04/02/2020
ገና የኮሮና ቫይረስ ጉዳይ ሳይሰማ በሚሰራበት ሆስፒታል ይህን አስደንገጭ ወረረረሽኝ በመገንዘብ ለማሥጠንቀቅ የሞከረው ዶክተር በፖሊስ አማካኝነት አፉን እንዲዘጋና ምንም እንዳይል ቢታዘዝም ዛሬ ላይ ከሆስፒታል አልጋ ላይ እንደተጋደመ ታሪኩን ሲያጋራ ቻይናዉን "ጀግናችን" እያሉት ነው፡፡
*****
ዶክተር ሊ ይባላል ገና በወርሃ ታህሳስ በሚሰራበት ሆሰፒታል ዉስጥ 7 የቫይረሱ ምልከት ሚታይባቸው ሰዎች ሲያጋጥሙት በ2003 ተከስቶ ከነበረው ሳርስ እየተባለ የሚጠራው ቫይረስ እንደሚሆን በመገመት ለዶክተር ወዳጆቹ ጥኝቃቄ ያደርጉ ዘንድ መለእክት ላከላቸው ፡፡ ያጋጠመው ቫይረስ ግን አደገኛው ኮሮና ቫይረስ ነበር
*****
ይሁን እንጂ ከቀናት በኋላ ፖሊሶች መጥተው የሀሰት መረጃ ከማሰራጨት እንዲታቀብ አስጠንቅቀው ወረቀት አስፈረሙት፡፡
ከሳምንተ በኋላ በኮሮና ቫይረስ መያዟን ያለወቀው ሌላስትን የግላኮማ ህክምና እየሰጣት ቆየ፤፡
*****
ዌቦ በተባለ ማህበራዊ ድረገጽ ላይ ሂደቱን አብራርቶ ሲቀርብ የዉሃን ከተማ ባለስልጣኖች ይቅርታ አድርግልን ቢሉትም ነገሩ ግን የረፈደ ነበር
****
ከጥር 10 ጀሞሮ ሃይለኛ ሳል በማግስቱ ትኩሳት እያለ በመጨረሻም ሆስፒታል ገባ፡፡ ቤተሰቦቹ በተመሳሳይ ምልክት ወደ ሆስፒታል ተከተሉት፡፡ ከዚህ በኋላ ቻይና በጥር 20 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ይፋ አደረገች፡፡
*****
‘የጤና ተቋም ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆንም እንደ ዶክተር ሊ ያሉ ሚሊዮኖችን እንፈልጋለን’ የሚሉ ቻይናውያንም ዶክተሩን ጅግናችን እያሉት ይገኛሉ፡፡