EBC-መዝናኛ

EBC-መዝናኛ Ethiopian Broadcasting Corporation is a 24 hour working public media.

12/10/2025

የኢትዮጵያ አይዶል ጉዞ ጥበብን ፍለጋ በቦንጋ

በቻይና በዩንቨርስቲዎች መካከል የሚደረገው የአውሮፕላን ዲዛይን ፈጠራ ውድድር **********************በቻይና በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚማሩ የአቬሽን ዘርፍ ተማሪዎች ትምህርታ...
12/10/2025

በቻይና በዩንቨርስቲዎች መካከል የሚደረገው የአውሮፕላን ዲዛይን ፈጠራ ውድድር
**********************

በቻይና በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚማሩ የአቬሽን ዘርፍ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በተግባር እና በንድፈ ሐሳብ የቀሰሙትን የአቬሽን ዘርፍ እውቀት ወደ ተግባር አውርደው የዘመናዊ አውሮፕላኖች ዲዛይን በሚታይ መንገድ አዘጋጅተው በውድድር ይፎካከራሉ፡፡

በዚህ አመትም ከ150 ዩንቨርስቲዎች የተወጣጡ ከ4000 በላይ ተማሪዎች የራሳቸውን የአውሮፕላን ዲዛይን ይዘው በምስራቅ ቻይና በምትገኘው ሺጂያንግ ግዛት ተገኝተዋል፡፡

ተማሪዎቹ የሚያቀርቡት የአውሮፕላን ዲዛይን ፈጠራ ምን ያሕል የካርቦን ልቀት አለው፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራ ምን ያህል የበቃ ነው እና ከቻይና የአየር ንብረት ፖሊሲ ጋር አንዴት አብሮ ይጓዛል የሚለው ዋንኛ የውድድሩ መስፈርቶች ናቸው፡፡

በውድድሩ ላይ በርካታ የሐገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎች የሚገኙ ሲሆን የውድድሩ ዓላማ ተማሪዎቹ አሁን ካለው የአቬሽን ዘርፍ ጋር ምን ያህል እየተጓዙ ነው የሚለውን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በሰው አልባ አውሮፕላን እና በአየር ላይ የታክሲ አገልግሎት ከዓለም ቀዳሚ አምራች ለመሆን እሰራች ያለችው ቻይና፤ ብቁ እና የሰለጠኑ ወጣቶችን ለመለየት ውድድሩን እየተጠቀመችበት እንደምትገኝም ተነግሯል፡፡

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

ከበሬ አጥንት የመኪና ፍሬን አካላትን የሚሰራው ስራ ፈጣሪ ወጣት******************የበሬ ስጋን ለምግብነት ከተጠቀምን በኋላ አጥንቱን ወደ ቆሻሻ መጣያ ማስወገድ ወይም ለውሻ መስጠት ...
12/10/2025

ከበሬ አጥንት የመኪና ፍሬን አካላትን የሚሰራው ስራ ፈጣሪ ወጣት
******************

የበሬ ስጋን ለምግብነት ከተጠቀምን በኋላ አጥንቱን ወደ ቆሻሻ መጣያ ማስወገድ ወይም ለውሻ መስጠት የተለመደ ነዉ።

አንድ ወጣት ግን የሚጣለውን የበሬ አጥንት በመጠቀም የሰራው የፈጠራ ስራ ለበርካቶች የስራ አድል ፈጥሯል፡፡

ወጣቱ በሀይሉ ሰቦቃ ይባላል፡፡ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ድግሪ አለው፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአስኬማ ድርጅት መስራች ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ለሰዎች ችግር መፍትሄ መሆን ህልሙ እንነበር ይናገራል፡፡

ወጣቱ የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርቱን መመረቂያ ፕሮጀክት ከአጥንት እና ከወዳደቁ ብረታብረትን በመጠቀም በመስራት ስራ ፈጣሪ ሆኗል።

ወጣቱ የመኪና ፍሬን አካላትን በሀገር ውስጥ ከበሬ አጥንት፣ ከወዳደቁ ብረታብረት እና ሴራሚክ በመስራት ከራሱ አልፎ ለሌሎች የስራ ዕድልን ፈጥሯል።

ተቋሙ የመኪና ፍሬን አካላቶችን ለማምረት የበሬ አጥንቶቹን ከተለያዩ የቄራ ድርጅቶች እና ስጋ ቤቶች የሚሰበሰብ ሲሆን የወዳደቁ ሴራሚክ እና ብረታብረቶችን ከማምረቻ ድርጅቶች እና ሻጮች እንደሚያገኝ ገልጿል።

ለምርቶቹ የሚጠቀሙት የአጥንት ክፍል ዳሌ አካባቢ ያለውን የበሬ ክፍል ሲሆን የአጥንቱን ባህሪ እና ጥንካሬ በማጥናት እንደሚለዩ ተናግሯል።

በወጣቱ የተቋቋመው አስኬማ ድርጅት 268 ሰራተኞችን የያዘ ሲሆን ከ6 ሺህ 400 በላይ ደንበኞች ምርቶቻቸውን እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ገልጿል።

የተቋሙ መስራች ሀይሉ ሰቦቃ እንደሚለው ድርጅቱ ለመንገድ ግንባታ የሚያገለግሉ ማሽነሪዎች መለዋወጫ እቃዎችንም እየሰራ ሲሆን የISO ሰርተፍኬት ባለቤት መሆን ችሏል፡፡

በሔለን ተስፋዬ

አንጋፋዋ የሆሊዉድ ተዋናይት ዳያን ኪተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች********************አሜሪካዊቷ የሆሊዉድ ተዋናይት ዳያን ኪተን በ79 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተገልጿል፡...
12/10/2025

አንጋፋዋ የሆሊዉድ ተዋናይት ዳያን ኪተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
********************

አሜሪካዊቷ የሆሊዉድ ተዋናይት ዳያን ኪተን በ79 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተገልጿል፡፡

የኦስካር አሸናፊዋ ተዋናይት ዳያን ኪተን ቅዳሜ ዕለት በካሊፎርኒያ ህይወቷ ማለፉን ቤተሰቦቿ አረጋግጠዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

በሎስ አንጀለስ የተወለደችው ዳያን ኪተን በ1970ዎቹ "The Godfather" በተሰኘው ፊልም ውስጥ በተጫወተችው ገፀባህሪ ዝነኛ ለመሆን በቅታለች።

ዳያን ኪተን "አኒ ሆል" በተሰኘው ፊልም ላይ ባሳየችው ብቃት እ.አ.አ በ1978 የኦስካር (የምርጥ ተዋናይት አካዳሚ ሽልማት) አሸንፋለች።

ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ በዘለቀው የስራ ዘመኗ በደርዘኖች በሚቆጠሩ ፊልሞች ላይ የተወነች ሲሆን፤ እንደ "The Family Stone"፣ "Because I said So" ፣ "And So It Goes" እና በርካታ የዉዲ አለን ፊልሞች ላይ ተጫውታለች።

ከዚህ ባሻገር ከካሜራው ጀርባ በርካታ ስራዎች ላይ የተሳተፈቸው ዳያን ኪተን፤ እንደ Heaven፣ Unstrung Heroes እና Hanging Up ያሉ ፊልሞችን በዳይሬክተርነት መርታለች።

በሴራን ታደሰ

30ሺ ዶላር የሚጠጋ ዋጋ የወጣበት የዓለማችን ውዱ ላባ ***************9 ግራም የሚመዝነው የወፍ ላባ 46 ሺህ የኒውዚላንድ ዶላር (28 ሺህ 365 የአሜሪካ ዶላር) በጨረታ ተሽጧል።...
12/10/2025

30ሺ ዶላር የሚጠጋ ዋጋ የወጣበት የዓለማችን ውዱ ላባ
***************

9 ግራም የሚመዝነው የወፍ ላባ 46 ሺህ የኒውዚላንድ ዶላር (28 ሺህ 365 የአሜሪካ ዶላር) በጨረታ ተሽጧል።

በዚህም ላባው በይፋ የዓለማችን ውድ ላባ መሆን ችሏል።

ላባው በኒውዚላንድ ውስጥ ብቻ ይኖሩ ከነበሩ እና በ 20ኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ላይ ከጠፉት "ሁያ" ከተሰኙት የወፍ ዝርያዎች የተገኘ ነው።

በመጀመሪያ በጨረታ ወደ 3ሺ ዶላር እንደሚያወጣ የተተመነለት ላባው፤ ከተጠበቀው በላይ በአሥር እጥፍ ዋጋ ማውጣት መቻሉ ተነግሯል።

የኒውዚላንድ የማኦሪ ህዝብ በአንድ ወቅት ለሁያ ወፎች ላባ ጥልቅ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ትርጉም ይሰጣቸው እንደነበርም የኦዲቲሴንትራል ዘገባ አመልክቷል።

ይህ ባህላዊ እሴትም ታዲያ ከወፎቹ መጥፋት ጋር ተዳምሮ ላባው በጣም ያልተለመደ እና ዋጋ ያለው እንዲሆን አድርጓል ነው የተባለው።

በሴራን ታደሰ

11/10/2025
11/10/2025

እሑድ ቤት
እሑድ በኢቲቪ መዝናኛ

#እሑድቤት #ሙሉዓለምታደሰ #ሚካኤልታምሬ #የእልፍኝገበታ #የእልፍኝጨዋታ #ዚያራ #ቤትለእንግዳ #ብታዩት #ሄሎኢትዮጵያ #ደርሶመልስ

11/10/2025

ባለቅኔው ገጣሚ ሙሉጌታ ተስፋዬ ሲታወስ
******
ባለቅኔው አያ ሙሌ ከግጥም መድብሎቹ ባሻገር፤ በርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን የደረሰ የተባ ብዕር ባለቤት ነበር።

https://youtu.be/-w0ERG2A77o

#አያሙሌ #ገጣሚ

10/10/2025

መልህቅ ዓርማዬ ቀይ ባሕር ቤቴ፦ኢትዮጵያ የባሕር በር ያስፈልጋታል የሚል ትውልድ ተነስቷል
****
እሑድ በ7:00 በእሑድ ቤት
በኢቲቪ መዝናኛ

ፈረንሣዊው ቲክቶከር በሰራው ቪዲዮ ለእስር ተዳረገ******* በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ መርፌ የወጋ በማስመሰል ሰዎችን ፕራንክ ያደረገው ፈረንሳዊ ቲክቶከር የስድስት ወር እስራት መቀጣቱ ተገለጸ።...
10/10/2025

ፈረንሣዊው ቲክቶከር በሰራው ቪዲዮ ለእስር ተዳረገ
*******

በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ መርፌ የወጋ በማስመሰል ሰዎችን ፕራንክ ያደረገው ፈረንሳዊ ቲክቶከር የስድስት ወር እስራት መቀጣቱ ተገለጸ።

ሰዎችን ለድንጋጤ ሲዳርግ የሚያሳዩ ቪዲዮን በለቀቀ ማግስት ከፍተኛ ዕይታን ሊያገኝ ችሏል፡፡

ቲክቶከሩ ሰዎችን ለመጉዳት በማሰብ ሳይሆን እውቅናን ለማግኘት አስቤ ነው ሲል መናገሩን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ሆኖም የሀገሪቷ አቃቤ ሕግ አንዳንድ ሰዎች በፕራንኩ በጣም ስለተጎዱ በአእምሮ ጤና መዛባት ሆስፒታል መተኛታቸውን አንስተዋል።

ጠበቃው ለደንበኛው ምህረት እንዲደረግለት ፍርድ ቤቱን ቢጠይቅም፤ ዳኛው የቲክቶከሩ ድርጊት ወንጀል ነው በማለት በ6 ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስነውበታል።

በሜሮን ንብረት

ቻይና በአግባቡ የተጠቀመችባቸው የቱሪዝም ፀጋዎች ******ቻይና በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላ ናት ይሏታል የሚያውቋት። በአንድ በኩል ቱባ ባህል አላት፤ ከ56 በላይ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦቿን...
10/10/2025

ቻይና በአግባቡ የተጠቀመችባቸው የቱሪዝም ፀጋዎች
******

ቻይና በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላ ናት ይሏታል የሚያውቋት። በአንድ በኩል ቱባ ባህል አላት፤ ከ56 በላይ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦቿን ቋንቋ፣ አኗኗር፣ አመጋገብ እና የውዝዋዜ ስርዓትዋን ጠብቃ እስካሁን አለች። ታሪኳም በቅጡ ተሰንዷል።

በሌላ በኩል ደግሞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተለያዩ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ዓለምን እየቀየረች ነው።

1.4 ቢሊየን ሕዝብ ያላት ቻይና የራሷን ቋንቋ መጠቀሟም ሌላኛው የጥንካሬዋ መገለጫ ነው።

ቻይና በሯን ከፍታ በተደራጀ መልኩ ባስቀምጠቻቸው ባለሙያዎችዋ አማካኝነት ሀገሯን ለዓለም ታስታውቃለች።

ቴክኖሎጂዋን እና ምቹ መሰረተ ልማቶቿን በመጠቀምም የቱሪዝም ገቢዋን እያሳደገችም ይገኛል።

ቻይና እ.አ.አ. በ2019 65.7 ሚሊዮን ቱሪስቶችን አስተናግዳለች። ከዚያን በኋላ ግን የኮቪድ መምጣትን ተከትሎ የቱሪስቶች ቁጥር እጅግ አሽቆልቆሎ ነበር።

አሁን ላይ የቱሪስቶች ቁጥር ማንሰራራት እያሳየ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ። በ2025 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ 35 ሚሊዮን ቱሪስቶች ቻይናን ጎብኝተዋል።

ቻይና በ2025 ከጎብኚዎች በአጠቃላይ 3.9 ትሪሊየን ዶላር ወደኢኮኖሚዋ ፈሰስ እንደሚሆን የዓለም የቱሪዝም ሴክተር ካውንስል ትንበያውን አስቀምጧል።

ጎብኝዎች በቀላሉ ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ በማመቻቸት፣ የመስህብ ስፍራዎቿን በማደስ፣ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት፣ ምቹ የሆነ የአከፋፈል ስርዓትን በመዘርጋት እና የሰለጠኑ አስጎብኚዎችን ማዘጋጀት ቻይና የቱሪዝም ዘርፉን በአግባቡ እየተጠቀመችበትም ነው።

በነፃነት ክንፈ

10/10/2025

10ኛ ምዕራፍ የጠቅላላ እውቀት እሑድ 9:30 በኢቲቪ የልጆች ዓለም ይጀምራል
#የልጆችዓለም

Address

Churchil Road
Addis Ababa

Telephone

+251115172539

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EBC-መዝናኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EBC-መዝናኛ:

Share

Our Story

Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television,Radio and Website.