Team Talk Sport ቲም ቶክ ስፖርት

Team Talk Sport ቲም ቶክ ስፖርት ሁሉንም ስፖርት በአንድ መነፅር, "THE IN & OUT" We feed all sport news and analysis from every corner. sport news source

 #ሮማ ደርዘን ሲደመር 2 ለ 0 አሸነፈ::ሮማ ትላንት ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ 14 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል ።
21/07/2025

#ሮማ ደርዘን ሲደመር 2 ለ 0 አሸነፈ::

ሮማ ትላንት ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ 14 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል ።

ራሽፎርድ ከአባቱና ወንድሙ ጋር በባርሴሎና
21/07/2025

ራሽፎርድ ከአባቱና ወንድሙ ጋር በባርሴሎና

 #የ15 አመት ደቡብ አፍሪካዊ አትሌት ነው። #በናይጀሪያ አቡኩታ በተደረገው ከ18&20  አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን ክብረወሰኑን ያሻሻለ ተስፈኛ ነው። #ጆሽዋ ጌር...
21/07/2025

#የ15 አመት ደቡብ አፍሪካዊ አትሌት ነው።

#በናይጀሪያ አቡኩታ በተደረገው ከ18&20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን ክብረወሰኑን ያሻሻለ ተስፈኛ ነው።

#ጆሽዋ ጌርበር በዲስከስ ውርወራ 64.48 ሜትር በመወርወር በታዳጊዎች የአለም ሻምፒዮና ክብረ ወሰን ተጋርቷል።

 #አይምረው ዛሬ ልደቱ ነውሃላንድ ዛሬ 25 አመቱን ይዟል.    መልካም  ልደት
21/07/2025

#አይምረው ዛሬ ልደቱ ነው
ሃላንድ ዛሬ 25 አመቱን ይዟል.

መልካም ልደት

 #ከራግቢ ተጫዋችነት ወደ ቼልሲ 9 ቁጥር ለባሽነት #የወርዋሪው ሮሪ ዴላፕ ልጅ ሊያም ዴላፕ #ሮሪ ዴላፕ ይባላል፡፡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለደርቢ ካውንቲ፣ ሰንደርላንድ፣ ሳውዝሀምፕተን እ...
21/07/2025

#ከራግቢ ተጫዋችነት ወደ ቼልሲ 9 ቁጥር ለባሽነት

#የወርዋሪው ሮሪ ዴላፕ ልጅ ሊያም ዴላፕ

#ሮሪ ዴላፕ ይባላል፡፡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለደርቢ ካውንቲ፣ ሰንደርላንድ፣ ሳውዝሀምፕተን እና ስቶክ ሲቲ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡

በተለይ ለስቶክ ስቲ በተጫወተባቸው አምስት አመታት በሚጠቀማቸው የመልስ ውርወራዎች ብዙዎች ያውቁታል፡፡

ሀይልን በቀላቀለ አጨዋወቱ የሚታወቀው የአሰልጣኝ ቶኒ ፑሊስ ስብሰብ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ ነበር፡፡

የአየር ላንድ ሪፐብሊኩ አማካይ የቅጣት ምት እና የማእዘን ምት ያክል በሚያስፈሩ ውርወራዎቹ በበርካታ አጋጣሚዎች ክለቡ ውጤት ይዞ እንዲወጣ አድርጓል፡፡

በስቶክ ሲቲ ቆይታው በውርወራ ብቻ 24 ቀጥታ ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶም አቀብሏል፡፡

በ2008/09 የውድድር አመት ስቶክ ሲቲ በሊጉ አርሰናልን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ሮሪ ዴላፕ አመቻችቶ በማቀበል እና በጨዋታው በሚወረውራቸው ኳሶች የነበረው አስፈሪነት አርሰን ቬንገር ጨዋታው እግር ኳስ አይመስልም የሚል ሃሳብ እንዲሰነዝሩም አድርጓቸው ነበር፡፡

አሁን ደግሞ ልጁ ሊያም ዴላፕ የፕሪሚየር ሊጉ ተስፋ የተጣለበት ኮከብ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ በተያዘው የክረምቱ የተጫዋቾ የዝውወር መስኮት ከኢፕስዊች ታውን ወደ ቼልሲ አምርቷል፡፡

ከእግሩ ይልቅ በእጁ በሚወረውራቸው ኳሶች በተጽዕኖ ፈጣሪነቱ የሚታወቀው ሮሪ ዴላፕ ልጅ በትምህርት ቤት የራግቢ ተጫዋች ነበር፡፡

እንደ አባቱ በእጁ መጫዎት የሚቀናው ሊያም ዴላፕ በልጅነቱ ጎበዝ የራግቢ ተጫዋች እና በአጭር ርቀት ሩጫ የተዋጣለት አትሌት እንደነበር በትምህርት ቤት የስፖርት ሳይንስ መምህሩ የነበሩት ሰው ማርክ ሴለርለማንችስተር ኢቭኒንግ ተናግረዋል፡፡

የእግር ኳስ ህወቱን በደርቢ ካውንቲ አካዳሚ የጀመረው ዴላፕ ለማንችስተር ሲቲ ከ18 አመት በታች ቡድን ከነ ኮል ፓልመር፣ ሞርጋን ሮጀር እና ሮሚዮ ላቪያ ጋር ተጫውቷል፡፡

ለዋናው የሲቲ ቡድንም ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር አመት በኢፕስዊች ታውን በግሉ ድንቅ ጊዜን ያሳለፈው ሊያም ዴላፕ በማንችስተር ሲቲ ቤት የጋርዲዮላ ረዳት የነበሩት ኢንዞ ማሬስካ በተያዘው የዝውወር መስኮት ወደ ቼልሲ ወስደውታል፡፡

ባሳለፈባቸው አካዳሚዎች ፈጣን እና ጨራሻ እንደሆነ የሚነገርለት የ22 አመቱ ዴላፕ በምዕራብ ለንደን አዲሱ 9 ቁጥር ለባሽ ኮከብ ሆኖም ተከስቷል፡፡

ሲካሄድ የቆየው የፑል እና የከረንቡላ ውድድር ፍጻሜውን አገኘየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ቢሊያርድ  ኮሚቴ ከማሙሽ  ጌም ዞን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፑል እና የከረንቡላ ስፖርት  ሻም...
20/07/2025

ሲካሄድ የቆየው የፑል እና የከረንቡላ ውድድር ፍጻሜውን አገኘ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሊያርድ ኮሚቴ ከማሙሽ ጌም ዞን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፑል እና የከረንቡላ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ

አዝናኝ እና አሳታፊ የሆነው የፑል ስፖርት ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ማሙሽ ጌም ዞን ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረቡት የኮሚቴው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ አሰፋ የውድድሩ ሻንፒዮና ስፓርተኞች ወደ ፊት በሚዘጋጁ ታላላቅ ውድድሮች ተሳታፊ እንደሚሆኑ አሳውቀዋል።

ስፓርቱን ለማጠናከር እና በህበረተስቡ ዘንድ መነቃቃት ለመፍጠር ከአጋሮች በትብብር የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት አቶ ተሾመ ዘንድሮ የተካሄደው ውድድር በተሳታፊ በተመልካች እና በተደራሽነት ስኬታማ መሆኑን ገልጸዋል

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የከረንቡላ ስፓርት ውድድር ወንድወስን መንገሻ ሻምፒዮና ሲሆን መኮንን ገብረመድህን እና ይቤ ዘርጋው 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል

ወጣቶች ድንቅ ብቃታቸቅን ባሳዩበት የፑል ውድድር ሰለሞን መሀመድ(ጃኪ) 1ኛ፣አሽረቃ ታጁ 2ኛ ፀጋዬ አግዛ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል

ለውድድሩም አሸናፊዎች የማበረታች የገንዘብና የትጥቅ ሽልማት ከሜዳ ስፓርት ቤትና እና ከማሙሽ ጌምዞን ተበርክቶላቸዋል።

ንብ አናቢ... በ1985 ዓ.ም በአዲስአበባ ስታዲየም ውድድር ሲደረግ በሚስማር ተራ ባለው ጎል ውስጥ በመረቡ ጥግ በኩል የሆነ ጥቁር ነገር ተከምሯል።በረኛው መረቡን በእግሩ ነካ ሲያደርግ መን...
20/07/2025

ንብ አናቢ...

በ1985 ዓ.ም በአዲስአበባ ስታዲየም ውድድር ሲደረግ በሚስማር ተራ ባለው ጎል ውስጥ በመረቡ ጥግ በኩል የሆነ ጥቁር ነገር ተከምሯል።

በረኛው መረቡን በእግሩ ነካ ሲያደርግ መንጋ ንብ ኖሮ የተወሰኑት ተንቀሳቅሰው ሲመጡ በረኛው ሸሽቶ ሮጠ።

በዚህ ጊዜ የበረኛውን መውጣት ያየ ከርቀት ሲመታ ገባ። በረኛው ዳኛውን ጠራና አሳየው። ዳኛውም የንቦቹን መንቀሳቀስ አይቶ መሸሽ ገባ።

ንቦቹ ቀይና ቢጫ ካርድ አያውቁም። ዳኛም ካገኙ ያባርራሉ። ንቦቹ ከውስጥ ካልወጡ በረኛው ጎሉ ውስጥ ድርሽ አልልም አለ። ጨዋታው ቆመ።

ንቦቹ ከአከባቢው መነሳት ስላለባቸው ከተመልካቹ መሃል በድምፅ ማጉያ ንብ የማነብ ችሎታ ያለው ሰው ተጠራና መጣ።

"ትልቅ ዱላ ስጡኝ" አለ። የተነገረው ንቦቹን ዱላው ላይ አድርጎ ከስታዲየም ውጭ ባለው ዛፍ ላይ እንዲያሰፍራቸው ነበር።

ምን እንዳደረጋቸው ባይታወቅም ንቦቹ ተነስተው ሰውየውን ከማባረራቸው ባሻገር ስታዲየሙ ውስጥ ወደ ካታንጋ ግር ብለው ሲሄዱ በዚያ ያለው ተመልካች በሙሉ እግሬ አውጪኝ ብሎ ጥሎ ጠፋ።

ጥይት ቢተኮስ እንኳን እንደዚህ አይሮጡም።

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ(ሊብሮ), የእግርኳስ ወጎች,2006 ዓ.ም 3ተኛ እትም!

ኤልሳቤጥ አማረ ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አመጣች*****************በናጄሪያ፣ አቢኩታ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመ...
20/07/2025

ኤልሳቤጥ አማረ ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አመጣች
*****************

በናጄሪያ፣ አቢኩታ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻው ቀን ውሎ በ800ሜ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ኤልሳቤጥ አማረ 1ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች።

በሻምፒዮና የመጨረሻው ቀን ውሎ በ800ሜ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች የፍፃሜ ውድድር የተካፈለው ሲሳይ ዓለቤ ደግሞ 3ኛ በመውጣት ለሀገሩ የነሐስ ሜዳልያ አምጥቷል።

ዳርዊን ኑኔዝ በዛሬው ጨዋታ ሀትሪክ ለመስራት 14 ደቂቃዎች ብቻ ነበር የፈጀበት❤️የመጀመሪያውን ጎል - 6ተኛው ደቂቃ ላይሁለተኛውን ጎል - 12ተኛው ደቂቃ ላይሶስተኛውን ጎል - 20ኛው ደቂ...
20/07/2025

ዳርዊን ኑኔዝ በዛሬው ጨዋታ ሀትሪክ ለመስራት 14 ደቂቃዎች ብቻ ነበር የፈጀበት❤️

የመጀመሪያውን ጎል - 6ተኛው ደቂቃ ላይ
ሁለተኛውን ጎል - 12ተኛው ደቂቃ ላይ
ሶስተኛውን ጎል - 20ኛው ደቂቃ ላይ

ኢትዮ ሊቨርፑል ደጋፊዎች ማህበር

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #በናይጄሪያ አቢኩታ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና  በአምስተኛው እና መዝጊያው ቀን በ5,000 ሜትር ሴቶች  እርምጃ ከ18...
20/07/2025

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #በናይጄሪያ አቢኩታ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአምስተኛው እና መዝጊያው ቀን በ5,000 ሜትር ሴቶች እርምጃ ከ18 ዓመት በታች የፍፃሜ ውድድር፦

በሚገርም ብቃት እና ብቻዋን ውድድሩን በመምራት የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራች አስገኝታለች

ህይወት አምባው 1ኛ 🥇

🇪🇹🇪🇹እንኳን ደስ አለን!

አብዲሳ ፈይሳ በማድሪድ ስፔን በወንዶች 1500 ሜትር እና ንግሥት ጌታቸው በቤልጂየም ሂዩስደን በሴቶች 800 ሜትር አሸንፈዋል።በትላንትናው ዕለት በስፔን ማድሪድ ከተማ በተካሄደው የብር ደረጃ...
20/07/2025

አብዲሳ ፈይሳ በማድሪድ ስፔን በወንዶች 1500 ሜትር እና ንግሥት ጌታቸው በቤልጂየም ሂዩስደን በሴቶች 800 ሜትር አሸንፈዋል።

በትላንትናው ዕለት በስፔን ማድሪድ ከተማ በተካሄደው የብር ደረጃ ያለው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር ውድድር (ሚቲንግ ማድሪድ 2025) ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አብዲሳ ፈይሳ 3፡34.63 በሆነ ሰዓት የወንዶች 1500 ሜትር አሸናፊ ሆኗል፡፡ በማድሪዱ የወንዶች 1500 ሜትር ፉክክር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሞሲሳ ስዩም (3፡35.98) እና ወገኔ አዲሱ (3፡36.36) በቅደም ተከተል ሰባተኛ እና ስምንተኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡

በማድሪድ የሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ላይም ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ነፃነት ደስታ በ4፡08.79 እና ትግስት ግርማ በ4፡09.50 ሰዓት በቅደም ተከተል ሶስተኛ እና አራተኛ ሲወጡ ባዪሴ ቶለሳ በ4፡15.90 ሰዓት አስራ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

በቤልጂየም በተካሄደው የነሐስ ደረጃ ያለው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር የሴቶች 800 ሜትር ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረችው ንግስት ጌታቸው የራሷን ምርጥ ባሻሻለችበት 1፡57.01 የሆነ ሰዓት አሸንፋለች፡፡

በሂዩስደን በወንዶች 1500 ሜትር ውድድር ላይ የተሳተፈው መልኬነህ አዘዘ 3፡36.17 በሆነ ሰዓት አምስተኛ ሲወጣ በወንዶች 5000 ሜትር የተወዳደረው ሀይለማሪያም አማረ በ13፡19.65 ሰዓት አስረኛ ሆኖ ጨርሷል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ወንድ አትሌቶች በማድሪድ እና ሂዩስደን ያደረጉት የ1500 ሜትር የቶኪዮ 2025 የዓለም ሻምፒዮናን ሚኒማ (ዝቅተኛ የሰዓት መስፈርት) የማሟላት ሙከራ ስኬታማ አልነበረም፡፡




20/07/2025

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Team Talk Sport ቲም ቶክ ስፖርት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Team Talk Sport ቲም ቶክ ስፖርት:

Share