ሐሪማ ቲቪ - Harima Tv

ሐሪማ ቲቪ - Harima Tv ሐሪማ ቲቪ !
የምጥቀት መሰላል !

ሐሪማ ቴቪ የአላህን ውዴታ የሚፈልግ፣ ለረሱል (ሶ•ዐ•ወ) ፍቅር ኖሮት ሱናቸውን የሚከተል፣ ሶሃቦቹን አርአያው የሚያደርግ፣ የመሻይኾቹን መንገድ የሚያፀና፣ መሻይኾቹን የሚወድና ፈለጋቸውን ለመከተል የሚተጋ ዜጋ እና ማህበረሰብ መፍጠር፣ የአህለሱና ወልጀማዓ መስመር የመሻይኾቹን መንገድ የኢትዮጵያ እስልምና ገዢ የአስተሳሰብ መስመር ለማድረግ የሚተጋ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው

21/07/2025
ሐገራዊውን “መንዙማ” በዕውቀትና በሥርዓት፣ በተዋበ ድምጽና ወግ በጠበቀ ቅኝት ለትውልድ በማሸጋገር ለአርባዎቹ ዓመታት የላቀ ሚና ያበረከቱት ማዲህ ሸህ ሙሐመድ ሑሴን በ63 ዓመታቸው በዛሬው ...
03/07/2025

ሐገራዊውን “መንዙማ” በዕውቀትና በሥርዓት፣ በተዋበ ድምጽና ወግ በጠበቀ ቅኝት ለትውልድ በማሸጋገር ለአርባዎቹ ዓመታት የላቀ ሚና ያበረከቱት ማዲህ ሸህ ሙሐመድ ሑሴን በ63 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት አርፈዋል።

ውልደት እና ዕድገታቸው ደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ አካባቢ ነበር። የዒልም(ዕውቀት)፣ የአዳብ(ሥርዓት)፣ የመንፈሳዊ እነጻ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁት በ“ዛውዮች” በ“ኡላኡላ” በ“መጅት” የዕውቀትና መንፈሳዊ ማዕከላት ነው። በዋነኝነት የዳግማዊ መጅት(ሸህ ሰዒድ ቡሽራ) ምሩቅ ናቸው።

ለመንፈሳዊ መምህራቸው ለዳግማዊ መጅት የላቀ ፍቅር፣ አክብሮት እና አገልግሎት(ኺድሚያ) ነበራቸው። ሦስት ጊዜ መካ-መዲና አብሮ የመጓዝ ወርቃማ ዕድል አግኝተዋል። ዱዓ እና ምርቃትም ተችረዋል።

ሸህ ሙሐመድ ሑሴን ለነቢ ሙሐመድ(ሶ.ዓ.ዎ.) የከበረ ፍቅር፣ ናፍቆት፣ ተከታይነት ነበራቸው። ለሃያ ጊዜ ያክል መካ-መዲናን የመዘየራቸው ሚስጥር፣ ለአርባዎቹ ዓመታት በመድህ(መወድሰ ነቢ) የማገልገላቸው ቀመር ከዚያ የሚመነጭ ነው።

በኢማምነት፣ በመልካም ጸባይ ታግዘው ግብረ ገባዊ ምክርና ታሪክ በመለገስ፣ ሐገርን ሰርክ በጸሎት/ዱዓ በማሰብ ይታዎቃሉ። በወሎ በአዲስ አበባ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አላቸው። የመንዙማ አበርክቷቸው በመላ ኢትዮጵያ ዕውቅና አለው። እንዲሁም ከዐስራ አምስት በላይ ዕውቅ ተተኪ ማዲሆችን አፍርተዋል። በትዳር ሕይዎታቸውም አምስት ልጆችን ወልደዋል።

በአዲስ አበባ በዛሬው ዕለት ሙፍቲ ሐጂ ዑመርን ጨምሮ በርካታ ዓሊሞች(ሊቃውንት)፣ ምሁራን እና ምእመናን መንፈሳዊ ሽኝት አድርገውላቸዋል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸው በነገው ዕለት በኮምቦልቻ ከተማ ይፈጸማል።

(በኸድር ታጁ)

ታላቁ ማዲህ ሸይኽ ሙሀመድ ሁሴን ወደ አኼራ ተሻግረዋል................................ለዘመናት ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በማወደስ የሚታወቁት ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን ...
03/07/2025

ታላቁ ማዲህ ሸይኽ ሙሀመድ ሁሴን ወደ አኼራ ተሻግረዋል................................
ለዘመናት ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በማወደስ የሚታወቁት ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን ዛሬ ጠዋት አዲስአበባ ላይ ያለፉ ሲሆን ረፋድ ላይ ታላላቅ ዑለማዎች እና ወዳጆቻቸው ተሰባስበው ጀናዛቸው ወደ ሚያርፍበት ኮምቦልቻ ሸኝተዋል ።

ሐሪማ ቴሌቪዥን በኚህ ታላቅ አሊም እና ማዲህ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ ህዝበ ሙስሊሙ ዱአ እንዲያደርግ መልእክቱን ያስተላልፋል።

Address

Addis Abeba

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሐሪማ ቲቪ - Harima Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሐሪማ ቲቪ - Harima Tv:

Share

Category