Ethio-Online

Ethio-Online Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio-Online, Media/News Company, Olompiya, Addis Ababa.

አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም /የአማራው ፈተና/
17/02/2022

አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም /የአማራው ፈተና/

ethio-online.comበወለጋ ከፍተኛ የዘር ፍጅትና ማፅዳት እየተካሄደ ነው በብዙ መቶዎች ሞተዋል ንብረታቸው ተቀምቷል፡፡ በብዙ ሺዎች ተሠደው አጎራባች ከተሞች ገብተዋል፡፡ ከ7ሺህ በላይ የሚሆኑ ....

26/11/2021

በአዲስ አበባ ራስ እምሩ የኢንዳስትሪ መንደር የእሳት አደጋ ተከሰተ

ኅዳር 17 ቀን 2014 ዓም፡- በአዲስ አበባ በተለምዶ ራስ እምሩ ሜዳ አካባቢ ማምሻውን የእሳት አደጋ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዋች ለኢትዮ ኦንላይን አስታወቁ፡፡

የእሳት አደጋው የተከሰተው በአካባቢው በሚገኘው የኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ መሆኑን ለዘጋቢያችን ገልፀዋል፡፡

የእሳት አደጋው መንስዔ ለጊዜው አለመታወቁን የገለፁልን የዓይን እማኞች፡ በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ምንም አይነት ምልከታ እንደሌላቸው ገልፀው፡ ንብረት ግን የምርት መሣሪያዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ እሳት አደጋ እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲ አደጋውን ሳይባባስ ለመቆጣጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች የተገነባላቸውን ህንጻ ተረከቡበአዲስ አበባ በቀጨኔ አካባቢ ከዕድሜ ብዛት ሊፈርስ በመቃረቡ ምክንያት የነዋሪዎቹን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል የነበረን ከእን...
26/11/2021

ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች የተገነባላቸውን ህንጻ ተረከቡ

በአዲስ አበባ በቀጨኔ አካባቢ ከዕድሜ ብዛት ሊፈርስ በመቃረቡ ምክንያት የነዋሪዎቹን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል የነበረን ከእንጨትና ጭቃ የተሰሩ ቤቶች፡ ሃይንከን ኢትዮጵያ አፍርሶ በመስራት ለነዋሪዎቹ መልሶ አስረክቧል።

ቤቶቹ አምስት አባወራዎችን ከእነ 42 ቤተሰቦቻቸው የያዙ ሲሆን፤ በውስጡ 5 ካሬ በማይሞላ ቤት ውስጥ ስድስት ቤተሰባቸውን ይዘው የሚኖሩ እናትንም ያካተተ ነበር።

ወ/ሮ ታዛ ትርፉ እንደገለፁት ከቦታ ጥበት የተነሳ ሁለት ልጆቻቸውን አልጋ ስር ያስተኙ ነበር ።

"አሁን ልጆቼ ከአልጋ ስር ወጥተው አልጋ ላይ ሊተኙልኝ ነው" ያሉት ወ/ሮ ታዛ በዛሬው እለት 64 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሳሎን፣ ሁለት መኝታ ቤት፣ መጸዳጃ ቤትና ኩሽና ያለው ቤት ተረክበዋል።

ሃይንከን ባለፈው ዓመት ከረዩ ሰፈር የገነባቸውን 53 ደረጃቸውን የጠበቁ መኖርያ ቤቶች ለነዋሪዎች ማስረከቡ ይታወሳል።

የካምፓኒው የውጭ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍቃዱ በሻህ እንደገለፁት፤ ሃይንከን በመጪው አመት ጨርቆስ አካባቢ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ የሚኖሩ ወገኖችን ለመርዳት አቅዷል።

ሰውየው አገሬን አለ፤ ምዕራቡ ዓለም- አሻንጉሊቴን                                                                                         ...
15/11/2021

ሰውየው አገሬን አለ፤ ምዕራቡ ዓለም- አሻንጉሊቴን

ማርቆስ ረታ
ዛሬ አውሮፓ ሕብረትና አሜሪካ የሕወሐት ደጋፊ ሆነው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ለመወንጀል ውሸት ፈብራኪ ዘጋቢዎቻቸውን አሰማርተዋል። በሕወሓት ቀስቃሽነት በተነሳው ጦርነትም፣ ዶ/ር ዐቢይ የሚመሩት የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲያጠቃ “ተው” ሲሉ፣ ሲጠቃ ደግሞ “ተደራደሩ” ይላሉ። ግን ለምን!? አሰላለፋቸውን ለምን ቀየሩ? ቢያንስ ሁለት ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል። አንዱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በባይደን መቀየሩ ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱም ትራምፕ አንድ የአገር መሪ ቅድሚያ ለዜጋው መስጠት እንደሚገባው የሚያምኑና የሚሰብኩም ነበሩ። ስለ አፍሪካ ጸያፍ መናገራቸው፣ በግድባችን ላይም በእብሪት መደንፋታቸው ቢታወቅም፣ ‹‹ቅድሚያ ለራስ አገር›› የሚለው እና “አሜሪካ ትቅደም” በሚለው መፈክር የተገለጸው አቋማቸው ፍትሐዊ ነበር ለማለት ይቻላል።

መግቢያ፤ ምነው የምዕራቡ ዓለም ሚድያ እብዝቶ ጠመደን!? ያን ሁሉ የሀሰት ዘገ...

"ከሰራን ለምነን የማናገኘውን ሁሉ ሰርተን እናገኘዋለን" ዙምራ ኑሩ - የአውራ አምባ ማኅበረሰብ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ሊያከብር ነው!"እኛ ወደ ሥራ ከገባን ሥራውም ወደ እኛ ይመጣል፡ ...
22/10/2021

"ከሰራን ለምነን የማናገኘውን ሁሉ ሰርተን እናገኘዋለን" ዙምራ ኑሩ

- የአውራ አምባ ማኅበረሰብ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ሊያከብር ነው!

"እኛ ወደ ሥራ ከገባን ሥራውም ወደ እኛ ይመጣል፡ ከዜሮ ጀምሮ የትም ይደረሳል" የሚለው ማኅበረሰባዊ እሳቤያቸው መሆኑን የአውራምባ ማኅበረሰብ መሥራች የክብር ዶ/ር ዙምራ ኑሩ ተናገሩ፡፡

ቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ ከአርትስ ቴሌቭዥን ጋር በመተባበር በሜክሲኮ ካምፖስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአውራምባ ማኅበረሰብ መሥራች የክብር ዶክተር ዙምራ የሕይወት ተሞክሯቸውን ለተማሪዎች ገልጸዋል፡፡

የኔ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት፡ እናቴ ናት፡ ቀን በግብርና አባቴን ታግዛለች፡ምሽት የቤት ውስጥ ሥራ ትቀጥላለች ያሉት የክብር ዶ/ር ዙምራ፡ እናቴ ያልተሳካላት ቀን ግን ከአባቴ ወቀሳና አንዳንዴም ዱላ ነው ሲቀርብላት የነበረው፡፡

ይህ ኹኔታ ለመኅበራዊ ሕይወት እሳቤዬ መነሻዬ ሆኗል፡፡ እናቴ የመጀመሪያዋ መምህርቴ ናት ብለዋል፡፡

የሰው ልጅ አንድ የቤተሰብ አካል መሆኑ እና የሰው ልጅ እኩልነት፡ የፆታ እኩልነት፡ የሥራ ክቡርነት፡ የተቸገሩ ሰዎችን መደገፍ የሚሉ እሳቤዎችን ከቤተሰቤ ለጥቆ ከልጅነቴ ጀምሮ በአካባቢዬ ከተመለከትኩት ማኅበራዊ ኢ-ፍትሐዊነት ሳስብ እና ስጠይቅ በመኖር የዛሬውን የማኅበረሰብ እሳቤ ለማዳበር የቻልኩት ብለዋል፡፡

ከ1964 ዓም ጀምሮ በማኅበረሰባችን ግጭትና ፀብ ገጥሞን ወደ ወረዳ ፖሊስ፡ ወደ ፍርድ ቤት ሄደን አናውቅም፡፡ ችግሮቻችንን በውይይት ነው የምንፈታው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የዙምራ ባለቤት ወ/ሮ እናነይ ክብረት በበኩላቸው ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሰማሩ ነው የምናደርገው፡ በቤት ውስጥ አቅማቸውን ያማከለ የሥራ ተሳትፎም ያደርጋሉ፡፡

ልጆች ሲያጠፉ በማኀበረሰባችን ይመከራሉ፡ ጥፋቱ ከተደጋገመ ልጆች ከቤተሰብ ጋር በጋራ አብረው ባወጡት የቤተሰብ ሕግ ከስሜት በራቀ ትንሽ ቁንጥጫ ሊኖር ይችላል ብለዋል፡፡
የአውራምባው ማሕበረሰብ መስራች ክቡር ዶ/ር ዙምራ ኑሩ፡ በቅድስተ ማሪያም ዩኒቨርሲቲ ተጋብዘው ስለ ሰላም፣ ስለመደጋገፍ፣ በጋራ ስለመበልፀግ፣ ስለ ስራ ባሕልና ስለ ትውልድ ቀረጻ ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፡ የዩኒቨርስቲው መምህራን እና ተማሪዎች ታድመዋል።

ሃይንከን እና የጀምስ ቦንዱ አዲሱ ፊልም ምን አገናኛቸው?ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ከቦንድ ፊልም ጋር የአጋርነት ስምምነት ያለው ሃይንከን አዲሱን No Time To Die የተሰኘውን ፊልም...
07/10/2021

ሃይንከን እና የጀምስ ቦንዱ አዲሱ ፊልም ምን አገናኛቸው?

ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ከቦንድ ፊልም ጋር የአጋርነት ስምምነት ያለው ሃይንከን አዲሱን No Time To Die የተሰኘውን ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ዛሬ ያቀርባል።

ፊልሙ ዛሬ ምሽት ላይ ለሃይንከን ቤተሰቦች የሚ ቀርበው በሸራተን አዲስ የቀይ ምንጣፍ ዝግጅት ነው። በዝግጅቱ ላይ ታዋቂ ግለሰቦች እና የምርቱ ተጠቃሚዎች ይታደማሉ።

ሃይንከን ይህን የሚያደርገው የፊልም አፍቃሪያኑን ፍላጎት ለማርካት እና ከደምበኞቹ እና ከቤተሰቦቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሆነ የካምፓኒው የውጭ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍቃዱ በሻህ ተናግረዋል።

የዚህ ዓይነት አዳዲስ ክስተቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት የሚታወቀው ሃይንከን ከዚህ ቀደምም ሮናልዲንሆ ጉቾን፣ ማካሌሌን እና የሻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ ማስመጣቱ ይታወቃል።

‹‹የመንግሥትን ኃላፊነት ለቀቅኩ ማለት፣ ሀገሬንና ህዝቤን ጥዬ እሄዳለሁ ማለት አይደለም›› ሚ/ር ፊልሰን አብዶላሂ- ለአገልግሎት ወደ እናንተ ነው የምመጣው፤ ከእናተው ጎን ነኝ!የተክለ ኃይማ...
03/10/2021

‹‹የመንግሥትን ኃላፊነት ለቀቅኩ ማለት፣ ሀገሬንና ህዝቤን ጥዬ እሄዳለሁ ማለት አይደለም›› ሚ/ር ፊልሰን አብዶላሂ

- ለአገልግሎት ወደ እናንተ ነው የምመጣው፤ ከእናተው ጎን ነኝ!

የተክለ ኃይማኖት ሠፈር አብሮ አደግ በጎ አድራጎት መርጃ ማኅበር ከአካባቢው ያሰባሰባቸውን ረጂ የሌላቸው አቅመ ደካማ ወገኖች ራሳቸውን እንዲችሉ ለመደገፍ በሚያደርገው ጥረት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ለማድረግ ግለሰቦችና ተቋማት ቃል ገቡ፡፡

የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚንስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዶላሂ፣ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ እና በበጎ አድራጎቱ የሚታወቀው ዮኒ ቬጋስ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ ለመፈለግ በጋራ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

እሁድ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ ተክለ ኃይማኖት ሠፈር በተከናወነው የቁርስ መርሃ ግብር ላይ፣ ለመቶ ሃምሳ ተማሪዎች የሚሆን የደብተር፣ መጽሐፍት፣ እስክርቢቶ፣ እስራስ እና የአልባሳት ሥጦታዎችን የሜሪጆይ ኢትዮጵያ መሥራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ያበረከቱ ሲሆን፣ የቁርስ ምገባውን መርሃ ግብር ወጪ የሸፈነው ደግሞ በጎ አድራጊው ዮኒ ቬጋስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምገባ መርሃ ግብሩ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የቀረቡት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚንስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዶላሂ፣ ‹‹ማዕድ ማካፈል ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን እንደ አርአያ ሆነው ያስጀመሩት በጎ ሥራ ነው፤ ከወገን ጋር አብሮ ማዕድ መካፈል ለመነጋገር፣ ለመተሳሰብና ለመረዳዳት ዕድል የሚሰጥ ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹እኔ ከዚህ ቀጥሎ መንግሥታዊ ኃላፊነቴን አስረክባለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ›› ያሉት ወ/ሮ ፊልሰን፣ ‹‹ነገር ግን ኃላፊነቴን ለማስረክበው ሰው ይህን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ይዞ እንዲሄድ የበኩሌን አደርጋለሁ፡፡ የመንግሥት ሥራ ለቀቅኩ እንጂ፣ ሀገሬንና ህዝቤን ጥዬ አልሄድም፤ ለአገልግሎት ወደ እናንተ ነው የምመጣው፤ ከእናተው ጎን ነኝ፤ ስለዚህ ሥራን መፍጠር በዋናነት ከእናንተ ነው የምንጠብቀው፤ እኛ ደግሞ ድጋፉን እናመጣለን፤ ሳንለያይ በርትተን እንሰራለን፤ ሀገራችንን ካለችበት ውጥረትና ድህነት ተጋግዘን እናወጣለን›› በማለት በቀጣይ ስለሚሰማሩበት የአገልግሎት መስክ ጥቁምታ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ዛሬ በዋናነት ላገኛችሁ የፈለግኩት፣ እዚህ ውስጥ የሥራ አቅም ያላቸው ጠንካራ ወጣቶችን ክብርት ሚንስትርም ማየት አለባቸው ብዬ ስለማምን ነው›› ያለው በጎ አድራጊው ዮኒ ቬጋስ፣ ‹‹በቀጣይም የሥራ አቅም ያለው ወጣት እንዴት ቢደገፍ ነው ወደ ሥራ የሚገባው፣ አረጋዊያን እንዴት መረዳት አለባቸው፣ ማድረግ የሚገባንስ ምንድን ነው የሚለውን ነገር ከክብርት ሚንስትር ወ/ሮ ፊልሰን ጋር እየተነጋገርንበት ነው›› ብሏል፡፡

የሜሪጆይ ኢትዮጵያ መሥራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በበኩላቸው፣ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ለአንድ መቶ ሃምሳ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት ማቅረባቸውን ገልጸው፤ ይህን ያደረግነው ልጆች በአግባቡ የትምህርት ዕድል ካገኙ ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ማህበረሰባቸውን መለወጥ የሚያስችላቸውን አቅም ስለሚያጎለብቱ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እሁድ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ ተክለ ኃይማኖት ሠፈር የተከናወነውን የቁርስ መርሃ ግብር ከበጎ አድራጎት መርጃ ማኅበሩ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሜሪጆይ ኢትዮጵያ እና በበጎ አድራጎቱ የሚታወቀው ዮኒ ቬጋስ መሆናቸውን የተክለ ኃይማኖት ሠፈር አብሮ አደግ በጎ አድራጎት መርጃ ማኅበር አስተባባሪ አቶ ስለሺ ገልጸዋል፡፡

በማኅበሩ ከተሰባሰቡ አቅመ ደካማ ወገኖች ውስጥ በጥቂት ድጋፍ ወደ ሥራ ሊሰማሩ የሚችሉ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ዲፕሎማ ያላቸው ይገኙበታል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ጤና ጣቢያ ታድሶ የተሟላ ግልጋሎት መስጠት ጀመረበአቃቂ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወርቁ ሠፈር በሚባለው አካባቢ የሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ካቶሊክ ጤና ጣቢያ ሙሉ እድሳት ተደ...
08/09/2021

ቅዱስ ገብርኤል ጤና ጣቢያ ታድሶ የተሟላ ግልጋሎት መስጠት ጀመረ

በአቃቂ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወርቁ ሠፈር በሚባለው አካባቢ የሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ካቶሊክ ጤና ጣቢያ ሙሉ እድሳት ተደርጎለት የተሟላ የ24 ሰዓት የጤና አገልግሎት በዛሬው እለት መስጠት ጀምሯል፡፡ ለጤና ጣቢያው ሙሉ እድሳት 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጎ ያስገነባው ሃይንከን ኢትዮጵያ/ ሃይንከን አፍሪካ ፋውንዴሽን ነው፡፡

የቅዱስ ገብርኤል ካቶሊክ ጤና ጣቢያ ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ኃይሉ እንደገለጹት፣ ጤና ጣቢያው በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ባለቤትነት ከመልካም ወንድሞች ሥራ ማኅበርና ከሌሎች ለጋሽ አካላት በሚያገኘው የፋይናንስ ድጋፍ የሚተዳደር ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም በመሆኑ፣ አገልግሎቱን ለማግኘት ከአቃቂ/ቃሊቲ፣ ከቂሊንጦ፣ ከሳሪስ፣ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ከቦሌ ቡልቡላ የሚመጡ ከ 31 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች አሉ ብለዋል፡፡

የቅዱስ ገብርኤል ካቶሊክ ጤና ጣቢያ 10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና የህንፃው እድሳት መጠናቀቅን በማስመልከት ትላንት ጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በተከናወነ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንትና የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል፣ በህንፃው እድሳት ግንባታ ላይ የተሳተፈውን ሃይንከን ኢትዮጵያን ለበጎ አድራጎቱ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

‹‹ከ10 ዓመት በፊት ራስ ደስታ ሆስፒታል አቅራቢያ ያለውን ማኅበረሰብ ለማገልገል ጤና ጣቢያ ለመገንባት የመሬት ጥያቄ ብናቀርብም ቶሎ ምላሽ አላገኘንም ነበር›› ያሉት ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ፣ ‹‹ፕሮጀግቱ እንዳይጓተት ሲባል ወደ አየር ጤና ወለቴ አካባቢ ለመገንባት የአካባቢውን መስተዳደር የመሬት ጥያቄ አቀረብን እዚያም ምላሹ ተጓትቶ ሳይሳካ ቀርቷል›› ብለዋል፡፡

በመጨረሻም፣ የጤና ጣቢያ የልማት መሬት ጥያቄውን ለአቃቂ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቅርበን በቶሎ ምላሽ በማግኘታችን በተለምዶ ወርቁ ሰፈር የሚባለው አካባቢ 6 ሺህ ካሬ ሜትር ተሰጥቶን ጤና ጣቢያውን ገንብተን ለአገልግሎት አብቅተናል፤ ለዚህም የአካባቢውን ማኅበረሰብ እና መስተዳድሩን እናመሰግናለን ብለዋል- ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል፡፡

የሃይንከን ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ሰስቴኔብሊቲ ማኔጀር አቶ ፍቃዱ በሻህ እንደተናገሩት፣ የእናቶችና ህፃናት ክፍል (ማዋለጃ ክፍል) እየተሰነጠቀና ውኃ እያስገባ ለአገልግሎት ስላስቸገረ እንደገና የዲዛይን ማሻሻያ ተደርጎ ከሥር መሰረት ወጥቶለት እና ምሶሶዎች እንዲቆሙ ተደርጎ ነው ዳግም በ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የተገነባው፡፡

ይህ ጤና ጣቢያ ይበልጡኑ በእናቶችና ህፃናት ላይ አተኩሮ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በነፃ ስለሚያገለግል ይህ ለእኛ በጣም የሚያስደስተን ተግባር ነው ብለዋል- አቶ ፍቃዱ በሻህ፡፡

ሃይንከን ኢትዮጵያ/ ሃይንከን አፍሪካ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ የሚያግዝ ሲሆን፣ በተለይ በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ብዙ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በቅርቡም ለቂሊንጦ ጤና ጣቢያ የአምፑላንስ እና ለእናቶችና ህፃናት የህክምና ክፍል የሚያገለግሉ በርካታ ቁሳቁሶችን አበርክቷል፡፡

ሃይንከን ኢትዮጵያ/ ሃይንከን አፍሪካ ፋውንዴሽን በመላ ዓለም ያሉ የሃይንከን ድርጅቶች ያዋጡትን ገንዘብ አፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ በተለይ በእናቶች ጤና እና ‹‹ዋሽ›› በሚለው ፕሮጀክት ንጽህና ላይ አተኩሮ ማኅበረሰብ አቀፍ ግልጋሎት ላይ እንደሚሰራ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ “ዴልታ” የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መኖሩ በመረጋገጡ የጥንቃቄ እርምጃዎች ይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ _________________የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ...
07/09/2021

በኢትዮጵያ “ዴልታ” የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መኖሩ በመረጋገጡ የጥንቃቄ እርምጃዎች ይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ
_________________

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በጋራ በኮቪድ አሁናዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ዴልታ የተሰኘው ዝርያ በስርጭት ፍጥነት ቀደም ብሎ ከነበረው አልፋ ከተሰኘው ዝርያ በ2 እጥፍ እንደሚበልጥ የጠቆሙት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ብቻ 8300 ሰዎች በኮሮና መያዛቸውንና 118 ሰዎች መሞታቸውን በዚህም ሳምንታዊ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ 20 ፐርሰንት መድረሱን አማካይ የሞት ምጣኔም በቀን 16 ሰዎች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመከላከያ መንገዶች ጎን ለጎን የተሳሳቱ አመለካከቶችን በመተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራቱ የተረጋገጠውንና ላለመያዝ የሚከላከለውን፣ ከተያዙ በኋላም ፅኑ ህሙም የመሆን እድልን የሚቀንሰውን ክትባት እንዲወስድ፤ በዝግ ቦታዎች የሚደረጉ መሰባሰቦችን መቀነስ እንደሚያስፈልግና አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም ጥንቃቄያቸውን መጨመር እንደሚገባቸው መክረዋል፡፡
አያይዘውም በተሰሩ በርካታ ስራዎች የክትባት ተደራሽነት እየሰፋ በመሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎች መከተብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በበኩላቸው አዲሱ ዝርያ መኖሩ በቅርብ ቢረጋገጥም ስርጭቱ እንደቆየ የሚያሳዩ ጥናቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

በርካታ ሃገራት በ3ኛና 4ኛ የኮቪድ ስርጭት ማዕበል እየተመቱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘውም የዛሬውን የጳጉሜን 2 የአገልጋይት ቀን አስመልክተው የጤና ባለሙያዎችና የጤና እንክብካቤ ሠራተኞቻችን የኮሮና ወረርሽኝን ለመቋቋምና ህዝባቸንን ከከፋ ስቃይና ህልፈተ ህይወት ለመታደግ ሙያቸውን እና የማይተካ ህይወታቸውን ጭምር አሳልፈው በመስጠት ሌት ተቀን ከህዝብ ጎን በመቆም፣ ከቫይረሱ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው አገልግለዋል እንደዚሁም ሌሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች ሳይቋረጡ በማስቀጠል ረገድም ጉልህ እና የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረከቱ በመሆናቸው በአገልጋይነት ቀን ምስጋና እና እውቅና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በሰደድ እሳት የወደመ ደን ለመተካት የአንኮበር ወረዳ እና ዋሊያ ቢራ በጋራ እየሰሩ ነው!- የወፍ ዋሻ ደን ብሔራዊ ፓርክ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ነው!- ድምፃዊ ካሥማሠ የችግኝ ተከላ መር...
30/08/2021

በሰደድ እሳት የወደመ ደን ለመተካት የአንኮበር ወረዳ እና ዋሊያ ቢራ በጋራ እየሰሩ ነው!

- የወፍ ዋሻ ደን ብሔራዊ ፓርክ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ነው!
- ድምፃዊ ካሥማሠ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ተሳታፊ ነበር!

በአማራ ክልል የአንኮበር ወረዳ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ጽ/ፈት ቤት አስተባባሪት እና በዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር ድጋፍ አቅራቢነት በወረዳው በመጋቢት ወር በሰደድ እሳት የወደሙ የደን ሃብቶችን መልሶ ለመተካት በትብብር እየተሰራ ነው፡፡

በአንኮበር ወረዳ ዘጎ ቀበሌ የወፍ ዋሻ ደን በተሰኘ አካባቢ በሰደድ እሳት የወደሙ የደን ሃብቶችን መልሶ ለመተካት የችግኝ ተከላ ሥራ በዛሬው (ሰኞ ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም) እለትም በአካባቢው ነዋሪዎች እየተከናወነ ነው፡፡ ለችግኝ ተከላው የሚውሉ ከ2500 በላይ የአገር በቀል ዛፎችን ችግኝ ያቀረበው ዋሊያ ቢራ ሲሆን፣ ችግኙ በአግባቡ እንዲጸድቅ ለመንከባከብ የሚያስችልና የአካባቢውን ተራራማ መልክዓ ምድር ተደራሽ የሚያደርጉ (መኪና ስለማይገባ) ሁለት ሞተር ሳይክል ለወረዳው ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ጽ/ፈት ቤት አበርክቷል፡፡

ቅዳሜ ነሐሴ 22 እና እሁድ ነሐሴ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በዋሊያ ቢራ ሠራተኞች፣ በአካባቢው ማኅበረሰብ፣ በወረዳው ኃላፊዎች እና በበጎ ፈቃደኞች በተከናወነ አካባቢውን የመንከባከብና የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በርካታ ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ሀገር በቀል ዛፎች ተተክለዋል፡፡ የዋሊያ ቢራ የክብር አምባሳደር ድምፃዊ ካሥማሠ በአንኮበር ተገኝቶ ችግኞችን ተክሏል፡፡

የአንኮበር ወረዳ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ኃላፊ አቶ ይሻው ታምሬ እንደገለጹት፣ የወፍ ዋሻ ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ ስምንት ሺህ ሄክታር መሬት በደን የተሸፈን ጥብቅ ሥፍራ ሲሆን፣ ባለፈው መጋቢት ወር በሰደድ እሳት የተቃጠለው 235 ሄክታር መሬት ነው፤ ከዚህ ውስጥ 90 ሄክታር መሬት መልሶ መልማት ያለበት ነው ያሉት ኃላፊው፣ እስከ አሁን 11 ሄክታር በክልሉ አካባቢ ነዋሪዎችና በተባባሪ አካላት መልሶ ማልማት ተችሏል፡፡ 79 ሄክታር የደን ሥፍራው ደግሞ በራሱ ጊዜ መልሶ ያገግማል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር ሲኒየር ብራንድ ማኔጀር ወ/ሪት ፋይዳ ዘውዱ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን ‹‹ዋሊያ ቢራ ከተፈጥሮ መንከባከብ ጋር የተገናኙ እንቅስቃሴዎችን እንደ መርህ ይዞ ስለሚሳተፍ ነው ወደ አንኮበር የመጣነው ብለዋል፡፡

‹‹ይህን ድጋፍ ያደረግነው ምርቶቻችን ሁሉ የተፈጥሮ ጥገኞች በመሆናቸው ነው፤ አብረን በጋራ ስንሰራ የሕብረተሰቡን ልማት እናነቃቃለን፤ እኛም በውጤቱ እንጠቀማለን፡፡›› ያሉት ወ/ሪት ፋይዳ፣ ‹‹እንደሚታወቀው የዋሊያ ቢራ መሪ-ቃል ‹አንድ ላይ ወደ ላይ› የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉን ነገር የምናደርገው ከሕብረተሰቡ ጋር በአንድነት ነው፡፡ ስንተባበርና ስንተጋገዝ ኃይላችን ከፍ ይላል›› ብለዋል፡፡

የአንኮበር ወዳጆች ስብስብ አስተባባሪ አቶ ጌታ መኮንን በአማራ ክልል የአንኮበር ወረዳ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ጽ/ፈት እና በዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር መካከል የደን ልማት ትብብርና ድጋፍ እንዲደረግ ያስተባበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡

የወፍ ዋሻ ደን በአማራ ክልል አሉ ከሚባሉ ጥቂት ጥብቅ የደን ሃብት አንዱ ነው ያሉት አቶ ጌታ መኮንን፣ በሰደድ እሳት የወደመውን ደን ለመከላከል የአካባቢውን ማኅበረሰብ፣ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት እና የበጎ ፈቃድ ደጋፊዎችን በጉልበትም በገንዘብም በማስተባበርና በማስተዋወቅ ሰደድ እሳቱ እንዲጠፋ አደረግን፤ ክረምቱ ሲገባም ከተለያዩ አካላት ድጋፍ በማሰባሰብ የወደመውን ደን ለመተካት ባለፈው ወር ብቻ ወደ 19 ሺህ ችግኝ እንዲተከል አድርገናል ብለዋል፡፡

አሁን ደግሞ ዋሊያ ቢራ ባደረገው ድጋፍና ትብብር ነው ችግኝ እየተከልን የምንገኘው ብለዋል፡፡ ወደ ፊት ይሄ ሥፍራ ብሔራዊ ፓርክ እንዲሆን በአማራ ክልል ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር፣ የዋሊያ ቢራ ብራንድ መጠሪያ የሆነው ብርቅዬ የዱር እንስሳ (ዋሊያ) በሚገኝበት በሰሜን ተራራች ፓርክ ተገኝቶ ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ቂሊንጦ፣ በበደሌ፣ በሐረር ተፈጥሮን የማልማት፣ ዛፎችን የመትከል መርሃ ግብር፣ በየዓመቱ የሚያከናውነው የማኅበረሰብ ልማት ተግባራት ናቸው፡፡

"የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለአገልግሎት በማዋል የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ እየሰራሁ ነው" የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ለዜጎች የሥራ ዕድልን ...
25/08/2021

"የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለአገልግሎት በማዋል የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ እየሰራሁ ነው" የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ለዜጎች የሥራ ዕድልን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ፡ ኢትዮጵያ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ዘላቂ ምጣኔ ሃብታዊ እድገትን ለምረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከዓለም አቀፉ የልማት ድርጅት (UNIDO) ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2013 ዓም በደብረዘይት ከተማ ፒራሚድ ሆቴልና ሪዞልት እያከናወነ ባለው የምክክር መድረክ፡ በኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ሥራ የገቡ የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን አስተዋውቋል፡፡

በመድረኩ ላይ እንደተገለፀው፡ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 85 በመቶ ለአገልግሎት ብቁ ሲሆኑ፡ በሲዳማ ክልል 70 በመቶ፡ እንዲሁም በትግራይ ክልል የሚገኘው የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በክልሉ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከ50 በመቶ በላይ ማድረስ አለመቻሉ በመድረኩ ተወስቷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

አንጣሬ (አንጣሪያ)፣ ትኩረት ያጣው ጉምቱ ምግብበአማሪኛ አንጣሬ (Antare) ወይም አንጣሪያ ይባላል፡፡ በኦሮሚፋ ማራሬ (marare) ይባላል፡፡  በእኛ አገር አረም እንደሆነ ይታወቃል፡፡እ...
27/07/2021

አንጣሬ (አንጣሪያ)፣ ትኩረት ያጣው ጉምቱ ምግብ

በአማሪኛ አንጣሬ (Antare) ወይም አንጣሪያ ይባላል፡፡ በኦሮሚፋ ማራሬ (marare) ይባላል፡፡ በእኛ አገር አረም እንደሆነ ይታወቃል፡፡

እነ ደምል ተከታይ ባዘጋጁት የጥናት ሪፖርት (መጽሐፍ) ላይ የሚከተለው መረጃ ይገኛል፡፡ ከ ባህር ወለል በላይ ከ ዜሮ እስከ 2,35ዐ ሜ.ባ.ወ.በ ይበቅላል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሌ፣ ጋሙጎፋ፣ ጎንደር፣ ሐረርጌ፣ ኢሉአባቦር፣ ከፋ፣ ሸዋ፣ ሲዳሞ እና ወሎ ይገኛል፡፡ በየቦታው በተለያየ ቋንቋ ብዙ መጠሪያዎች አሉት፡፡ ከነዚህም በትግሪኛ- መለሔና፣ በአኙዋ-አዲላጌ፣ በአሪ-ሙቃዛ፣ በጋሞ- ቹርቃሌ፣ በከምባታ-አርባግራሶ፣ በኮንሶ-ማራይታ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ የተክሉ ሙሉ ክፍል ወይም ለጋ ቀንበጡ በጋሙጎፋ፣ በተለይም በሰገን ወንዝ ወይናደጋ እና በኮንሶ ደጋ ቦታዎች፣ ባኮ ጋዘር፣ ደቡብ ኦሞ፣ ሰሜን ኦሞ ቆላ፣ ጂንካ እና ጋምቤላ ውስጥ ለምግብነት ይጠቀማሉ፡፡ አመቱን ሙሉ በተለያየ የአገሪቱ ክፍሎች፤ በተለያየ ወቅት ይበቅላል፣ ያብባል፣ ያፈራል ወዘተ፡፡ ይበቅላል በተባለባቸው ቦታዎች በወቅቱ ይገኛል፡፡ ቅጠል እና አገዳውን ጭምር በኬንያ፣ ታንዛንያ እና ኡጋንዳ ይመገቡታል፡፡

መነሻ፣ በአማሪኛ አንጣሬ (Antare)...

Address

Olompiya
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio-Online:

Share