Ethiopia Today

Ethiopia Today Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopia Today, Media/News Company, Addis Ababa.

 የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በውስን ተሳታፊዎች ብቻ እየተከበረ ይገኛል። በበአሉ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተ...
03/10/2020



የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በውስን ተሳታፊዎች ብቻ እየተከበረ ይገኛል። በበአሉ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

PHOTO : EBC

 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,916 የላብራቶሪ ምርመራ 890 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 247 ሰዎች አገግመዋ...
02/10/2020



በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,916 የላብራቶሪ ምርመራ 890 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 247 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 76,988 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,208 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,677 ደርሷል።

የኬሚካል ርጭት በማድረግ ላይ የነበረች አውሮፕላን ተከሰከሰች !በወረባቦ ወረዳ ለተከሰተው አንበጣ መንጋ የኬሚካል ርጭት በማድረግ ላይ የነበረች አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ምክንያት 014 ቀበ...
02/10/2020

የኬሚካል ርጭት በማድረግ ላይ የነበረች አውሮፕላን ተከሰከሰች !

በወረባቦ ወረዳ ለተከሰተው አንበጣ መንጋ የኬሚካል ርጭት በማድረግ ላይ የነበረች አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ምክንያት 014 ቀበሌ ልዩ ስፍራው 'ፍራንጉል' በተባለ ቦታ ተከሰከሰች።

አውሮፕላኗን የሚያበረው ፖይለት በህይወት የተረፈ ሲሆን ሰመራ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

ምንጭ፦ የወረባቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን

ሲኒማ ቤቶች ከመስከረም 29 ጀምሮ ይከፈታሉ!በኮቪድ-19 ምክንያት ለ7 ወራት ተዘግተው የቆዩት ሲኒማ ቤቶች አስፈላጊውን የመከላከያ እርምጃዎች ተግባራዊ በማድረግ ሊከፍቱ እየተዘጋጁ መሆኑን '...
02/10/2020

ሲኒማ ቤቶች ከመስከረም 29 ጀምሮ ይከፈታሉ!

በኮቪድ-19 ምክንያት ለ7 ወራት ተዘግተው የቆዩት ሲኒማ ቤቶች አስፈላጊውን የመከላከያ እርምጃዎች ተግባራዊ በማድረግ ሊከፍቱ እየተዘጋጁ መሆኑን 'ባላገሩ ቴሌቪዥን' ዘግቧል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠው የፊልም ፕሮዲዩሰሮች ማህበር ሲኒማ ቤቶች በመዘጋታቸው ሳቢያ ከ40 ያላነሱ አዳዲስ ፊልሞች ለእይታ ሳይቀርቡ እንደቀሩ አሳውቋል።

በዚህም ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ኪሰራ በዘርፉ ላይ እንዳጋጠመ ገልጿል።

በተጨማሪም ዘርፉ ከእንቅስቃሴ ውጭ በነበረበት ወቅት በዚህ ስራ ህይወታቸውን የመሰረቱ ከ5,000 ያላነሱ ዜጎች ከስራ ውጭ ስለመሆናቸው ተነስቷል።

የሲኒማ ቤቶችን ስራ ዳግም ለማስጀመር ከጤና ሚኒስቴር እና ከEPHI ጋር 3 ወራት የፈጀ ምክክር እና የደህንነት መመሪያዎችን የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል።

ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑ ሲኒማ ቤቶች ዝግጁነታቸውን በሚመለከት በቅርቡ የቅኝት ስራ የሚሰራ ሲሆን የጥንቃቄ መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቻ ወደ ስራ እንደሚገቡ ተገልጿል።

"ተማሪዎች ከጥቅምት 9 ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት ዝግጅት ማድረግ አለባቸው" - አቶ ማሄ ቦዳ (የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)የደቡብ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ  ኃላፊ አቶ ማሄ ...
02/10/2020

"ተማሪዎች ከጥቅምት 9 ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት ዝግጅት ማድረግ አለባቸው" - አቶ ማሄ ቦዳ (የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)

የደቡብ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ፈተና #በክልል ደረጃ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የቢሮ ኃላፊው የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ. ም እንደሚሰጥ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ አስታውሰዋል።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል መሠረት ባደረገ መልክ በኦንላይ ስለሚሆን ከኩረጃ የፀዳ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ማሄ ቦዳ ተማሪዎች ከጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት ዝግጅታቸውን ማድረግ አለባቸው ሲሉ ማሳስበባቸውን ከቢሮው የ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Ethiopia today

 2ኛው ኢሬቻ ፎረም አባገዳዎች፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣...
02/10/2020



2ኛው ኢሬቻ ፎረም አባገዳዎች፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳውና ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

Ethiopia today

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share