
21/05/2025
አንጋፋው !!!
ጊዜው ከ 34 ዓመት በፊት ነበር ታሪካዊቷ ቀን (ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም) የሀገሪቷ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም ከሀገር የመውጣታቸው ዜና በብሔራዊ ራዲዮ የዘገበው እውቁ ጋዜጠኛ ዳሪዮስ ሞዲ ነበር።
ዜናው እንዲህ የሚል ነበር.. ..........
"ለረጅም አመታት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲካሄድ የነበረው የርስ በርስ ጦርነት ያስከተለውን የኢትዮጵያውያን ህይወት መጥፋትና ከኑሮ መፈናቀል ለማስቀረት በልዩ መልኩ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ሆኖም ችግሩ አልተቃለለም ፤ ይልቁንም ወደ ባሰ ደረጃ እየተሸጋገረ በመሄድ ላይ ይገኛል።
...ስለዚህ ደም መፋሰስ እንዲቆምና ሰላምም እንዲሰፍን በልዮ ልዩ ወገኖች የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ከስልጣን መውረዳቸው እንደሚበጅ የታመነበት ስለሆነ ይህንኑ በማመዛዘን ፕሬዘዳንት መንግስቱ ኃይለማሪያም በዛሬው ዕለት ከስልጣናቸው ወርደው ከኢትዮጲያ ውጪ ሄደዋል....።"
ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን በመውረድ አገር ለቀው በመሄዳቸው የሪፑብሊኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን ተክተው ይሰራሉ።