B̤e̤r̤e̤g̤e̤n̤a̤-A̤b̤a̤y̤e̤ M̤e̤d̤i̤a̤

B̤e̤r̤e̤g̤e̤n̤a̤-A̤b̤a̤y̤e̤ M̤e̤d̤i̤a̤ Kulito

09/11/2024

በህፃን ሟዓዝ ለሙስሊም ሴቶች የተላለፋ መልዕክት

 ስልጠና የለዉጡ ቱሩፋት መስክ ጉብኝት የተወሰዳ ፎቶ ጥቅምት 29/2017 ዓ ም
08/11/2024


ስልጠና የለዉጡ ቱሩፋት መስክ ጉብኝት የተወሰዳ ፎቶ
ጥቅምት 29/2017 ዓ ም

 ፦ስትኖር እንደ በቀቀን ሳይሆን እንደ ንስር ይሁን። በቀቀን ብዙ ያወራል ግን መብረር አይችልም፤ ንስር ግን በዝምታ ሆኖ ሰማይን የመንካት አቅም አለው!
11/10/2024



ስትኖር እንደ በቀቀን ሳይሆን እንደ ንስር ይሁን።

በቀቀን ብዙ ያወራል ግን መብረር አይችልም፤

ንስር ግን በዝምታ ሆኖ ሰማይን የመንካት አቅም አለው!

ልማቱን በህዝብ ድጋፍ የሚገነባአመለካከቱን ሳያደርግ የተዛባማነዉ አትበሉኝ ህዝቡም ሀላባየገበዉ ማይወጣት የፍቅር አምባለልማት ከሆና ለመስጣት የሚሽቀዳደምአጋጣሚ ሳትጠይቀዉ ብታልፈዉ አጠይቁኝም...
01/09/2024

ልማቱን በህዝብ ድጋፍ የሚገነባ
አመለካከቱን ሳያደርግ የተዛባ
ማነዉ አትበሉኝ ህዝቡም ሀላባ
የገበዉ ማይወጣት የፍቅር አምባ

ለልማት ከሆና ለመስጣት የሚሽቀዳደም
አጋጣሚ ሳትጠይቀዉ ብታልፈዉ አጠይቁኝም
ብሎ እኔ ሀላባ አይደለዉምዴ ብሎ የሚቀየም

ለመስጣት ስለሆና ይወስድና እጅ ይዞ ጎትቶ
መርጣችሁ ዉሰዱ ብሎ የሚሰጥ በረቱን ከፍቶ
ከጥንትም ጀምሮ ለመስጣት አይሰስትም ከቶ
እንደልማዱ ያስመርቃል ስታዲያሙን ገንብቶ

𝔹 𝔸 ነሐሴ 26/2016 ዓ ም

 🐝🐝🐝🐝የ2016 የኢትዮጵያ ክልሎች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀው የሀላባ ዞን ተወካይ ጉባ ከተማ አቶቲ እግር ኳስ ክለብ ወደ የሀላባ ዞን ስገቡ ከአለም ጤና ቀበሌ ጀምሮ ደመቅ...
24/07/2024

🐝🐝🐝🐝
የ2016 የኢትዮጵያ ክልሎች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀው የሀላባ ዞን ተወካይ ጉባ ከተማ አቶቲ እግር ኳስ ክለብ ወደ የሀላባ ዞን ስገቡ ከአለም ጤና ቀበሌ ጀምሮ ደመቅ አቀባባል እንደሚደረግ የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ
======

ሀምሌ 17/2016 የዘንድሮው የኢትዮጵያ ክልሎች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀው የሀላባ ዞን ተወካይ ጉባ ከተማ አቶቲ እግር ኳስ ክለብ ወደ የሀላባ ዞን ስገቡ ከአለም ጤና ቀበሌ ጀምሮ ደመቅ አቀባባል እንደሚደረግ የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ አስታወቀዋል።

የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ እንደገለጹት የሀላባው ጉባ አቶቲ የውድድርና ከውድድር በላይ ትኩረት የሚሰጠውን የፀባይ ዋንጫ በማንሳት በአጠቃላይ የ 2 ዋንጫ ባለቤት በመሆን ታሪክ የፈጸመውን ክለብ በነገው ዕለት ከ3:00 ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በነገ ዕለት ከ3:00 ጀምሮ በሀላባ ቁሊቶ አቀባበል ተደርጎላቸው ወደ አቶቲ ኡሎ ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ጉባ ከተማ እንደሚሸኝ ጠቁመዋል።

ስለሆነም ይህን ታሪክ የቀየረው ጉባ ከተማ አቶቲ የዞኑ ህዝብ እና የስፖርት ቤተሰብና፣ የስፖርት አፍቃሪዎች ተገኝታችሁ አቀባበል እንድያደርጉ አቶ ሀሩና አህመድ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የጉባ ከተማ አቶቲ እግር ኳስ ክለብ ዋና አቀባበል ፕሮግራም የወረዳው መቀመጫ የሆናችሁ በጉባ ከተማ እንደሚደረግ አቶ ሀሩና አህመድ ገልጸዋል።

የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው

  የማዕከላዊ እትዮጲያ ክልል ተወካይ የሀላባዉ   ለዋንጫ ማለፋቸዉን አረጋገጡ💪💪እንኳን ደስ አላችሁ
18/07/2024

የማዕከላዊ እትዮጲያ ክልል ተወካይ የሀላባዉ ለዋንጫ ማለፋቸዉን አረጋገጡ💪💪
እንኳን ደስ አላችሁ

 ̲i̲d̲_M̲u̲b̲a̲r̲i̲k̲_F̲o̲r̲_a̲l̲l̲ ሙስሊምበዓሉ የመተሳሰብ፣የመተዛዘን፣የተራቡትን የሚናበላበት እና የመከባበር በዓል እንዲሆንልን ዘንድ ምኞቴ ነዉ።
15/06/2024

̲i̲d̲_M̲u̲b̲a̲r̲i̲k̲_F̲o̲r̲_a̲l̲l̲ ሙስሊም
በዓሉ የመተሳሰብ፣የመተዛዘን፣የተራቡትን የሚናበላበት እና የመከባበር በዓል እንዲሆንልን ዘንድ ምኞቴ ነዉ።

በሀላባ  ዞን በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በባለፉት ስድስት(6) የለወጡ መንግሥት የሥልጣን ዓመታት ጉዞ በተሰጠው ብስለት የተሞላ አመራር ሚና በርካታ የሰላም፣የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲ...
07/04/2024

በሀላባ ዞን በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በባለፉት ስድስት(6) የለወጡ መንግሥት የሥልጣን ዓመታት ጉዞ በተሰጠው ብስለት የተሞላ አመራር ሚና በርካታ የሰላም፣የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ግንባታ ትሩፋቶች ተገኝተዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በሀላባ ዞን በለውጡ መንግስት ጠንካራ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠርና የተደራጀ የህዝብ ተሳትፎን በማሳለጥ የዞኑን ህዝብ ሁለንተናዊ ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ እየሠራ የሚገኝ የለውጥ
ፓርቲ ነው!።

ፓርቲው በዞኑ በተለይም የባለፉት ስድስት የለውጡ ዓመታት በሰጠው በሳልና ብቃት የለው መሪነት በየዘርፉ የዞኑን ህዝብ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግና በተጨባጭ ያረጋገጡ የተለያዩ ተግባራትን አከናውኗል።

በዚህም በትምህርት፣ጤና፣በግብርና ፣በውሃ፣በመንገድና፣ በተለያዩ በመሰረተ ልማት መስኮች አንጸባራቂ ድሎች ተመዝግቧል።

ለውጡ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ግንባር ቀደም መሪነት የዞኑ የአመራር አንድነት በመፍጠር እስከ ታችኛው መዋቅር ወርዶ በመደገፍና በማስተባበር፣ ህዝቡን ከጫፍ እስከጫፍ በማነቃነቅ በአጽንኦት ሰርቷል፣ እየሠራም ይገኛል።

በተለይም በዞኑ የለውጡ አመራር፣መንግስት እና ህዝብ መደማመጥ፣መተማመን፣መግባባት ላይ መድረስ በመቻሉ በቅንጅትና በጋራ ተሳትፎ በርካታ አመርቂ ሥራዎችን በተግባር አሳይቷል።

በዚህም በዞኑ የህዝቡ የቆዩና የረጅም ጊዜያት፣የዘመናት የልማት ጥያቄዎች ከመመለስም ባለፈ የዞኑን ማህበረሰብ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ውጤቶች ተገኝተዋል።

የህዝቡን የልማት፣የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ከምንጫቸው ለማክሰም በቁርጠኛነት ማሰራቱንም አብራርተዋል።

በዚህም የተመዘገበው ስኬትም በፓርቲው በሳል አመራር፣በመላው አመራር፣አባላትና ደጋፊዎቹ ጥንካሬና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ መሆኑንም እውቅና ሰጥተዋል።

በማህበራዊ፣በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካ መስኮች በአፈፃፀም ረገድ የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም፣የተገኙ ስኬቶች አጠናክሮ በማስቀጠል እና የተሳኩ ተሞክሮዎችን በማስፋት የሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ መላው የፓርቲው አባል በነቃ ተሳትፎ መረባረብ እንዳለባትም አቶ ሙህድን አሳስበዋል።

የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ፣

በዚህ በኸይር ወር ቀንና ማታ ሁለት ፆም የሚፆሙትን ማስፈጠር ወላህ ሀጅ ከማድረግ አይተናነስም Mêrryyêm Yh Bêrgênå Lj አለህ አጅራችሁን ከፍ ያድርግላችሁ ጀዘዉን ይክፈላችሁ።አለህ...
23/03/2024

በዚህ በኸይር ወር ቀንና ማታ ሁለት ፆም የሚፆሙትን ማስፈጠር ወላህ ሀጅ ከማድረግ አይተናነስም Mêrryyêm Yh Bêrgênå Lj አለህ አጅራችሁን ከፍ ያድርግላችሁ ጀዘዉን ይክፈላችሁ።
አለህ እኛንም ይወፍቀን

የበርካታ በሽታ ፈዋሽና የብዙ ታሪክ ባለቤት የሆነዉ የአርቶ ፍል ዉሃ በሰንሰለታማዉ ሞቶቆማ ተራራ ከላይ በኩል ከብቶች የሚዉሉበት የተንጣለለዉ እጅግ ዉብ የሆና ሜዳማ ስፍራ በተጨማሪም አሩንጓ...
25/02/2024

የበርካታ በሽታ ፈዋሽና የብዙ ታሪክ ባለቤት የሆነዉ የአርቶ ፍል ዉሃ በሰንሰለታማዉ ሞቶቆማ ተራራ ከላይ በኩል ከብቶች የሚዉሉበት የተንጣለለዉ እጅግ ዉብ የሆና ሜዳማ ስፍራ በተጨማሪም አሩንጓዴ ፓርኩ ማራኪ አድርጓታል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ክርስቲያን ሙስሊሙ መከባበር በጥምቀት በዓል
20/01/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ክርስቲያን ሙስሊሙ መከባበር በጥምቀት በዓል

ከፌዴራልና ከክልል እንዲሁም ከአጎራባች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች አቀባበል በስንፖዚያም።ሀበይ ወገሬቲን አሜቴንተ እንኳን ደህና መጡ
13/01/2024

ከፌዴራልና ከክልል እንዲሁም ከአጎራባች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች አቀባበል በስንፖዚያም።
ሀበይ ወገሬቲን አሜቴንተ

እንኳን ደህና መጡ

ዕድገቱን የሀላቢሳን ቋንቋና ባህል ወጉን ማመር ያደረገዉ ወጣት ሸምሰዲን አዳም በቅፅል ስሙ የሀላባዉ ሐጫሉ ይሉታል።ከልጅነቱ እስከ ወጣትነት በዚህ በትንሽ ዕድሜዉ የሀላብኛን ቋንቋ በተለያዩ ...
02/01/2024

ዕድገቱን የሀላቢሳን ቋንቋና ባህል ወጉን ማመር ያደረገዉ ወጣት ሸምሰዲን አዳም በቅፅል ስሙ የሀላባዉ ሐጫሉ ይሉታል።
ከልጅነቱ እስከ ወጣትነት በዚህ በትንሽ ዕድሜዉ የሀላብኛን ቋንቋ በተለያዩ መልክ በመዝፈን በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ ሀላባን ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም እንዲታወቅ አድርጎታል።
....ጅማሬወቹ
ያኔ ትምህርት ቤቶች መዝግያ ዕለት የእሱ ግጥም አልፎም ድራማዉ የት/ቤቱ ድምቀት ነበር በየክፍሉ ከ1-3ኛ ደረጀ የወጡ ተማሪዎች የተለያዩ ሽልማቶችን ይዘዉ ሲመለሱ እሱ ግን ከወላጆች የተሸለመዉን ብር ይዞ ነበር ሰፈሩን የሚመለሰዉ
......በዚህም አልተዋም ለዚህ ደረጃ ያበቀዉም የት/ቤቱ ክነ-ጥበብ ክበብ ነበር
ወጣቱ ልጅ ጉዞዉን ቀጥሏል የሀላባን ባህል ወደፊት ለማሳደግ ገጣሚዉ እራሱ ሆኖ ቅንብርም እራሱ የሚገርመዉ ዜማዉም እራሱን አርግቶ ግስጋሴዉን ወደ ፊት አርግቷል።

ከ'ሀይ በራን'ችሎተኖ ጀምሮ
አሰምተሃል የቄረንሶን ህዝብ እሮሮ
አሁንም እያደመቃ ነዉ በሴራ ዋዜማ
ሴራዉን አስመልክቶ ለቋል አንድ ዜማ
በዕድሜ ትንሹ በስራዉ አንጋፋ
ገነ ትሰራለህ ሀላቢሳ እንዲሰፋ

የወደፊቱ ብቻ አይደለም ከኋላም ደርሶ ወደፊት መምጣት እንደሚቻል ጭምር ያስተማርከን ጀግና ወጣት ሸምሰዲን አዳም በርታ ለማለት ወደድኩኝ።

አመሰግናለዉ🙏
ታህሳስ 23/2016 ዓ/ም 🇧 🇦

እንደ በርበሬዉ ጣፋጮች በሴራዉ
31/12/2023

እንደ በርበሬዉ ጣፋጮች በሴራዉ

የሴራዉ (መንገሳ)በዓል በዛሬዉ ዕለት በዌራ ዲጆ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዉሏል።
27/12/2023

የሴራዉ (መንገሳ)በዓል በዛሬዉ ዕለት በዌራ ዲጆ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዉሏል።

የሴራዉ ድምቀት
25/12/2023

የሴራዉ ድምቀት

የሀላባ ሴራ በዓል ዋዜማ ድባብ
25/12/2023

የሀላባ ሴራ በዓል ዋዜማ ድባብ

የሴራ በዓል ድባብ 🇪🇹🇪🇹
25/12/2023

የሴራ በዓል ድባብ
🇪🇹🇪🇹

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when B̤e̤r̤e̤g̤e̤n̤a̤-A̤b̤a̤y̤e̤ M̤e̤d̤i̤a̤ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share