General News/ጠቅላላ ዜና

General News/ጠቅላላ ዜና እውነት እውነት ነው!!!

" ለፍትሃዊ ጥያቄያችን ፍትሃዊ ምላሽ እንሻለን !! " የመቐለ 70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበራት አመራርና አባላት " ጥያቄያችን ላለፉት 6 ዓመታት ሰሚ ጀሮ አጥቷል " በማለት በትግራይ ጊዚያ...
24/04/2025

" ለፍትሃዊ ጥያቄያችን ፍትሃዊ ምላሽ እንሻለን !! "

የመቐለ 70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበራት አመራርና አባላት " ጥያቄያችን ላለፉት 6 ዓመታት ሰሚ ጀሮ አጥቷል " በማለት በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በሰላማዊ ሰልፍ ምሬታቸውን ገልፀዋል።

ከ6 ዓመታት በፊት ለአንድ አባወራ 70 ካሬ ሜትር የመኖሪያ የቤት ግንባታ መሬት ለመሰጠት በሚፈቅድ መመሪያ መደራጀታቸው ገልጸው ከጦርነት በኋላ ነባሩ መመሪያ በመጣስ በአፓርታማ ነው የምትስተናገዱት መባላቸው ኢፍትሃዊ እንደሆነ ገልጸዋል።

በትግራይ ደረጃ የተደራጁት እነዚህ 60 ሺህ የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር ጥያቄ አቅራቢዎች የመኖሪያ ቤት የግንባታ መሬት አሰጣጥ አስመልክቶ በክልሉ ከተሞች የሚታየው ወጥ ያልሆነ አሰራር እንዲታረም ድምፃቸውን አስምተዋል።

በሌሎች ከተሞች ተፈቅዶ በመቐለ ከተማ ለ70 ካሬ የቤት መኖሪያ ግንባታ " መሬት አይሰጥም " መባሉ አጅግ እንዳስገረማቸውና እንዳሰዘናቸው ገልፀዋል።

ጥያቄያቸው የተደረጁበት መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት የመኖሪያ የቤት ግንባታ መሬት ከማግኘት የዘለለ ፓለቲካዊ ተልእኮና ዓላማ እንደሌለው አስረድተዋል።

ከቤት ኪራይ ስቃይና ሰቆቃ እንዲገላገሉ የሚያስችል መንግስታዊ መፍትሄ እንደሚሹ ተናግረዋል።

ማህበራቱ ዛሬ ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት አከባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችና መፈክሮች እያሰሙ አስከ እኩለ ቀን ቢጠብቁም ጥያቄዎቻቸው ሰምቶ ምላሽ የሚሰጥ የመንግስት ሃላፊ እንዳልተገኘ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከቦታው ሆኖ መረጃውን ልኳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ፖሊስ የሠርግ አጃቢ አሽከርካሪዎችን አስጠነቀቀበአዲስ አበባ ከተማ በዓላትና ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ መንገድ የሚዘጉ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲ...
23/04/2025

ፖሊስ የሠርግ አጃቢ አሽከርካሪዎችን አስጠነቀቀ

በአዲስ አበባ ከተማ በዓላትና ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ መንገድ የሚዘጉ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።

ሕብረተሰቡ የጸጥታ አካላት የሚያስተላልፉትን የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶች በአግባቡ እየተገበረ መሆኑን ተከትሎ በከተማዋ የወንጀል ድርጊቶች እየቀነሱ መምጣታቸውንም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንዳሉት፣ በከተማዋ የትንሳኤ በዓል በሰላማዊ ሁኔታ ተከብሯል።

ቀላል ከሚባሉ የስርቆትና የማጭበርበር ድርጊቶች ውጪ በዓሉን ተከትሎ ውስብስብና ከባድ የወንጀል ድርጊቶች አለመፈጸማቸውንም አመልክተዋል።

ለዚህ ደግሞ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበሩ መሆኑን በመጥቀስ።

መጪውን የሰርግ ወራት ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ላይ ያልተገባ የመንገድ መጨናነቅ የሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ከተማዋን በማይመጥን መልኩ መንገድ በሚዘጉና የትራፊክ ፍሰቱን በሚያስተጓጉሉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም መናገራቸውን ተዘግቧል።
(ኢዜአ)

በመዲናዋ የትንሣኤ በዓል እንዴት አለፈ ?በ2017 ዓ/ም የትንሣዔ በዓል የተለያዩ ደንቦችን በተላለፉ አሽከርካሪዎች እርምጃ መወሰዱን፣ የበዓል ዋዜማ አንድ ሰው በመኪና አደጋ መሞቱን የአዲስ ...
22/04/2025

በመዲናዋ የትንሣኤ በዓል እንዴት አለፈ ?

በ2017 ዓ/ም የትንሣዔ በዓል የተለያዩ ደንቦችን በተላለፉ አሽከርካሪዎች እርምጃ መወሰዱን፣ የበዓል ዋዜማ አንድ ሰው በመኪና አደጋ መሞቱን የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን አሉ ?

“ ከወንጀል አንጻር ስንመለከት፥ በመደበኛነት ከሚፈጸሙ እንደሌብነት፣ ጸብ፣ ቅሚያና የመሳሰሉ ከመጠጥ ጋር የተገናኙ ድርጊቶች ካልሆኑ በስተቀር ከበዓሉ ጋር በተገናኘ ከባድ ወንጀል የተፈጸመበት ጊዜ አልነበረም።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ኮድ 2 64942 አውቶብስ የ50 ዓመት እድሜ ያላቸው ሰው በውስጥ ለውስጥ መንገድ ወጥተው ሲሻገሩ ገጭቷቸው ህይወታቸው እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል።

የትራፊክ አደጋ ላይ በአልኮል መጠጥ ፍተሻ ጭምር ቁጥጥር አድርገናል። በዚህም በአልኮል ጥሰት ወደ 1,072 አሽከርካሪዎችን ተፈትሽዋል። 33 አሽከርከሪዎች ከመጠን በላይ ጠጥተው ሺያሽከረክሩ ተገኝተው በደንብ መተላለፍ ቅጣት ተወስዶባቸዋል።

ከመጠን በታች የጠጡ ደግሞ ወደ 41 አሽከርካሪዎች አግኝተናል። አልኮል ጠጥተዋል፤ ግን መጠኑ ከ0.4 በላይ አይደለም። ከፍተኛ የሚባለው ከዚህ በላይ ሲሆን ነው። ግን ይሄም አደጋ የሚያደርስ ስለሆነ አስተምረን ለቀናቸዋል።

ሌሎች ልዩ ልዩ ደንቦችን የጣሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር አድርገናል። ወደ 99 አሽከርካሪዎች ደንብ ሲተላለፉ ተገኝተው አስፈላጊው እርምጃ ተወስዶባቸዋል። በዓሉ በጣም ደማቅ ነበር፤ ከድምቀቱና ከሰው ብዛቱ አንፃር ሰላማዊ በዓል አሳልፈናል ማለት ይቻላል ” ብለዋል።

ሰዎች ወንጀል ሲፈጽሙ ብዙ ጊዜ በጥቅል “እርምጃ ተወስዶባቸዋል” ነው የሚባለውና በሾፌሮቹ የተወሰደው እርምጃስ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ “ ከ70 በላይ ደንብ መተላለፎች ናቸው። 70ዎቹንም መጥቀስ አይቻልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በበዓሉ ህገ ወጥ የብር ኖት ማጭበርበር፣ በምግብና መጠጥ ላይ በዓድ ነገሮችን ቀላቅሎ ከመሸጥ አንፃር የተፈጸመ ወንጀል ካለ ስንጠይቃቸውም፣ እስካሁን የደረሳቸው የክስ ሁኔታ እንደሌለ፣ ካለ ግልጽ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል።

ኮማንደር ባስተላለፉት መልዕክት ምን አሉ ?

“ ከዚህ በኋላም የሰርግ ወራት ነው፤ በተለይ የትራፊክ አደጋ ሥጋት አለብን ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩ ሹፌሮች እንደሚበዙ ይገመታል።

አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ሰው ስለሚበዛ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ ሰውና እቃን አንድ ላይ መጫን እና የመሳሰሉ ደንብ መተላለፎች ሊበዙ ይችላሉ ተብሎ ስለሚገመት ጥብቅ ቁጥጥር እናደርጋለን።

የትራንስፓርት መጠበቂያ፣ በጥቅሉ ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች የኪስ ቀበኞች ሊኖሩ ስለሚችሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት ” ብለዋል።

ልዩ መረጃ‼️በቁጥጥር ስር የዋለውን ኃይለ ሊባኖስ ኃይለሚካኤልን በሚመለከት በርካታ መረጃዎች እየተፈለፈሉ ነው። በተገኘው መረጃ መሰረት ኃይለ ሊባኖስ የፈትለወርቅ ገብረእግዛብሔር (መንጆሪኖ)...
22/04/2025

ልዩ መረጃ‼️

በቁጥጥር ስር የዋለውን ኃይለ ሊባኖስ ኃይለሚካኤልን በሚመለከት በርካታ መረጃዎች እየተፈለፈሉ ነው።

በተገኘው መረጃ መሰረት ኃይለ ሊባኖስ የፈትለወርቅ ገብረእግዛብሔር (መንጆሪኖ) ባለቤት ነው። ግለሰቡ ከጦርነቱ በፊት በለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ በመሆን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህ ቆይታው ከሀገራዊ ስራ ይልቅ በዋናነት በህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር፣ ማዕድን ዝውውር እና ህገ ወጥ ጦር መሳርያን በአስፈፃሚዎቹ በኩል በማስተሌለፍ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮችን ያፈራ ነው። ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላም ቢሆን መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ለመቆጣጠር ባለበት ጊዜ 25 ኩንታል ወርቅ እና 300ሺ ዶላር በካሽ ይዞ ለንደን ገብቷል። ለዚህም ዶ/ር ደብረፅዮን እና መንጆሪኖ ተመካክረው “ህወሓትን ወክሎ እየተጓዘ መሆኑን እና ንብረቱም የህውሓት ነው” የሚል ደብዳቤ ፅፈውለት ነበር። እንደሚታወሰው የወርቅ ጉዳይ የሕወሓት ሰዎችን ብዙ ሲያባላ ቆይቷል። አሁን ፍንጭ የተገኘ ይመስላል።

የጉሮሮ አለርጂ ምንነት እና መፍትሄዎች🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶የጉሮሮ አለርጂ (አለርጂክ ፋረንጃይተስ) (Allergic pharyngitis) በአለርጂ ሪአክሽን ወይም ምላሽ ምክንያት ጉሮሮ ሲቆጣ ...
18/04/2025

የጉሮሮ አለርጂ ምንነት እና መፍትሄዎች
🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶

የጉሮሮ አለርጂ (አለርጂክ ፋረንጃይተስ) (Allergic pharyngitis) በአለርጂ ሪአክሽን ወይም ምላሽ ምክንያት ጉሮሮ ሲቆጣ (irritated) የሚከሰት ሁኔታ ነው።

አብዛኛውን ጊዜ በአበባ ድቄት (ፖለን)፣ በአቧራ ብናኝ፣ በቤት እንስሳት፣ ወይም በአንዳንድ ምግቦች ምክንያት አለርጂ ይቀሰቀሳል ወይም ይነሳል።

✳️ የጉሮሮ አለርጂ መንስኤዎች | Causes of Throat Allergy
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

የጉሮሮ መቆጣትን ሊያስከትሉ ወይም ሊቀሰቅሱ የሚችሉ የተለመዱ አለርጂኖች (allergens) የሚከተሉት ናቸው:-

🍋 አየር ወለድ አለርጂኖች:- የአበባ ዱቄት፣ በዓይን የማይታዩ ጥቃቅን ነፍሳት፣ የሻጋታ ስፖሮች፣ የቤት እንስሳት ብናኞች።

🍋 የምግብ አለርጂኖች፡ ለውዝ፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ እንቁላል፣ ሼልፊሽ፣ አኩሪ አተር፣ ስንዴ።

🍋 የሚያስቆጡ ነገሮች፡- ማጨስ (ሲጋራ ወይም የአየር ብክለት)፣ ጠንካራ ሽታ፣ ኬሚካሎች።

🍋 የአየር ሁኔታ ለውጦች:- ቀዝቃዛ፣ ደረቅ አየር የጉሮሮ ሴንሲቲቪቲን ያባብሳል።

🍋 ፖስትናሳል ድሪፕ (postnasal drip):- ንፍጥ ወደ ጉሮሮ ውስጥ እንዲንጠባጠብ የሚያደርግ አለርጂ።

✳️ ምልክቶች | Symptoms!
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

🍓 የጉሮሮ ማሳከክ ወይም መብላት
🍓 የድምጽ መጎርነን ወይም መቀየር
🍓 ደረቅ ሳል
🍓 ለመዋጥ መቸገር
🍓 የቶንሲል ማበጥ ወይም መቆጣት (አንዳንድ ጊዜ)
🍓 የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት
🍓 በዓይን ስር የሚታዩ ጥቋቁር ነጠብጣብ
🍓 ማስመለስ፣ ማስቀመጥ (በተለይም በምግብ ምክንያት የተከሰተ አለርጂ ሲሆን)።

✳️ ወደ ሕክምና መሄድ ያለብን መቼ ነው? | When to See a Doctor
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

🍑 የበሽታው ምልክቶቹ ከአንድ ሳምንት በላይ ከቆዩ
🍑 ከባድ እብጠት ወይም የመተንፈስ ችግር ካለ።
🍑 ከፍተኛ ትኩሳት (አለርጂ ሳይሆን ኢንፌክሽንን ሊያመለክት ይችላል)

✳️ ለጉሮሮ አለርጂ የሚደረግ ሕክምና | Treatment for Throat Allergy
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

1️⃣ አንታይሂስታሚን | Antihistamines:- (ለምሳሌ:- Cetirizine, Loratadine, Fexofenadine) - የአለርጂ ምላሾችን ያግዳሉ።

2️⃣ ዲኮንጀስታንት | Decongestants:- (ለምሳሌ:- Pseudoephedrine) - የአፍንጫ መታፈንን እና ፖስትናሳል ድሪፕን ይቀንሳል።

3️⃣ ትሮት ላዛንጂስ ስፕሬይስ | Throat Lozenges or Sprays:- የጉሮሮ መቆጣትን ያስታግሳል (ለምሳሌ:- ማር ወይም ሜንቶል የያዙ)።

4️⃣ ናሳል ኮርቲኮስቴሮይድ ስፕሬይስ | Nasal Corticosteroid Sprays:- (ለምሳሌ:- Fluticasone) - በአፍንጫ የአየር መተላለፊያ ቱቦዎች ውስጥ ኢንፍላሜሽንን ይቀንሳል።

5️⃣ በጨው ውሃ መጉመጥመጥ | Saltwater Gargle:- የጉሮሮ መቆጣትን ለማስታገስ ይረዳል።

6️⃣ ሃይድሬሽን | Hydration:- ሙቅ ሻይ፣ ሾርባዎች እና ውሃ ጉሮሮአችንን እርጥብ ያደርገዋል። continued

 #ለጥንቃቄ" በተለይ ነጋዴዎች ቢዚ የሚሆኑባቸው ስቶሮች/ሱቆች አካባቢ የወንጀል ፈፃሚዎች ትኩረት ነው " - ኮማንደር ማርቆስ ታደሰበትንሳዔ የበዓል ግብይት ወቅት ሸማቾችና ነጋዴዎች ከህገ ወ...
18/04/2025

#ለጥንቃቄ

" በተለይ ነጋዴዎች ቢዚ የሚሆኑባቸው ስቶሮች/ሱቆች አካባቢ የወንጀል ፈፃሚዎች ትኩረት ነው " - ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ

በትንሳዔ የበዓል ግብይት ወቅት ሸማቾችና ነጋዴዎች ከህገ ወጥ የገንዘብ ኖቶች መጭበርበር እንዲሁም ከምግብና መጠጥ ጋር ከሚቀላቀሉ ባዕድ ነገሮች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳሰበ።

በህገወጥ ወጥ የብር ኖት ከመጭበርበር ማህበረሰቡ በምን መልኩ ሊድን ይችላል ? ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ? ማጭበርበሩ የሚፈጸመውስ በምን ሁኔታ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኮሚሽኑን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን መለሱ ?

“ በበዓል ሰሞን ከሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች መካከል አንዱ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ነው። ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ በሁለት መልኩ ነው በገበያ ላይ እንቅስቃሴ የሚያደርገው።

አንዱ፥ ሙሉ ለሙሉ ህገ ወጥ የሆኑ የገንዘብ ኖቶች ወደ ገበያ ሊመጡ ይችላሉ። ወይን ደግሞ ህጋዊ ከሆኑት ጋር በመቀላቀል ህነ ወጥ የገንዘብ ኖቶች ወደ ገበያ ሊመጡ ይችላሉ።

ስለዚህ በተለይ ነጋዴዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። በተመሳሳይ ሸማቾችም ከነጋዴዎች የሚቀሉትን አረጋግጠው መቀበል ይኖርባቸዋል።

በተለይ ነጋዴዎች ቢዚ የሚሆኑባቸው ስቶሮች/ሱቆች አካባቢ የወንጀል ፈፃሚዎች ትኩረት ነው። እዚያ አካባቢ መጥተው አጭበርብረው ከሌሎች ሰዎች ገንዘቡን ሰጥተው ሊሄዱ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል።

ስለዚህ ነጋዴው ገንዘብ የሚቀበል ራሱን የቻለ አንድ ሰው፣ ቁሳቁሶቹን ለሸማች የሚሰጥ ደግሞ ሌላ ሰው አድርጎ በጥንቃቄ መገበያዬት ያስፈልጋል። ካልሆነም ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን መከተልም ተቀባይነት አለው ” ብለዋል።

ኮማንደሩ በሚበሉና በሚጠጡ ነገሮች መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

“ የሚበሉና የሚጠጡ ነገሮች ላይ ባዕድ ነገሮችን ቀላቅሎ ማምጣት በተለይ በበዓል ሰሞን ቁጥሩ ከፍ ይላል ተብሎ ይገመታልና በተቻለ አቅም ሸማቾች የሚገዟቸውን ለበዓል የሚጠቀሟቸው እንደ ዘይት፣ ቅቤ፣ በበሬና የመሳሰሉ ነገሮችን በጥንቃቄ መገብዬት እንዳለባቸው ለማስታወስ እንወዳለን።

በእምነት ተቋማት፣ በዋና ዋና አደባባዮች በሰፈሮች አካባቢ ጠንካራ የወንጀሎች መከላከል ሥራ እንሰራለን። ህብረተሰቡ ግን አጠራጣሪ ነገር ካየ በ 0111110111 እና በ 991 መረጃ በመስጠት ተባባሪ መሆን አለበት ” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

“ የአዲስ አበባ ፓሊስ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ሥራ ገብቷል። በዓሉን የሚመጥን ትልቅ ዝግጅት ተደርጓል። በበዓሉ ከሚሰማራው የወንጀልና የትራፊክ መከላከል አባላት ባሻገር በበዓሉ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። በተለያዩ የመገበያያ ቦታዎች የፓሊስ ጥበቃ እናደርጋለን ” ነው ያሉት።

  : በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረውን የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ አገልግሎት ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ ውሳኔ ሃሳብ ላይ ካቢኔው ውሳኔ አሳለፈ።የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ አመት 10...
18/04/2025

: በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረውን የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ አገልግሎት ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ ውሳኔ ሃሳብ ላይ ካቢኔው ውሳኔ አሳለፈ።

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ከነዚህም አንዱ ተቋርጦ የነበረዉ የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን የሚመለከት ነበር።

በዚህም አገልግሎቱን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ ማሳለፉ ተነግሯል።

ሌላኛው ፦
- የብርሃን አይሰውራን፣
- የመነን
- የገላን ቦርዲንግ ትምህርት ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማዉ ትምህርት ቢሮ እንዲሆን የቀረበዉን ደንብ መርምሮ አጽድቋል።

ካቢኔው ሀገራዊ ፋይዳ አላቸው ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

አንድ ኪሎ ስጋ ከ460 እስከ 520 ብር ብቻ እንዲሸጥ ተተመን   | ለፋሲካ በዓል 239 የሸማች የህብረት ስራ ሉካንዳ ቤቶች አንድ ኪሎ ስጋ ከ460 እስከ 520 ብር ብቻ እንዲሸጡ ተመን መ...
17/04/2025

አንድ ኪሎ ስጋ ከ460 እስከ 520 ብር ብቻ እንዲሸጥ ተተመን

| ለፋሲካ በዓል 239 የሸማች የህብረት ስራ ሉካንዳ ቤቶች አንድ ኪሎ ስጋ ከ460 እስከ 520 ብር ብቻ እንዲሸጡ ተመን መቀመጡን የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ልእልቲ ግደይ በሰጡት መግለጫ ለበዓሉ የእርድ እንስሳት ወደ ከተማዋ እንዲገቡ በማድረግ 1 ኪሎ ስጋ ከ460 እስከ 520 ብቻ በማህበራቱ ሉካንዳ ቤቶች እንዲሸጥ በጥናት ተወስኗል ብለዋል።

በተጨማሪም 137 ባዛሮች በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን እንዲያቀርቡ መደረጉን እና 800 የሚጠጉ የህብረት ስራ ሱቆች ለበዓሉ ሙሉ አቅርቦትን በመያዝ እየሰሩ መሆናቸውን ኮሚሽነሯ አመልክተዋል።

 “ አስከሬኑን ይዘው ትላንት ምሽት 11 ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል። ዛሬ ቀጨኔ ተቀበሩ ” - የረዳቱ የቅርብ ሰው➡️ " የኔ ቤተሰቦች ሦስት ናቸው። ከሦስቱ አንዷ ሞታለች። ትላንት ተቀበረ...
15/04/2025



“ አስከሬኑን ይዘው ትላንት ምሽት 11 ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል። ዛሬ ቀጨኔ ተቀበሩ ” - የረዳቱ የቅርብ ሰው

➡️ " የኔ ቤተሰቦች ሦስት ናቸው። ከሦስቱ አንዷ ሞታለች። ትላንት ተቀበረች " - ቤተሰብ

ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ ነበር የተባሉ የአንድ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎች ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ/ም ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ “ጎሃ ፅዮን” እና “ ቱሉ ሚልኪ ” የተሰኘ ቦታ ሲደርሱ የግድያና እገታ ጥቃት እንደደረሰባቸው መገለጹ ይታወቃል።

በታጣቂዎች ታገተ የተባለው መኪና ባለቤት የመኪናው ረዳት መገደላቸውን፣ ሁለት የሟች ቤተሰቦችም ተገደሉ የተባሉት ረዳት ዛሬ መቀበራቸውን፣ ሌላኛው የሟች ቅርብ ቤተሰብ ደግሞ ሌሎች ሁለት ተሳፋሪዎች መገደላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት ምን አሉ ?

የተሽከርካሪው ባለቤት ትላንት በሰጡን ቃል፣ 62 ሰዎችን አሳፍሮ የተነሳው የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መታገቱ በስልክ እንደተነገራቸው፣ ረዳቱ መሞቱን እንደሰሙ፣ ሹፌሩ እስካሁን ያለበትን እንደማያውቁ ተናግረዋል።

እኝሁ አካል፣ ስለጉዳዩ እንዲያጣሩ ሰዎችን ወደ ቦታው መላካቸውን፣ የተላኩት ሰዎች ስልካቸው ባለመስራቱ ምንም መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ተጨማሪ መረጃ ስንጠይቃቸው ልቅሶ ላይ እንደሆኑ ገልጸው፣ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የሟች ቅርብ ሰዎችስ ምን አሉ ?

የሟቹ የቅርብ ቤተሰብ ዛሬ በሰጡን ቃል ደግሞ፣ " አስከሬኑን ይዘው ትላንት ምሽት 11 ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል። ዛሬ ቀጨኔ ተቀበሩ " ብለዋል።

" አንዱ ሟች ረዳት ነው። ሹፍርና ይሰራ ነበር፤ ግን በእግሩ ላይ ህመም አድሮበት በኋላ ረዳት ሆኖ ነው እየሰራ የቆየው " ብለው፣ " ምስጋና ለአንዳንድ ደጋግ ኢትዮጵያውያን አስክሬኑን ገንዘው አዘጋጅተው ለጠበቁን ሰዎች ይሁን። እንደዚህም አይነት ሰዎች አያሳጣን " ነው ያሉት።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሟች ልጅ ጓደኛ በበኩላቸው፣ " አባታቸው ነበር የሚያስተዳድሯቸው። ሟቹ ጓደኛዬን ጨምሮ ሦስት ልጆች አሏቸው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በቀጨኔ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥርዓት ዛሬ እንደፈጸመ ገልጸው፣ ልጆቹ ሲያስተዳድራቸው የነበረ አባታቸውን በቅጽበት ስላጡ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሌሎች የሟቾች ቤተሰቦች ምን አሉ ?

አንድ የሟች ቤተሰብ፣ "ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ ባሱ ተኩስ ተነሳበት ጎሃ ፅዮን አካባቢ ነው)፤ የኔ ቤተሰቦች ሦስት ናቸው። ከሦስቱ አንዷ ሞታለች። ሁለቱ እህትማማቾች ነበሩ አንደኛዋ ቤተሰብ ነች። ሁለቱ ተረፉ አንዷ ግን ሞታለች ተቀበረች " ሲሉ ነግረውናል።

መንግስት፣ ሚዲያዎች ጉዳዩን ትኩረት እንዳልሰጡት ገልጸው፣ "ብቻ ወደት እየሄድን እንደሆነ በጣም ያሳስባል። ፈጣሪ አገራችንን ሰላም ያድርግ እንጂ የመንግስቱ ነገርስ ጭር የሚልም የለም " ሲሉ አዝነዋል።

ሌላኛው የቤተሰብ አባል ደግሞ፣ ሁለት ተሳፋሪዎች መገደላቸውን፣ ቤተሰብ ሀዘን ላይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከተሳፋሪዎቹ መካከል ከፊሎቹ ታግተው እንደተወሰዱ፣ ለጊዜው ቁጥሩን በውል ማወቅ ባይቻልም በርካቶች እንደተገደሉ የተመላከተ ሲሆን፣ ታግተው ተወሰዱ የተባሉት ዬት እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም።

ትላንት ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቃቸው በፌደራል ፓሊስ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ፣ ሌላ ሥራ ላይ እንደሆኑ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ በድጋሚ ስለእገታው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ መኩራ ስናደርግም ስልካቸውን አላነሱም።

እያጣራሁ ነው! - የአዲስ አበባ ፖሊስ    | ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እ...
14/04/2025

እያጣራሁ ነው! - የአዲስ አበባ ፖሊስ

| ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

ግለሰቡ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸውን ያነሱበት ጉዳይ ሆኗል።

ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቦቹ ከሚያነሱት ቅሬታ ባሻገር በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች በመልቀቅ በፈፀመው ህገ ወጥ ተግባርና በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አንዳንድ ምስሎች ተገቢነታቸውን የሳቱና ያፈነገጡ እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ ገልፆ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

13/04/2025
" ጤና ሚኒስቴር ' አጽድቄዋለሁ ' የሚለው አዋጅ የጤና ባለሞያዎችን ችግር የሚፈታ ነው ይላል ነገር ግን ችግሮቻችን እነኚህ ብቻ አይደሉም " - ሃኪም➡️ " አዋጁ የጤና ባለሞያዎችን የረጅም...
12/04/2025

" ጤና ሚኒስቴር ' አጽድቄዋለሁ ' የሚለው አዋጅ የጤና ባለሞያዎችን ችግር የሚፈታ ነው ይላል ነገር ግን ችግሮቻችን እነኚህ ብቻ አይደሉም " - ሃኪም

➡️ " አዋጁ የጤና ባለሞያዎችን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ ነው " - ጤና ሚኒስቴር

የጤና ባለሞያዎች " ለዘመናት እየጠየቅናቸው ያሉ በጤናው ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮቻችን ይፈቱ" ሲሉ ድምጻቸውን በተለያየ መንገድ በዘመቻ እያሰሙ ናቸው።

በርካታ ባለሙያዎችም ጥያቄያቸውን እና ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎቹ በተለያዩ መንገዶች እያካሄዱ የሚገኙትን ዘመቻ ለመከታተል ባደረገው ጥረት በርካታ ባለሙያዎች በተናጠል እንዲሁም አንዳንድ የሞያ ማህበራት ዘመቻውን እያስተጋቡ መሆኑን ለማስተዋል ችሏል።

10 ነጥቦችን ይዞ የተነሳው ዘመቻ ፦
- የኢኮኖሚ፣
- የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣
- የሃኪሞች የሥራ ቦታ ደህንነት ፣
- የቤት እና የትራንስፖርት አቅርቦት፣
- አግባብነት ያለው ወቅታዊ የሥራ ክፍያ
- ለአለም አቀፍ የሥራ ገበያ የሚወዳደሩበት የብቃት መመዘኛ የፈተና ማዕከላት በሃገር ውስጥ እንዲቋቋሙ ይጠይቃል።

ንቅናቄው የኢትዮጵያ የህክምና ማህበር ድጋፍ ያለው ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ለማህበሩ ፕሬዝዳንት ፣ ስራ አስፈጻሚዎች እና የህዝብ ግንኙነት ክፍል ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማህበሩ አባል ከሆኑ እና ስሜ አይጠቀስ ብለው ከጠየቁ የጤና ባለሞያ ንቅናቄው የማህበሩ ሙሉ ድጋፍ ያለው ስለመሆኑ አረጋግጠዋል።

" ማህበሩ ከዚህ በፊት ሲያነሳ የነበራቸው በርካታ ጥያቄዎች ነበሩ ባለመመለሳቸው ምክንያት ድጋሚ ጥያቄውን በማንሳት ለጤና ሚኒስቴርም ደብዳቤ እንሚያስገቡ እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮም እየተዘጋጀ ያለ ደብዳቤ መኖሩን መረጃው አለኝ " ብለዋል።

የጤና ባለሞያና የማህበሩ አባል በዝርዝር ባነሱት ሃሳብ ምን አሉ ?

" የንቅናቄው የመጀመሪያ አላማ የጤና ባለሞያዎችን መብት ማረጋገጥ ነው።

መብት ስንል ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መብት ሊሆን ይችላል በዋናነት ኢኮኖሚያ ያለብን ጫና መስተካከል አለበት።

የአንድ ሃኪም የሚከፈለው ደሞዝ እና የሚኖርበት ሁኔታ ሲታይ በጣም አሳፋሪ ነው።

እየተራበ የሚያገለግልበት ሰዓት ታሳቢ ተደርጎ ፣ምን ያህል ድካም እንዳለበት እና ምን ያህል ሰዓት እንደሚሰራ ታሳቢ ተደርጎ ሊከፈል ከሚገባው ጋር አይመጣጠንም።

የትኛውም ሆስፒታል የሚሰራ ሃኪም ሳይከፍል መታከም አይችልም እንደማንኛውም ህብረተሰብ ካርድ አውጥቶ እና ከፍሎ ነው የሚታከመው ይህ መሆን የለበትም በሚያገለግልበት ሆስፒታል ነጻ የህክምና አገልግሎት ሊመቻችለት ይገባል።

ጤና ሚኒስቴር ' አጽድቄዋለሁ ' የሚለው አዋጅ የጤና ባለሞያዎችን ችግር የሚፈታ ነው ይላል ነገር ችግሮቻችን እነኚህ ብቻ አይደሉም በአንድ በኩል ብቻ ችግሩን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት አመርቂ አይደለም ከዚህ ቀደምም የተነሱ ጥያቄዎች አሉ አንዱን ክንፍ ብቻ ፈትተህ ሙሉ በሙሉ ችግሮቹ ተፈተዋል ብለህ የምትናገረው አይደለም።

የእኛ ጥያቄ ችግሮቹ በሙሉ ይታዩ ነው ከችግሮቹ መካከል አንድ ነጠላ ነገር ብቻ አውጥተህ ይኸው ችግራቹን ፈትተናል ችግር የለም ተብሎ ለማድበስበስ የሚኬደው ጥረት ተገቢ አይደለም " ብለዋል።

የጤና ሚኒስቴር ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ገባኤ ላይ የጸደቀው " የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 " የጤና ባለሞያዎችን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ ነው ብሏል።
....

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 08:00
Tuesday 09:00 - 08:00
Wednesday 09:00 - 08:00
Thursday 09:00 - 08:00
Friday 09:00 - 08:00
Saturday 09:00 - 08:00
Sunday 09:00 - 06:00

Telephone

+251911813506

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when General News/ጠቅላላ ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category