
04/04/2025
ግንባታ የጀመርንበት 365ኛ ቀናችን ዛሬ ነው።
B+G+3 የሆነ መስጂድ ለመገንባት የመጀመሪያውን ስራ በረመዷን ወር ከማህበረሰቡ በተሰበሰበ መዋጮ ግንባታውን ያስጀመርንበት ታሪካዊ ቀን። የህንፃውን ዲዛይን በበጎ ፍቃደኝነት የሰሩልን ባለሙያዎች ግንባታው ከ90 ሚሊየን እስከ 100 ሚሊየን ይፈጃል ሲሉን በርካታ ሰዎች ይሄ በዚህ ሰፈር ሰው አቅም አይቻልም ብለው ነበር። በአላህ እገዛ እና በማህበረሰቡ ርብርብ እንዲሁም በአንዳንድ ኡስታዞችና መሻይኮች ድጋፍ በተጨማሪም በቲክቶከር እህት ወንድሞች አስተዋፅኦ በአንድ አመት ውስጥ 25 ሚሊየን የሚጠጋ ብር በማሰባሰብ ከታች በምስሉ ላይ በምታዩት መልኩ የቤዝመንት እና የግራውንዱን ስትራክቸር በማጠናቀቅ የ1ኛ ፎቅን ኮለን በማቆም ላይ እንገኛለን።
በዚህ ሂደት ውስጥ ከጎናችን የነበራቹህ ወንድም እህቶች በገንዘብ፣በጉልበት፣በሙያ፣በአይነት፣ በሚድያቹ ሽፋን የሰጣችሁ የሚድያ አካላት እና በሀሳብ ጭምር ያገዛችሁንን እንዲሁም የግንባታውን ግብኣት የሚሆኑ እቃዎች ልንገዛቹህ ስንል ለመስጂድ ነው በማለት ዋጋ የቀነሳችሁልንን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በመጨረሻም መስጂዱን ለማጠናቀቅ ያስችል ዘንድ አሁንም ተጨማሪ ድጋፋቹ አይለየን እያልን የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የቡራዩ ሰለሀዲን መስጂድ
መልካም ጁመዓ ይሁንላችሁ
የመስጂዳችንን ግንባታ ለማፋጣን በምናደርገው ጉዞ ከጎናችን እንድትሆኑ በአክብሮት እንጠይቃለን።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000551081013
በዘምዘም ባንክ
0040137820101
ዳሽን ባንክ
2958571560711
ኦሮሚያ ባንክ
1323534100001
የአካውንት ስም የሰለሀዲን መስጂድ ግንባታ ኮሚቴ
ለበለጠ መረጃ 0921125054 ደውሉ