SDL

SDL SDL- Strives to provide you truthfull information.

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!
26/09/2024

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!

26/04/2024

We have the power, the energy and the perfect reasons to win life!!

ጥምቀት 2016 ዓ.ም መልካም በዓል!!
21/01/2024

ጥምቀት 2016 ዓ.ም
መልካም በዓል!!

የህፃናት መራመጃ ጋሪ (ጂሬሎ) ለልጆች ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ?ብዙ ወላጆች ላይ ከሚፈጠሩ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የህፃናት መራመጃ ጋሪ (ጂሬሎ) ለልጆች ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ የሚለው ነው። ታ...
24/12/2023

የህፃናት መራመጃ ጋሪ (ጂሬሎ) ለልጆች ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ?

ብዙ ወላጆች ላይ ከሚፈጠሩ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የህፃናት መራመጃ ጋሪ (ጂሬሎ) ለልጆች ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ የሚለው ነው። ታዲያ ለዚሁ ጥያቄ መልስ ምን እንደሆነ አብረን እናያለን።

በተለያዩ ሆስፒታሎች የህፃናት መራመጃ ጋሪ በሚጠቀሙ እና በማይጠቀሙ ህፃናት ላይ የተደረገው ጥናት ይህንን ውጤት አስቀምጧል

የህፃናት መራመጃ ጋሪ ጥቅሞቹ
1. ህፃናት መቆምና መራመድ እንዴት እንደሆነ ያውቃሉ
2. ያለማንም እርዳታ እንደልባቸው በመዟዟር ይጫወታሉ
3. ከጎናቸው ወላጆች በነፃነት ሌላ ስራን ማከናወን ይችላሉ
4. ጋሪው የተለያዩ ማጫወቻዎች ስላሉት ልጆችን ያዝናናል

የህፃናት መራመጃ ጋሪ ጉዳቶቹ
1. አብዛኛውን ጊዜ ከሚጠበቅባቸው ፍጥነት በላይ ስለሚሄዱ ለተለያዩ አደጋዎች ይጋለጣሉ። ለምሳሌ
- ከተጋጩ ጭንቅላታቸው ላይ እቃ ሊወድቅባቸው እና ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል
- የምግብ ማብሰያ እሳት ጋር ሊደርሱና የቃጠሎ አደጋ ወይም ትኩስ የሆነ ነገር ሊደፋባቸው ይችላል
- በቀላሉ ባእድ የሆኑ ነገሮችን ስለሚያገኙ እና በመብላት ለትንታ ወይም ለመታነቅ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ
- ከደረጃ ላይ በመገልበጥ ወይም በራሳቸው ሲጫወቱ በመገልበጥ የጭንቅላት እና የአንገት እስከሞት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል።
2. በራሳቸው ጊዜ እና ጥረት ለመገላበጥ ለመቀመጥ ለመዳህ ለመቆም እንዲሁም ለመራመድ የሚጠቅሟቸውን ጡንቻዎች እንዲዳከሙ በማድረግ የእንቅስቃሴ እድገታቸውን ያዘገየዋል
3. ጋሪ ውስጥ ሆነው ሲራመዱ እግራቸውን ማየት ስለማይችሉ የአይን እይታ እና እርምጃ ጥምረትን ያዛባል
4. የወገብ እና ጉልበት መገጣጠሚያዎችን የሰውነት ክብደት የመሸከም ብቃትን ይቀንሳል
5. ራሳቸውን ችለው ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዳይቆሙ እና እንዳይራመዱ ያሰንፋቸዋል
6. የጀርባ አከርካሪ አጥነታቸው ላይ ሚዛኑን ያልጠበቀ ጫና ስለሚፈጥር ካደጉ በኋላ ለወገብ ለህመም ሊያጋልጣቸው ይችላል

ስለዚህ በአጠቃላይ በተደረገው ጥናት መሰረት ውጤቱ የሚያሳየው የህፃናት መራመጃ ጋሪ (ጂሬሎ) ጥቅሞቹ እንዳሉ ሆነው ጉዳቶቹ ግን ያመዝናሉ ማለት ነው።

ዶ/ር ዮናታን ከተማ: በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሀኪም።

በፓኔሲያ ሆስፒታል ከአንድ የ40 አመት እድሜ ካላቸው 2094 የሃሞት ጠጠር በቀዶ ህክምና ሊወገድ ችሏል። ይህንን ያክል ቁጥር ያለው ከፍተኛ ቁጥር ያለው  የሃሞት ጠጠር በህክምና እንደ ሃገር...
24/12/2023

በፓኔሲያ ሆስፒታል ከአንድ የ40 አመት እድሜ ካላቸው 2094 የሃሞት ጠጠር በቀዶ ህክምና ሊወገድ ችሏል። ይህንን ያክል ቁጥር ያለው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሃሞት ጠጠር በህክምና እንደ ሃገር ተወግዶ አያውቅም።

በቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር Tsegaye Chebo እና የቀዶ ህክምና ቡድን ግን ይህ ተችሏል።

ADEEROO, RABBI JANNATAAN HAA QANANIISU😭የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ (አዴሮ) 1ኛ ዓመት የሙት መታሰቢያ ቀን በድሬደዋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛ...
07/11/2023

ADEEROO, RABBI JANNATAAN HAA QANANIISU😭
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ (አዴሮ) 1ኛ ዓመት የሙት መታሰቢያ ቀን በድሬደዋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
Sirni yaadannoo Doctora kabajaa Artist Alii Birraa magaalaa Dirree dhawaa Parkii Alii Birraatti gaggeefamaa jira.
Abbaa keenyaaf rabbiin jannataan haa qananiisu.🤲

To think too much is a disease.~Fyodor Dostoyevsky (Book: Notes from Underground https://amzn.to/454ouxg)(Art: 'The Weig...
14/08/2023

To think too much is a disease.
~Fyodor Dostoyevsky

(Book: Notes from Underground https://amzn.to/454ouxg)

(Art: 'The Weight Of Thought' sculpture by Thomas Lerooy)

የልጇ አባት ነፍሰ ጡር እያለች ጥሏት የጠፋባት እናት ልጄን አልፈልግም እያለች ነው!!😭😭😭😭በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን ስታረግዝ ፤ ያስረገዛት ወንድ ጥሏት ጠፍቷልእህታችንም በሰርጀሪ...
12/07/2023

የልጇ አባት ነፍሰ ጡር እያለች ጥሏት የጠፋባት እናት ልጄን አልፈልግም እያለች ነው!!😭😭😭😭

በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን ስታረግዝ ፤ ያስረገዛት ወንድ ጥሏት ጠፍቷል

እህታችንም በሰርጀሪ ልጇን በፖውሎስ ሆስፒታል በሰላም ተገላግላለች። ነገርን ግን አንድ ወር ሀኪም ቤት ከቆየች በኃላ ልጇን መንገድ ላይ ለመጣል ስትል ሰዎች ደርሰው ይዘዋታል። በአቅራቢያዋ ወደሚገኝ የሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤትም ወስደዋታል።

እናት በስነ ልቦና በጣም የተጎዳች ሲሆን ልጄን ጡት ማጥባትም ሆነ መያዝ አልፈልግም ብላለች።

የህፃኑን የርሃብ ሲቃ ቸተመለከተች በሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት የምትስራ አንዲት እናት ህፃኑን ጡት አጥብታ ለጊዜውም ቢሆን ከርሃብ ሲቃ ታድጋዋለች።

ቀጣይ የህፃኑ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? ማን ምን ማድረግ አለበት?? ህፃኑን ለጨከነበት የእናት አንጀት መልሶ መስጠት ተገቢ ሊሆን ይችል ይሆን??

ሃሳባችሁን አጋሩ!!

የእነዚህ 3 ህፃናት ልጆችች ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ማግኘት ይችሉ ዘንድ share ኘድርጉላቸው!!* እናታቸው ወይንም * አባታቸው ነኝ አልያም አውቃቸዋለሁ የሚል ወገን እንዲያገኛቸው አድርጉ!!ከ...
01/07/2023

የእነዚህ 3 ህፃናት ልጆችች ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ማግኘት ይችሉ ዘንድ share ኘድርጉላቸው!!

* እናታቸው ወይንም
* አባታቸው ነኝ አልያም አውቃቸዋለሁ የሚል ወገን እንዲያገኛቸው አድርጉ!!

ከትላንትና ወዲያ በአዲስ አበባ በአውቶብስ ተራ አካባቢ አንዲት ሴት እነዚህ ሶሶት ልጆች ይዛ ስትሄድ ፖሊስ ጠርጥሮ የያዛት ሲሆን እሷም ልጆቹን ከቡታጅራ ከተማ ነው ያመጣዋቸው ብላለች። እንዲሁም አሳዳጊ ነኝ ብላለች!!

ነገር ግን ፖሊስ ሴትየዋን በመጠራጠሩ ፖሊስ ጣቢያ አስገብቷታል።

የእነዚህ 3 ልጆች ቤተሰብነኝ የሚል አካል ካለ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማመልከት እንደሚችል እና ስለ ህፃናቱ ተጨማሪ መረጃ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ለመምሪያው መረጃ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

8.2 ኪ.ሜ ርዝመት እና ከ10 እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለውን የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል። ህዳር  2013...
01/07/2023

8.2 ኪ.ሜ ርዝመት እና ከ10 እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለውን የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ህዳር 2013 ዓ.ም የመንገዱን ግንባታ ባስጀመርንበት ወቅት የአካባቢው መህበረሰብ እና የጋራ መኖርያ ቤት ባለዕድለኞች “ቶሎ ገንቡልን” ሲል ጋቢ አልብሰው አደራ ሰጥተውን ነበር።
እኛም መንገዱ በአካባቢው ያለውን የመንገድ መሰረተ ልማት እጥረት የሚቀርፍ እና የጋራ መኖርያ ቤት ባለዕድለኞች ወደ ቤታቸው ሲገቡ የሚሰጣቸውን ፋይዳ በመገንዘብ ግንባታውን ባስጀመርንበት ወቅት በገባነው ቃል መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀን ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
በዚህ በጀት አመት የያዝናቸው ትልልቅ ተሻጋሪ ድልድዮች እና የመንገድ ፕሮጀክቶችም እየተጠናቀቁ ነው።

Mayor Adanech Abiebie.

በፊፋ የደረጃ ስንጠረዥ ምርጥ 10 የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች የትኞቹ ናቸው?ፊፋ የሰኔ ወር የሀገራት የደረጃ ሰንጠረዥን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ አርጀንቲነ ከዓለም ቀዳሚ ናት። በሰኔ ወር የደረጃ ...
01/07/2023

በፊፋ የደረጃ ስንጠረዥ ምርጥ 10 የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች የትኞቹ ናቸው?

ፊፋ የሰኔ ወር የሀገራት የደረጃ ሰንጠረዥን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ አርጀንቲነ ከዓለም ቀዳሚ ናት። በሰኔ ወር የደረጃ ሰንጠረዥ ሞሮኮ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ኢትዮጵያ በፊፋ የሰኔ ወር የደረጃ ሰንጠረዥ ከዓለም 143ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ ከአፍሪካ ደግሞ 42ኛ ደረጃን ይዛለችይዛለች።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SDL posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share

Addis TV

የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን አዲስ ቴሌቭዥን ለተሻለ ጥራት በመስራት ላይ ይገኛል በመሆኑም በEutlesat 8 WB @west Frequency 12688 Polarization V Symbol rate 27500 ላይ በጥራት መከታተል ትችላላችሁ