Henok Abera Mamo

Henok Abera Mamo There can be no higher law in journalism than to tell the truth and to shame the devil. Walter Lippma

ባህሉን የሚያከብር የከበረ ህዝብ!አይዴ ጫምባላላ!
15/03/2026

ባህሉን የሚያከብር የከበረ ህዝብ!

አይዴ ጫምባላላ!

የበጋ መልክገፀ ውብ ኢትዮጵያ!
23/01/2026

የበጋ መልክ

ገፀ ውብ ኢትዮጵያ!

ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!መልካም በዓል!
19/01/2026

ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

Back to the spirit, back to the theatre!
17/01/2026

Back to the spirit, back to the theatre!

ነፍስህ በሰላም ትረፍ ነፂ!ለተሰበረ ልብ እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ!
16/01/2026

ነፍስህ በሰላም ትረፍ ነፂ!

ለተሰበረ ልብ እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ!

ኢትዮጵያ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፉን ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ዛሬ ጀምራለች።በቢሾፍቱ የሚገነባው ግዙፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አ...
10/01/2026

ኢትዮጵያ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፉን ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ዛሬ ጀምራለች።

በቢሾፍቱ የሚገነባው ግዙፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አስጀምረውታል።

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓል(ገና) በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!መልካም በዓል!
07/01/2026

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓል(ገና) በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

03/01/2026

በሳንቲያጎ ነዋሪ የሆኑት የቬኔዙዌላ ዜጎች የሀገራቸው መሪ ኒኮላስ ማዱሮ በአሜሪካ መታሰሩን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ነው።

ያወቅኳቸው በስራ ነው። ስለኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ያወቅኩትም በፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ ምክንያት ነው። በስራ ዓለም ረጅም ቃለመጠይቅ ያደረግኩት ከፕሮፌሰሩ ጋር ነበር። ቃለመጠይቁ በደቡብ ኤፍ...
09/11/2025

ያወቅኳቸው በስራ ነው። ስለኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ያወቅኩትም በፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ ምክንያት ነው። በስራ ዓለም ረጅም ቃለመጠይቅ ያደረግኩት ከፕሮፌሰሩ ጋር ነበር። ቃለመጠይቁ በደቡብ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ኤፍ ኤም 100.9 ለ4 ተከታታይ ሳምንታት መተላለፉ ትዝ ይለኛል። ለመጀመሪያ ጊዜ በግለሰብ ቤት ውስጥ ቤተ መፅሐፍት የተመለከትኩትም ፕሮፌሰር ጋር ገርጂ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነበር። በወቅቱ በጣም የገረመኝ አሁንም ሳስበው የምደንቀኝ አንዳንድ ታሪኮችን በቅርስ ጭምር አስደግፈው ማደራጀታቸው ነው። ከቤተ መጽሐፍት በተጨማሪ ልዩ ልዩ ቅርሶችን ሰብስበው ያደራጁበትን ክፍል መመልከቴን አስታውሳለሁ። እሳቸው ስለኢትዮጵያ ታሪክ ማውራት ከጀመሩ መቋጫ የለውም። ለሀገር ያላቸው ፍቅርም ጥልቅ ነው።

የኢትዮጵያ ታሪክ አባት፤ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል።

ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርና ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናት እንዲሆን እመኛለሁ።

የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በመግባት 6 መንደሮችን በጉልበት መቆጣጠሩን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገለፀ“የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በንጹሐን የአፋር አ...
06/11/2025

የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በመግባት 6 መንደሮችን በጉልበት መቆጣጠሩን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገለፀ

“የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግልጽ አፍርሷል” ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሰሰ

“የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በመግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 በመደብደብ የተለመደውን የሽብር ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል” ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሰሰ።

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከሰዓታት በፊት ባወጣው መግለጫ “ቡድኑ በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 26/02/2018 ዓ/ም በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች ወሰን ተሻግሮ በመግባት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግልጽ አፍርሷል” ሲል ገልጿል።

“የህወሓት ጠብ አጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንድመለሱ ቢማፀኗቸውም አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል” ያለው መግለጫው “ከትናንት ጥፋቱ የማይማረው የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ በአስቸኳይ ካልተቆጠበ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የዜጎች ደህንነትና የወሰኑን ክብር የማስጠበቅ፣ እንዲሁም ራስን ከማንኛውም ውጫዊ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ እንገልፃለን” ሲል አስጠንቅቋል።

👉 ! "አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት ሊሞላኝ ነው፤ ለሊት እንቅልፍ የለኝም ፥ ለ 2 ሠዓታት ብተኛ ነው ቀሪውን አለቅስበታለሁ። ለምንደነው ብዙ ለማንቆይበ...
19/10/2025

👉 !

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት ሊሞላኝ ነው፤ ለሊት እንቅልፍ የለኝም ፥ ለ 2 ሠዓታት ብተኛ ነው ቀሪውን አለቅስበታለሁ። ለምንደነው ብዙ ለማንቆይበት የምንጋደለው!? ለምንስ ነው የምንጫረሰው!? በጣም ያሳስበኛል ያስለቅሰኛል!"

***
ሰውነት ይቀድማል!

‹‹ሰው ሁኑ! ቅድሚያ ሰውነት ይቀድማል!
ከሐይማኖት ሰውነት ይቀድማል! ከዘርም ሰውነት ይቅደም!
አላህ ሰውን ከሁሉ በላይ አልቆታል::

ሰው ሊገፋ፣ ሊሰደድ፣ ሊገደል፣ ሊናቅ፣ ሊወገዝ በፍፁም አይገባም:: ልዩ ፍጥረቴን ክብሩን ጠብቁት በማለት አዟል››

የክብር ዶክተር፣ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ

Via

19/10/2025

ኮሬ!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Henok Abera Mamo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Henok Abera Mamo:

Share