06/01/2023
ቀን.28/04/2015
የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሉ ወቅታዊ ጥሪ እና ሳምንታዊ መልእክት
በወረዳችን ብልሹ አሰራር እና ሌብነትን መታገል ከጀመርን የቆየን ቢሆንም ባለዉ ዉስብስብ እና አስቸጋሪ ሁኔታ ያልተጋለጡ አለያም ተጣርተዉ ለሚመለከተዉ አካል ቀርበዉ ግን ዉሳኔ ያልተሰጣቸዉ እንዳሉ እርግጠኞቸ ነን፤
በመሆኑም በዙሪያችን ለተሰለፋችሁ የፀረ ሙስና ንቅናቄ ሀይሎች የምናቀርበዉ ጥሪና መልእክት ከኑሮ ዉድነት እና ከስራ አጥነት ቀጥሎ ግብር ከፋይ ደንበኛውንና ጠቅላላ ህዝቡን እያማረረ ያለዉን ሌብነትና ማጭበርበር በተዘረጋው ሚስጢራዊ የአሰራር ስርአት ጥቆማና መርጃ አድርሱን ፤ሽፋን ሰጭዎች፣ደላሎች፣ተላላኪዎች፣አቀባባዮች፣ተካፋዮች፣ሰዋሪዎች ደግሞ ድርጊታችሁን አቁሙ ለህዝብና ለሃገር ቁሙ ፤ፈጣሪያችሁን ቀና ብላችሁ እዩ፣ለነፍሳችሁ አስቡ፣ከዚህ እኩይ ተግባር እራሳችሁን አርቁ ይህንን ማድረግ ካልቻላችሁ ህዝቡ የሚታገስበት ጊዜና ነባራዊ ሁኔታ ያበቃ መሆኑን እራሳችሁን ቆም ብላችሁ እዩ ፡፡ ጊዜው ፖለቲካን ስልጣንን ሀይልን ጉልበትንና ጨለማን የማይፈራ ነው፡፡ ሲል የይልማና ዴንሳ ወረዳ አስተዳደር የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡