Betachn ቤታችን

Betachn ቤታችን ኑ አብረን ቤታችንን እንገንባ

20/04/2025

እጅግ ብዙ ቁምነገር ያለበት ቆይታ!

 #እንኳን አደርሳችሁ 🙏🙏🙏 #ዉድ የቤታችን ቤተሰቦች አመታትን አሻግሮ ለዚህ ላደረሰን  #እግዚአብሔር ምስጋና እያቀረብን እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰን በማለት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለ...
10/09/2024

#እንኳን አደርሳችሁ 🙏🙏🙏

#ዉድ የቤታችን ቤተሰቦች አመታትን አሻግሮ ለዚህ ላደረሰን #እግዚአብሔር ምስጋና እያቀረብን እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰን በማለት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን። 🙏🙏🙏

መፅሐፍ ቅዱስ "በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ" እንደሚል በሀገር ዉስጥ #እና በባህር ማዶ የምትገኙ ኢትዬጲያውያን እና ኤርትራዉያን እንዲሁን የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ እንኳን ለ2017ዓ.ም የዘመን መለወጫ #አዲስ አመት በሰላም አሸጋገረን 🙏🙏🙏

መጪው #አመት ከእግዚአብሔር ጋር ያልንን ግንኙነት የምናጠናክርበት ፣ ከወዳጆቻችን ጋር ያለንን ሕብረት የምናሳድግበት ፣ ለተቸገሩት የምንደርስበት ቤተሰባችንን የምኝጠብቅበት እንዲሆን Betachn ቤታችን #መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

በአገልግሎት አብራችሁን ያላችሁ በፀሎት እና ጥሩ ሃሳቦችን በመስጠት በተለያየ መልኩ ከጎናችን የቆማችሁ በሙሉ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ። 🙏🙏🙏

በ2017ዓ.ም ለብዙ ቤተሰብ የሚጠቅም ነገር እንደምንሰራ ቃል እየገባን እና በማድረግ ቤተሰብነታችን እንዲቀጥል እየጠየቅን በድጋሜ መልካም አዲስ እንዲሆንልን እንመኛለን። 🙏🙏🙏

09/09/2024

#እንኳን #አደረሳችሁ !!!

#ልዩ የበዓል ፕሮግራም ከተወዳጁ መጋቢ #እና ዘማሪ ደረጀ ሙላቱ እና ቤተሰቦቹ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤተሰቦቹ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

#ብዙ #ጊዜ የተሰማዉን በዜማ በመግለፅ ይታወቃል። ማመስገንም ይሁን መዉቀስ ቢፈልግ ቀዳሚ ምርጫዉ ክራሩን አንስቶ ዜማን መፍጠር ነዉ። ልዩ እንግዳችን

#እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ያልተሰሙ አስገራሚ ምስክርነቶች እና አስቂኝ ገጠመኞች... #ተወዳጁ ዘማሪ ከአገልግሎት ባሻገር በቤት #ዉስጥ እንዴት ይገለፃል.. ?

የበዓል #ቀን #በኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን እና The Christian News - የክርስቲያን ዜና እና Betachn ቤታችን የYoutube ቻናሎቻችን ብቻ ያገኙታል።

#ሙሉ ፕሮግራሙን ለማየት ሊንኩን ይጫኑ https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

 #መልካም  #ልደት ነብይ_ዘኔ... #በጣም የምንወደው፣ አብዝተን የተባረክንበት የኛ ትውልድ ስጦታ የሆነው የእግዚአብሔር ሰው ነብይ ዘነበ ግርማ ዘኔ የተወለደበት ቀን ነው።  #እንኳን ተወለ...
06/09/2024

#መልካም #ልደት ነብይ_ዘኔ...
#በጣም የምንወደው፣ አብዝተን የተባረክንበት የኛ ትውልድ ስጦታ የሆነው የእግዚአብሔር ሰው ነብይ ዘነበ ግርማ ዘኔ የተወለደበት ቀን ነው።

#እንኳን ተወለድክልን ዘመንህ ይባረክ...🙏🙏

በትዳር ላይ ትዳር ሊመሰረቱ የነበሩ ሁለት ጥንዶች በሰርግ ስነስርዓታቸዉ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ👉 በአፋጣኝ ችሎት ጥንዶቹ በ 4 ወራት ቀላል እስራት ተቀጥተዋልበምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጉር...
30/08/2024

በትዳር ላይ ትዳር ሊመሰረቱ የነበሩ ሁለት ጥንዶች በሰርግ ስነስርዓታቸዉ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

👉 በአፋጣኝ ችሎት ጥንዶቹ በ 4 ወራት ቀላል እስራት ተቀጥተዋል

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ለመፈጸም የሰርግ ስነስርዓት ላይ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ግለሰቦቹ ህጋዊ ትዳር እያላቸዉ ፤ ህጋዊ ፍቺ ሳያጠናቅቁ ሌላ ትዳር ለመመስረት ሲሞክሩ ነዉ በቁጥጥር ስር የዋሉት። ሃምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የሰርግ ስነስርዓታቸዉ ላይ የነበሩት ግለሰቦችን ፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ የሰርግ ስነስርዓቱን አግዶ ጥንዶቹን በቁጥጥር ስር አዉሏቸዋል።

የወረዳዉ ፖሊስ አፋጣኝ ምርመራ አድርጎ ድርጊቱን ለአቃቤ ህግ መዝገቡን አቅርቧል። የጉርሱም ወረዳ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደላከዉ መረጃ ከሆነ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በሶስት ቀናት ዉስጥ አፋጣኝ የፍትሕ አሰጣጥ ሂደትን ተከትሎ ዉሳኔ አሰጥቷል።ግለሰቦቹ ጋብቻ ላይ ጋብቻ በመመስረት በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 650 መሰረት ክልከላ የሚጥለዉን በጋብቻ ላይ ጋብቻ ወንጀልን በመጥቀስ ክስ መስርቷል።

ጉዳዩን ሲመለከት የነበረዉ የጉርሱም ወረዳ ፍ/ቤት ሁለቱ ግለሰቦች ህጋዊ ትዳራቸዉን በህጋዊ ፍቺ ሳያፈርሱ ሌላ ትዳር ሊመሰርቱ ሲሉ በቁጥጥር ስር በዋላቸዉ በአራት ወራት ቀላል እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከወረዳዉ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት የተላከለት መረጃ ያመለክታል።

በበረከት ሞገስ

 #ውድ እህቴ ዘሪቱ በዚህ ሰዓት  #እግዚአብሔር አምላክ በመጽናናት ይጎብኝሽ ከማለት ውጪ ምንም ልል አልችልም።ትላንትን ያሻገረሽ እግዚአብሔር ዛሬንም ያበረታሽ እና አቅም ይሆንልሽ ዘንድ እጸ...
05/06/2024

#ውድ እህቴ ዘሪቱ
በዚህ ሰዓት #እግዚአብሔር አምላክ በመጽናናት ይጎብኝሽ ከማለት ውጪ ምንም ልል አልችልም።

ትላንትን ያሻገረሽ እግዚአብሔር ዛሬንም ያበረታሽ እና አቅም ይሆንልሽ ዘንድ እጸልያለሁ።

በBetachn ቤታችን ስም ለአርቲስት ዘሪቱ እና ለቤተሰቦችሽ በሙሉ መፅናናትን እመኛለሁ።

 #እጅግ ልቤን ከነኩኝ ታሪኮች መካከል  #አንዱ ነዉ። ፖስተር ብዙዎች የሚፈሩትን ነገር የራስህን ሕይወት ምስክር አድርገህ ለብዙዎች ሕይወት መለወጥ ምክንያት ስለሆንክ ተባረክ 🙏🙏🙏ዛሬም ብዙ...
26/05/2024

#እጅግ ልቤን ከነኩኝ ታሪኮች መካከል #አንዱ ነዉ። ፖስተር ብዙዎች የሚፈሩትን ነገር የራስህን ሕይወት ምስክር አድርገህ ለብዙዎች ሕይወት መለወጥ ምክንያት ስለሆንክ ተባረክ 🙏🙏🙏

ዛሬም ብዙዎችን እያስተማርክ እና እየገሰፅክ ብዙዎችን እየታደክ በመሆኑ #ጌታ በአንተ በኩል እየሰራ ስላለዉ ስራ አመሰግነዋለሁ 🙏🙏

#ወድ የቤታችን ቤተሰቦች ይህንን #ድንቅ ምስክርነት እንድትማሩበት ግብዣዬ ነዉ።

የዝሙት ሕይወቴን ማንም አያወቅም ነበር ሰዎች መማር ካለባቸው ከእኔ ይማሩ #ድንቅ #ምስክርነት ከዚህ ልምምድ መውጣት ሲያቅተኝ ከጌታ ቤት ባክ አደረኩኝ

#ይህ ድንቅ ምስክርነት ለብዙዎች መለወጫ ስለሚሆን በጥንቃቄ ይመልከቱት ለብዙዎች ሰዎች መማር ካለባቸው ከእኔ ይማሩ አገልጋይ ነኝ ግን አልቻልኩም #ድንቅ #ምስክርነት ከዚህ ልምምድ መው.....

24/05/2024

የማይቀርበት #ቀጠሮ #ወደ #ቤተ #ምህረት

በዚህች አጥቢያ አተኩረን የምንሰራዉ ተተኪ ትዉልድ #ላይ ነዉ። ዘማሪ #እና መጋቢ እንዳለወልደ ጊዮርጊስ

የቤተ ክርስቲያን ተከላና- የመክፈቻ ፕሮግራም ከግንቦት 21-25 / ከእሮብ እስከ ቅዳሜ ከ 10:00 ጀምሮ እሁድ ጠዋት ይከናወናል።

አድራሻ፦ ከቡልጋሪያ ወደ ቄራ ሲወርዱ ስካኒያ አካባቢ የቤተ ምህረት ማስታወቂያ ባለበት 100 ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል።

ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት Comment
በፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል ያድረጉ

ተለቀቀ ...  #ወንጌል ማንኛውንም ነገር ሊያስከፈልሽ ይችላል  #እኔ አገልጋይ ነኝ እያየሽ ግቢበት ነው ያልኳት  #ልዩ የትንሳኤ በዓል ፕሮግራም ከተወዳጁ ዘማሪ እንዳለ እና
05/05/2024

ተለቀቀ ... #ወንጌል ማንኛውንም ነገር ሊያስከፈልሽ ይችላል #እኔ አገልጋይ ነኝ እያየሽ ግቢበት ነው ያልኳት #ልዩ የትንሳኤ በዓል ፕሮግራም ከተወዳጁ ዘማሪ እንዳለ እና

እንኳን አደረሳችሁ! ውድ የቤታችን ቤተሰቦች በዛሬው መሰናዶዓችን የ2016 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከተወዳጁ ዘማሪ እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ ቤተሰብ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ይ.....

03/05/2024

#እንኳን #አደረሳችሁ!!!
#ልዩ የበዓል ፕሮግራም ከተወዳጁ መጋቢ #እና ዘማሪ እንዳለ ወልደጊዮርጊስ እና ቤተሰቦቹ ጋር

#እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ያልተሰሙ አስገራሚ ምስክርነቶች እና አስቂኝ ገጠመኞች... #ተወዳጁ ዘማሪ በቤት #ዉስጥ እንዴት ይገለፃል.. ?

የበዓል ቀን #በኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን እና The Christian News - የክርስቲያን ዜና እና Betachn ቤታችን የYoutube ቻናሎቻችን ብቻ ያገኙታል።..

ሊንኩን ይጫኑ https://www.youtube.com/watch?v=mZ1fCB8dMOM

ለ8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ሚስቱን ተሸክሞ የቆመው ባል የመኪና ተሸላሚ ሆነበካምቦዲያ ሴቶችን ተሸክሞ ረጅም ሰዓት በመቆም ከዚህ ቀደም ያልነበረ እና አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘግባለች።በዚ...
10/03/2024

ለ8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ሚስቱን ተሸክሞ የቆመው ባል የመኪና ተሸላሚ ሆነ

በካምቦዲያ ሴቶችን ተሸክሞ ረጅም ሰዓት በመቆም ከዚህ ቀደም ያልነበረ እና አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘግባለች።

በዚህ ውድድር ላይ ሬውን ቪቼት እና ባለቤቱ ሂም ፒሴይ ውድድሩን በማሸነፍ የማዝዳ መኪና ተሸላሚ መሆን የቻሉ ሲሆን፤ ሬውን ቪቼት ሚስቱን ለ8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ያክል ተሸክሞ በመቆም ክብረወሰን ጭምር አስመዝግቧል።

ውድድሩ የሴቶች ቀንን ለማክበርና የሴቶች በወንዶች ህይወት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማሳየት የተካሄደ ነው።

Betachn ቤታችን Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 👍👍👍

 !!🙏🙏 የትዳር ቁንጮ በሆነው  #ፍቅር  #ውስጥ በመኖር በትዳር 20 ዓመታትን አስቆጠሩ!አገልግሎት የጀመረዉ በሀረር ከተማ ነዉ። በአገልግሎት ጉዞ ዉስጥ ከመደብደብ አንስቶ ሞቷል በሚያስብል...
28/02/2024

!!🙏🙏

የትዳር ቁንጮ በሆነው #ፍቅር #ውስጥ በመኖር በትዳር 20 ዓመታትን አስቆጠሩ!

አገልግሎት የጀመረዉ በሀረር ከተማ ነዉ። በአገልግሎት ጉዞ ዉስጥ ከመደብደብ አንስቶ ሞቷል በሚያስብል ለወንጌል ዋጋ ከፍሎአል።

በ90ዎቹ በመላዉ ኢትዬጲያ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በነበረበት ወቅት ከነበሩ ወጣት አገልጋዮች መካከል አንዱ ነዉ።

ዛሬ በአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ከሚያገለግሉ ወጣት እና አንጋፋ ከሚባሉት መካከል ይጠቀሳል።

ሀረር ፣ ናዝሬት ፣ እና ሜክሲኮ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ላለፉት ከ22 ዓመታት በላይ አገልግሏል።

በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን "ሀልዎት" አጥቢያን ላለፉት አራት ዓመታት እየመራ ይገኛል።

ላለፉት በርካታ አመታት በአገልግሎት ብዙዎች የተባረኩበት ትሁቱና ተወዳጁ አገልጋይ ነብይ ዘኔ እጅግ ከሚወዳት ከሚያከብራት ለአገልግሎት ለህይወቱ አጋር ከሆነችዉ የሁለት ልጆቹ እናት ባለቤቱ ገነት ለማ ጋር ከተጋቡ 20 ዓመታትን አስቆጥረዋል።

የሀልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስትያን የ4 አመት የምስረታ ክብረ በዓል እና 20 ዓመት የተሳካ የትዳር ቆይታ! ድርብ በዓል ።

ለቤታችን ቴሌቪዥን አገልግሎት የቅርብ ወዳጅ ናቸዉ በድጋሜ #እንኳን አደረሳችሁ። ቀሪ ዘመናችሁም የተባረከ ለትውልዱ ትዳራችሁና አገልግሎታችሁ የህይወት ሽታና ምሳሌ እዲሆን መልካም ምኞቴ ነዉ።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Betachn ቤታችን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Betachn ቤታችን:

Share