29/06/2025
⚡️ካኒባሊዝም በዶሮ እርባታ ውስጥ
ሀ.ካኒባሊዝም ምንድነው ?
ለ.እንዴት ይከሰታል ?
ሐ.እንዴትስ መከላከል ይቻላል?
📌ሀ. ካኒባሊዝም ማለት በአንድ የዶሮ እርባታ ውስጥ ባልታሰበ ሰአት ዶሮዎቹን እርስ በእርስ እንዲነካከሱ የሚያደርግ አመል ሲሆን በተጨማሪም እርስ በእርስ በቁም ስልቅጥ ተደራርጎ እስከመበላላት የሚያደርግ እና ይህ ሲከሰት ዶሮዎቹ ሰይጣን የገባባቸው እስኪመስል ድረስ ባህሪያቸውን አውሬ እና ቅብዝብዝ የሚያደርግ በየትኛውም ፋርም ውስጥ ሊከሰት የሚችል ለባለቤቱ ግራ የሚያጋባ ክስተት ነው።
📌ለ. ከኒባሊዝም ምንድን ነው? በሽታ አይባልም : ጭንቀት ልንለው እንችላለን
በብዛት የሚከሰተው በማኔጅመንት ክፍተት ሲሆን: አንድ ዶሮ በሚጨንቃት ጊዜ አጠገቧ ያለችውን ዶሮ ላባ መንቀል ትጀምራለች ወይም የጓደኛዋን አናቷ ላይ ያለውን ኩክኒ በመንከስ ልክ እንደደማ ካኒባሊዝም የሚባለው ይከሰታል: በቃ ሰላም የነበሩት ዶሮዎች የደማውን ዶሮ በቁም ጥሩ ምግብ ያደርጉታል: በዚህም አያበቃም አንዱን የበሉበት አፋቸው ላይ ደም ስለሚቀር እርስ በእርስ መበላላት ይቀጥላሉ። በይበልጥ ከኋላ ከማህፀናቸው አካባቢ ነው የደማውን ዶሮ የሚተገትጉት።
ይህንን ሁኔታ ቶሎ ማቆም ካልተቻለ ኪሳራው ቀላል አይባልም።
📌ሐ. መነሻ ምክንያቶች እና መፍትሄ
1. የተመጣጠነ ምግብ እጥረት
ዶሮ ኦምኒቨረስ ፍጡር ናት : ይህ ማለት ህይወት ያለው ነገር እንደተጨማሪ ምግብ ይመገባሉ: ልቅ እርባታ ላይ ትላትል የሚፈልጉት ለዛ ነው። እርባታው ዝግ ከሆነ ከመኖ ይዘት ውስጥ የግድ የአጥንት እና የደም ንጥረ ነገር ያስፈልጋቸዋል።
የፋይበር እና የፖሮቲን እጥረት ዶሮዎችን አግሬሲቭ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል: በተለይ የአሚኖ አሲድ እጥረት ዶሮ ላባ እንድትበላ ያደርጋታል: የወደቀ ላባ መብላት ትጀምራለች ከዛ የጎደኞቾ መንቀል ትቀጥላለች።
ስለዚህ የሚመገቡት መኖ ኒውትሪሽኑን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
2. ሙቀት
የሙቀት መጠን መጨመር ዶሮዎች ላይ ጭንቀት ይፈጥራል: የዶሮዎቹ ቤት ያለው የሙቀት መጠን የዶሮዎችን እድሜ ባመከለ መልኩ ሙቀቱ እየቀነሰ መምጣት አለበት።
ያደጉ የዶሮዎች ቤት በቂ አየር እና ንፋስ የሚገባበት በሽቦ የተዘጋ ክፍተት እንዲኖረው ይመከራል።
3.ከመጠን ያለፈ ብርሃን ወይንም ጨረር
የዶሮ ቤት ውስጥ ያለው አምፖል ከ40 ዋት ማለፍ የለበትም: 12 ሳምንት እና ከዛ በላይ እድሜ ላላቸው ዶሮዎች ከ 15 - 25 ዋት አምፖል ከመመገቢያው እና ከመጠጫው በላይ ይጠቀሙ።
4. የቦታ መጣበብ
የቦታ ጥበት ችግር ካለ ክፍተት ለማግኘት መነካከስ አይቀርም በመነካከስ ውስጥ አንዱ ከደማ አይለቁትም: ያለው ቦታ የዶሮዎቹን ቁጥር ያማከለ መሆን አለበታ: ካልሆነ ባሎት ግቢ ውስጥ መልቀቅ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
5. በመሃል የተጎዱ ወይንም የቆሰሉ ዶሮዎች መኖር
ቁስል ያለው ዶሮ ካኒባሊዝም ያስነሳል: ቁስሉ እስኪድን መለየት ግድ ነው። ካልህነ ግን ጥሩ ምግብ ነው የሚያደርጉት።
6. የተለያየ እድሜ ወይንም የተለያየ ከለር ያለቸውን ዶሮዎች አንድ ላይ ማድረግ
አዲስን ዶሮ/ አነስ ያለን ዶሮ/ ከለሩ የተለየን ዶሮ ማሳደድ እና መንከስ የዶሮ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። ዶሮዎች በዕድሜ በከለር እና በዝርያ ለይቶ ማኔጅ ማድረግ ካኒባሊዝም እንዳይከሰት ያደርጋል።
7. ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ዘገምተኛ የሆኑ ዶሮዎች
ብሮይለርስ ወይንም የስጋ ዶሮዎች ለካነባሊዝም ተጋላጭ ናቸው :ምክንያቱም በዘመናዊ የማዳቀል ምርምር ውስጥ በአጭር ጊዜ እንዲያድጉ ስለሚደረጉ በአጭር ጊዜ ውስ የሚኖራቸው ክብደት የመተንፈስ ችግር እና ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል : 45 ቀን ካለፋቸው ደግም ጭንቀቱ ይጨምራል ከዛም አጠገቡ ያለውን መጎንተል ይጀምራል። ከዛም ካኒባሊዝም ይቀጥላል
📌ማስታወሻ:- አፍ መቆረጡና አለመቆረጡ ከካኒባሊዝም ጋር አይያያዝም ከላይ የተጠቀሱት እንጂ።
The Agri-Lancer