: ጎሳዬ ተስፋዬ : ፀጋዬ ሲሜ እንዲሁም ሌሎችም የነበሩበት የጥንቱ የባህል ኪነት ባንድ !====ከድጻዊ ቴዲ አፍሮ...
14/07/2025

ክስታኔ ባንድ !
💖💖💖
ታዋቂ አርቲስቶች እንደነ ቴዲ አፍሮ : አብነት አጎናፈር: ጎሳዬ ተስፋዬ : ፀጋዬ ሲሜ እንዲሁም ሌሎችም የነበሩበት የጥንቱ የባህል ኪነት ባንድ !
====
ከድጻዊ ቴዲ አፍሮ አንድ ጉራጊኛ ነጠላ ዜማ እንፈልጋለን !
💓💓💓
በዚህ አጋጣሚ መልካም ልደት ለንጉሱ 49th yr

~ ከክስታኔ ባንድ አባላት ማንን ታስታውሳላችሁ ?
💗💗💗

 # የሚደነቅ የመሪነት ሚና !          ⏳⏳⏳
14/07/2025

# የሚደነቅ የመሪነት ሚና !
⏳⏳⏳

06/07/2025

ዬቦላላ !
🥰🥰🥰
የክስቶ እሚት !

✍️ቡኢ ከተማና የስሟ ትርጓሜ ..‼    -------------------------------------------👉ቡኢ የሚለው ስያሜ እንዴት ሊሰጣት ቻለ.?👉የስሟ ትክክለኛውስ ትርጓሜ ምንድነው ...
30/06/2025

✍️ቡኢ ከተማና የስሟ ትርጓሜ ..‼
-------------------------------------------
👉ቡኢ የሚለው ስያሜ እንዴት ሊሰጣት ቻለ.?
👉የስሟ ትክክለኛውስ ትርጓሜ ምንድነው ..?
🎯ነገሩ እንዲህ ነው በ1940 ዎቹ ላይ የሶዶ ክስታኔ ክፍለ ህዝብ መንግስታዊ አስተዳደር መቀመጫ ገሬኖ /አማውቴ ላይ ነበር ።
፦በወቅቱ አሁን ቡኢ ብለን የምንጠራት ከተማ የነጋዴዎች መተላለፊያ ነበረች ነጋዴዎቹም በስተ ደቡብ ኬላ - ዳሎቻ- በወቅቱ አጠራር ሲዳሞ ክፍለ ሃገር _ወላይታ ሶዶ -ሃገረ ማርያም ና ያቤሎ ድረስ በስተሰሜን አዲስ አበባ ድረስ በስተምዕራብ ጨቦና ጉራጌ አውራጃ ድረስ በስተምስራቅ መቂ (ዱቢሳ )ድረስ የንግድ መስመር ዘርግተው የሚተላለፉባት ሲሻቸው በእግር ሲያሻቸው በፈረስ ና በቅሎ እየተዘዋወሩባት ንግዱን የሚያሳልጡባት መንገዳቸው ነበረች
👉በሗላ ላይ ግን አሁን ቡኢ ብለን በምንጠራት ከተማ ላይ በወቅቱ አጠራር "አርጉ መቀል " የተባለ መንደር ውስጥ ሽፍቶች ተደራጅተው ነጋዴውን መዝረፍ ና መግደል ማሰቃየት ይጀምራሉ ይሄም የንግዱን ስረዓት ክፉኛ ጎዳው !!
👉በሗላ ላይ ይሄ የንግድ መስመር መሰበር በኢኮኖሚ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጫና በመረዳት ፊታውራሪ ሩጋ አሻሚ (የመርከቶው ነፃ አውጪ ) ለአውራጃ አስተዳዳሪዎች ምክረ ሃሳብ ያቀርባሉ ምክረ ሃሳቡም እንዲህ የሚል ነበረ "መንግስታዊ ተቋማትን ከአማውቴ /ገሬኖ አውርደን ሽፍቶች አሉበት በተባለው አካባቢ ብናቋቁም ና በቂ ነፍጠኛ ፖሊስ ( የታጠቀ የፀጥታ ሃይል ) ብናሰማራ የሽፍቶቹን እንቅስቃሴ በመግታት ወደ ደማቁ የንግድ ስረዓት እንመለሳለን " የሚል ምክረ ሃሳብ ቀርቦ በወቅቱ በነበሩ ሹማምንት ፀደቀ ከዛም በኢትዮጲያዊያን አቆጣጠር በ1944 ዓ/ም ከተራራማው ገሬኖ /አማውቴ ወደ ታችኛው በዝቅተኛ ስፍራ ወደ ተመሰረተችው ቡኢ የሶዶ ክስታኔ ክፍለ ህዝብ መንግስታዊ ስረአቱ ወረደ
👉አቶ ደምሴ አወቀም የመጀመሪያው ሊቀመንበር (አስተዳዳሪ ) ሆነው ህዝቡን እንዲመሩ ተሾሙ ።
👉በወቅቱ ከተለያየ የኦሮሚያ አካባቢ ጉዳይ ለማስፈፀም ወይም ለተለያየ አገልግሎት ወደገሬኖ /አማውቴ መጥተው መንግስት ተቋማትን ፈልገው ሲያጡ "እገሌ የሚባለው ተቋምስ ብለው በኦሮሚፋ ሲጠይቁ በአካባቢው መንግስት ተቋማት ከዳገት ወደዝቅተኛው ስፍራ መቀየሩን ለማመልከት ቡኢ (ውረድ ) እዛ ታገኛቸዋለህ እያለ ይጠቁም ነበር ።
👉ይሃን መነሻ በማድረግ :- ቡኢ የሚል ስያሜ ተሰጣት ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ቡኢ ተብላ ተጠራች ‼
🥇🥇እና የሁላችን ከተማ የሆነችው ቡኢ የትናንት ምስረታዋ ና ስያሜዋ ይሄን ይመስላል 🎯🎯🎯
🙏🙏ምስጋና 🙏🙏🙏
👉ይሄን የታሪክ ሰነድ ስሰንድ ለተባበሩኝ
(*ቀኝ አዝማች ጫካ አሰፋ አለቃ ብርሃኑ ዋካ ጋሽ እንዳልካቸው እሸቴ ና ሌሎችም አባቶቻችንን ከልብ አመሰግናለሁ እድሜና ጤና ይስጥልኝ ,,🙏🙏 )
-----
በፊታውራሪ እንዳሻው አለማየሁ !!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gordena Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gordena Online:

Share