Capital

Capital Capital is the longest-established private English newspaper in Ethiopia Capital is the longest established private English newspaper in Ethiopia
(1)

በትግራይ ክልል ውስጥ ከሁለት ዓመታት የእርስ በርስ ግጭት በኋላ፣ በዓለም አቀፍ ላይ የሚስተዋለዉን የወርቅ ዋጋ መናር ተከትሎ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያንቀሳቅስ ሕገ-ወጥ የወርቅ ንግድ ...
15/11/2025

በትግራይ ክልል ውስጥ ከሁለት ዓመታት የእርስ በርስ ግጭት በኋላ፣ በዓለም አቀፍ ላይ የሚስተዋለዉን የወርቅ ዋጋ መናር ተከትሎ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያንቀሳቅስ ሕገ-ወጥ የወርቅ ንግድ መፋፋሙን አዲስ የጋራ ምርመራ አመለከተ።

ምርመራው እንደሚያመለክተው፣ የካናዳው ኩባንያ ኢስት አፍሪካ ሜታልስ ንብረት በሆኑት ማቶ ቡላ እና ዳ ታምቡክ ማዕድን ቦታዎች ላይ ሕገወጥ የማዕድን ማውጣት ተግባር በስፋት እየተፈጸመ ነው።

ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል ከ ቡሮ ኦፍ ኢንቨስቲጌቲቭ ጆርናሊዝም ጋር ባደረጉት ምርመራ መሠረት፣ ሥራ ያልጀመሩና ተደራሽ አይደሉም የተባሉት እነዚህ ቦታዎች ላይ፣ የቀድሞ ወታደሮች እና የቻይና ማዕድን ቆፋሪዎች ስማቸው ያልተገለጸ ባለሀብቶች ድጋፍ አግኝተው ከ2024 መጀመሪያ አንስቶ እስከ 2025 አጋማሽ ድረስ ወርቅ ሲያወጡ ቆይተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://capitalethiopia.com/2025/11/15/tigray/

ባለፉት 33 ዓመታት በዓለም ዙሪያ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በግብርናው ዘርፍ የደረሰው አጠቃላይ ኪሳራ 3.26 ትሪሊዮን ዶላር እንደደረሰ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ...
14/11/2025

ባለፉት 33 ዓመታት በዓለም ዙሪያ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በግብርናው ዘርፍ የደረሰው አጠቃላይ ኪሳራ 3.26 ትሪሊዮን ዶላር እንደደረሰ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አስታወቀ።

እንደ ፋኦ ሪፖርት ከሆነ ይህ ኪሳራ በየዓመቱ በአማካይ $99 ቢሊዮን የሚገመት ሲሆን፣ ይህም ከአለም አቀፉ የግብርና ጠቅላላ ምርት (GDP) አራት በመቶ የሚሆነውን ይይዛል።

"የአደጋዎች በግብርና እና በምግብ ዋስትና ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ 2025" የተሰኘው የፋኦ ሪፖርት ድርቅ፣ ጎርፍ፣ ተባዮች እና የባህር ሙቀት መጨመር የመሳሰሉ አደጋዎች የምግብ ምርትን እና ኑሮን እንዴት እንዳስተጓጎሉ አመልክቷል።

በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ የደረሰ ከባድ ኪሳራ
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ፣ አደጋዎች በአጠቃላይ 4.6 ቢሊዮን ቶን የእህል ምርት፣ 2.8 ቢሊዮን ቶን ፍራፍሬ እና አትክልት እንዲሁም 900 ሚሊዮን ቶን የስጋ እና የወተት ተዋጽኦ አውድመዋል።

ካፒታል ጋዜጣ በተመለከተዉ በዚህ ወሳኝ ሪፖርት ላይ እንደተመላከተዉ ፤እነዚህ ኪሳራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀን ለአንድ ሰው የሚያስፈልገው 320 ኪሎ ካሎሪ ቅናሽ እንዲያሳይ አድርጓል።

እስያ በጎርፍ እና በዐውሎ ነፋስ ከፍተኛ ተጋላጭነት ምክንያት 1.53 ትሪሊዮን ዶላር በማጣት የአለም አቀፉን ኪሳራ 47% የያዘች ሲሆን አፍሪካ ደግሞ በድምሩ 611 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ብታስመዘግብም፣ ከሌሎች ክልሎች በበለጠ በግብርና ጠቅላላ ምርት ላይ 7.4 በመቶ ያህል ደርሶባታል።

ሪፖርቱ መንግስታት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና የግል ዘርፎች የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ወደ አገር አቀፍ የግብርና ፖሊሲዎች በማዋሃድ እና ለዲጂታል መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት በመጨመር የአደጋ ቅነሳ ጥረቶችን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ፍላይዱባይ (FlyDubai) ወደ ሶማሊላንድ ለሚደረጉ በረራዎች የጉዞ መመሪያዎቻቸውን በማዘመን፣ የሶማሊያ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ (ኢ-ቪዛ) መስፈርት በሃርጌሳ እና...
14/11/2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ፍላይዱባይ (FlyDubai) ወደ ሶማሊላንድ ለሚደረጉ በረራዎች የጉዞ መመሪያዎቻቸውን በማዘመን፣ የሶማሊያ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ (ኢ-ቪዛ) መስፈርት በሃርጌሳ እና በበርበራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ እንደማይሠራ በይፋ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀው "የሶማሊያ የኢ-ቪዛ መስፈርቶች ወደ በርበራ ወይም ሃርጌሳ ለሚመጡ ተሳፋሪዎች አይሰራም" በማለት ገልጿል። አየር መንገዱ ወደ ሶማሊላንድ የሚጓዙ ተሳፋሪዎች ሲደርሱ ቪዛ ማግኘት እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቷል።

ፍላይዱባይ በተመሳሳይ የጉዞ ማስጠንቀቂያውን በማሻሻል፣ መንገደኞች በሃርጌሳ እና በበርበራ ሲደርሱ ቪዛ ማግኘት እንደሚችሉ አረጋግጧል። ይህ እርምጃ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA)ን ጨምሮ በርካታ አካላት የሶማሊላንድን የኢሚግሬሽን ቁጥጥር ከሶማሊያ ሥርዓት በመለየት የጉዞ መመሪያዎችን ካወጡ በኋላ የተወሰደ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://capitalethiopia.com/2025/11/14/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%a0%e1%8b%a8%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8d%8d%e1%88%8b%e1%8b%ad%e1%8b%b1%e1%89%a3%e1%8b%ad-%e1%8b%a8/

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፤ በዓለም ላይ ዝቅተኛ ካርቦን የሚያመነጩ የአልሙኒየም ምርቶችን በማምረት ከሚታወቀው ከሩሳል ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ ግዙፍ የአልሙኒየም ማቅለጫ ፋብሪካ ለማ...
14/11/2025

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፤ በዓለም ላይ ዝቅተኛ ካርቦን የሚያመነጩ የአልሙኒየም ምርቶችን በማምረት ከሚታወቀው ከሩሳል ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ ግዙፍ የአልሙኒየም ማቅለጫ ፋብሪካ ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙን አስታወቀ።

ይህ ፕሮጀክት ለመጀመሪያ ምዕራፍ የሚገመተው ወጪ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፣ ፋብሪካው በዓመት 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአልሙኒየም የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ፤ ፋብሪካው በዋናነት ሁለት ተግዳሮቶችን ለመፍታት ታስቦ የተነደፈ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን በዚህ መሰረት :- እያደገ የመጣውን የአገር ውስጥ የአልሙኒየም ፍላጎት ለሟሟላት እና የውጭ ምንዛሪ ወጪ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ የሚሉት ይገኙበታል።

ሁለቱ ተቋማት የፈረሙት ስምምነት እንደሚያሳየው፣ የፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ከ3 እስከ 4 ዓመታት እንደሆነ የሚገመት ሲሆን፣ ፋብሪካውም ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪ እሴት በመፍጠር እስከ 50 ዓመታት ድረስ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

አንድ ቢሊዮን ዶላር ግምት የተሰጠው የመጀመሪያው ምዕራፍ፣ ተነሳሽነቱን ለመደገፍ ፍላጎት ካሳዩ ዕዳ ሰጪዎች 70% የሚሆነው ፋይናንስ እንደሚቀርብለት በሪፖርቱ ተመላክቷል።

የመግባቢያ ሰነዱን ተከትሎ የፕሮጀክቱን ዝግጅት በጋራ ለመቆጣጠር በሁለቱ አካላት መካከል የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሟል። የፕሮጀክቱን ወቅታዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቦታ መለየት እና ሁሉን አቀፍ የአዋጭነት ጥናትን የመሰሉ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጀመራቸውም ታውቋል።

የጤና ሚኒስቴር ተከናዉኗል ባለዉ የዘረመል ምርመራ፣ ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ ከተማ መከሰቱ የተገለጸው የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Viru...
14/11/2025

የጤና ሚኒስቴር ተከናዉኗል ባለዉ የዘረመል ምርመራ፣ ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ ከተማ መከሰቱ የተገለጸው የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ተደርጓል ባለዉ ምርመራ ከቀናት በፊት በበሽታዉ መጠርጣራቸዉን ካሳወቀዉ 8 ሰዎች ዉጪ አዲስ በበሽታው የተጠረጠረ አለመገኘቱን ገልጿል።

ቫይረሱን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከር የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ክልሉ መላኩን ጠቁሟል።

በምርመራው መሰረት፣ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘው የቫይረስ ዝርያ ከዚህ በፊት በሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለው መሆኑ ታውቋል።

ይህን ተከትሎ በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ተቋቁሞ የምላሽ ስራዎች እየተስተባበሩ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

በ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የሚመራዉ የአለም ጤና ድርጅት በጂንካ አካባቢ የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመከላከል 300 ሺህ ዶላር ከድርጅቱ አስቸኳይ ፈንድ በኩል መልቀቃቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።

   | ዳሸን ባንክ እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት ያለውን የ"ዳሸን ዕድል" ጨዋታ ይፋ አደረገ ዳሸን ባንክ በዳሸን ሱፐር አፕ ላይ ብቻ የሚገኝ አዲስ የዲጂታል ሽልማት እና የጨዋታ ተሞክሮ ...
14/11/2025

| ዳሸን ባንክ እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት ያለውን የ"ዳሸን ዕድል" ጨዋታ ይፋ አደረገ

ዳሸን ባንክ በዳሸን ሱፐር አፕ ላይ ብቻ የሚገኝ አዲስ የዲጂታል ሽልማት እና የጨዋታ ተሞክሮ የሆነውን ዳሸን እድልን በይፋ መጀመሩን አሳወቀ።

ይህበአይነቱ ልዩ የሆነው የሱፐር አፕ እድል እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው ሲሆን፣ ይህም የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች የባንኩን ዘመናዊ ዲጂታል አገልግሎቶች በመጠቀም አስደሳች ሽልማቶችን የማግኘት ልዩ እድል የሚሰጣቸው ነው።

የዳሸን ዕድል ሎተሪ ደንበኞች እንዲሳተፉ እና እንዲያሸንፉ በአርኪ መንገድ የቀረበ ጨዋታ ነው፡፡ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች በዕለት ተዕለት በሚያደርጓቸው ዲጂታል ግብይቶች፣ (ማለትም የገንዘብ ዝውውሮችን በማድረግ፣ ሱፐር አፕን በማውረድ እና በመጠቀም፣ ከሌሎች ባንኮች ገንዘብ በመቀበል፣ የንግድ ክፍያዎችን በመፈፀም፣ የአየር ሰዓት በመሙላት እንዲሁም ሌሎች በመተግበሪያው ውስጥ የሚገኙትን የቻት ባንኪንግና የበጀት አገልግሎቶችን) እና ሌሎች አገልግሎቶችን በመጠቀም በቀላሉ "ሳንቲሞችን" መሰብሰብ ይችላሉ፡፡

ደንበኞች ከዚያም የሰበሰቡትን ሳንቲሞች በመጠቀም ስልኮቻቸውን "በማወዛወዝ" እና ከሞባይል ዳታ ፓኬጆች አንስቶ ከ100 ብር እስከ 100,000 ብር የሚደርሱ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ (e-money) ሽልማቶችን፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ 23 እና ኤ 54፣ አይፎን 16 ሞዴል ስልኮችን እንዲሁም አዲስ የቢዋይዲ መኪና ሽልማቶችን ማሸነፍ ይችላሉ።

ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳሸን ባንክ በዳሸን ዕድል የማስተዋወቅ ዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ ሽልማቶችን ለአሸናፊዎች መስጠት ጀምሯል። ይህ የማስተዋወቅ ዘመቻ የዳሸንን ደንበኞች ለመሸለም ብቻ የቀረበ ሳይሆን ደንበኞች በዳሸን ሱፐር መተግበሪያ ላይ የቀረቡትን በርካታ የአገልግሎት አይነቶች እንዲጠቀሙ ለማነሳሳት የተነደፈ ነው።

ዛሬውኑ ይህን አስደሳች ጨዋታ ይቀላቀሉ!

የዳሸን ሱፐር መተግበሪያን ያውርዱ፣ ሳንቲሞችን ማግኘት ይጀምሩ፣ እና በዳሸን ባንክ የዲጂታል ባንክ ሕይወትን የሚቀይሩ ሽልማቶችን ለማሸነፍ እድልዎን ይጠቀሙ።

የዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ መተግበሪያ ያውርዱ 👇 https://www.dashensuperapp.com/download

14/11/2025

| በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ

📍ሳር ቤት ቫቲካን

🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)

👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር

🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል

👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር

#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት

* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251901211153
https://t.me/temeraman2018

13/11/2025

ህንድ በኢትዮጵያ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ ትኩረት አደረገች
በደቡብ እስያ ትልቁን የግንባታ ቴክኖሎጂ የንግድ ትርዒት የሚያስተዋውቀው የኤክስኮን 2025 (Excon 2025) መድረክ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ መካሄዱ ተገልጿል።

13/11/2025

ከ27 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ውስጥ 60 በመቶ ሴቶች የሆኑበት እናት ባንክ፣ የሥርዓተ ፆታ ቦንድ ልጀምር ነዉ አለ
በ11 ባለራዕይ ሴቶች የተመሠረተው እናት ባንክ፣ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የመጀመሪያውን በግል ዘርፍ የሚወጣ 'የሥርዓተ ፆታ ቦንድ' (Gender Bond) ለገበያ ለማቅረብ ጥናት መጀመሩን አስታውቋል።

https://www.youtube.com/watch?v=_Qybby7kgxQ
13/11/2025

https://www.youtube.com/watch?v=_Qybby7kgxQ

የኢትዮጵያ የተለያዩ ምርቶች ወደ ዉጪ የሚልኩ ላኪዎች የዓመቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ግብ ለማሳካት እክል እየፈጠረ ያለውን የአገር ውስጥ የግብርና ምርቶች ዋጋ መናር ለመግታት መንግሥት በ...

ሴቶችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በልዩ ሁኔታ የተመሠረተው እናት ባንክ፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የመጀመሪያውን በግል ዘርፍ የሚወጣ 'የሥርዓተ ፆታ ቦንድ' (Gender ...
13/11/2025

ሴቶችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በልዩ ሁኔታ የተመሠረተው እናት ባንክ፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የመጀመሪያውን በግል ዘርፍ የሚወጣ 'የሥርዓተ ፆታ ቦንድ' (Gender Bond) ለገበያ ለማቅረብ ጥናት መጀመሩን አስታውቋል።

ይህንን አዲስ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መሣሪያ ለመጠቀም የሚያስችለውን ጥናት ከትራንዛክሽን አማካሪው አይ ካፒታል ኢንስቲትዩት ኃ.የተ.የግ.ማ. ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

የቦንዱ ዋና ዓላማ እስካሁን ድረስ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት ያላገኙትን በሴቶች ባለቤትነት የተያዙ ወይም በሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች፣ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችና አርሶ አደሮችን በአመቺ ብድር ተደራሽ ማድረግ ነው።

ይህ እርምጃ ባንኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአካታችነት (Financial Inclusion) የያዘውን ዕቅድ ለመደገፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

የእናት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ አንዳርጌ እንደገለጹት፣ ባንኩ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ቁልፍ ተጫዋች ለመሆን የሚያስችሉ ዝግጅቶችን እያደረገ ሲሆን፣ ባለስልጣኑ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በህዝብ የተያዙ አክሲዮኖችን መዝግቦ ለማጠናቀቅ ከአይ ካፒታል ኢንስቲትዩት ጋር በመስራት ላይ ይገኛል።

ባንኩ፣ ከ11 ባለራዕይ ሴቶች በመቋቋሙ ላለፉት 12 ዓመታት አሳይቷል በተባለዉ ዕድገት ተከትሎ፣ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ቁጥር 27 ሺህ 136 የደረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን አስታውቋል።

ባንኩ በዛሬዉ ዕለት በሰጠዉ መግለጫ ፤ በቅርቡም የብሔራዊ ባንክን የብር 5 ቢሊዮን የተከፈለ ካፒታል መስፈርት ለመሙላት ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።

እናት ባንክ የሥርዓተ ፆታ ቦንዱን አስመልክቶ የሚያስፈልጉ ጥናቶችን በአስቸኳይ በማጠናቀቅ ለብሔራዊ ባንክና ለካፒታል ገበያ ባለስልጣን እንደሚያቀርብና ዝርዝር መረጃውን እና የሽያጭ መጀመሪያ ቀኑን ፈቃድ እንዳገኘ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

13/11/2025

በኢትዮጵያ የሚገኙት የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ኒፖን እና ዓለም አቀፉ አጋሩ ጄሲቢ (JCB) በመጪዎቹ ጊዜያት 500 የከባድ መሣሪያ ኦፕሬተሮችን ለማሰልጠን እቅድ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል።

Address

Bole Behind Rwanda Embassy
Addis Ababa
P.O.BOX95CODE1110

Telephone

+251116183253

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Capital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Capital:

Share