Omotic Media Network

Omotic Media Network Omotic Society Future to Bulid the Largest Media Center by Omotic Language. Omotic languages are group of languages spoken in southwestern Ethiopia.

The Ge'ez script is used to write some of the Omotic languages, the Latin script for some others. They are fairly agglutinative and have complex tonal systems (for example, theBench language). The languages have around 6.2 million speakers. The group is generally classified as belonging to the Afroasiatic language family, but this is disputed by some.

06/01/2025
06/01/2025

እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ!

የኦሞ ባንክ የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ የባንኩ ሠራተኞች በሙሉ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ይገልፃሉ፡፡

ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ!

12/08/2024
12/08/2024
25/07/2024
25/07/2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

“እግዚኦ ሚ በዝኁ እለ ይሣቅዩኒ፦አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ ! ” (መዝ. 3፡1)

አባታዊ የማጽናኛ መልእክት

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ እጅግ ብዙ የሚሆኑ ወገኖቻችን በመሞታቸው ታላቅ ኀዘን ተሰምቶናል ። ምንም እንኳ የመከራ ድሀ ባንሆንም ይህ መከራ ለነጋሪውም ለሰሚውም ከባድ መሆኑን እንገነዘባለን ።

ይሁን እንጂ ጭንቀታችን ብዙ ቢሆንም እግዚአብሔር መልካም የምንሰማበትን ዘመን እንደሚያመጣ ተስፋ እናደርጋለን ።

በተለይም ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች በወገኖቻችን መጎዳት ብናዝንም በትንሣኤ ሙታን ስለምናምን የምጽናና በመሆኑ የሞቱት ልጆቻችን ዕረፍተ ነፍስ እንዲያገኙ እየጸለይን፤ የመከራው ገፈት ቀማሽ ለሆኑት የአካባቢው ማኅበረሰብእ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ሁሉም አቅሙ በፈቀደው መጠን እንዲደርስላቸው ስንል አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቦቻቸውና ለሕዝቡ መጽናናትን ይስጥልን፤ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

25/07/2024
25/07/2024
ዛሬ ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከንቾ ሻቻ ጎዝድ ቀበሌ የዘነበዉን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ ባጋጠመዉ ናዳ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተ...
23/07/2024

ዛሬ ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከንቾ ሻቻ ጎዝድ ቀበሌ የዘነበዉን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ ባጋጠመዉ ናዳ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ጥልቅ ሀዘኑን እየገለፀ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።

በቀጣይም ጉዳት የደረሰባቸዉና ከቀያቸዉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ እና ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደረግ ይሆናል።

Address

ጎፋ ማዞርያ
Addis Ababa

Telephone

+251912752653

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Omotic Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Omotic Media Network:

Share