
22/08/2025
የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ግዜ ገደብ ለመጠናቀቅ በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ ይገኛል - ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን
=====
ነሀሴ 16/2017 የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ግዜ ገደብ ለመጠናቀቅ በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን ገለጹ።
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳ ክብር አቶ ሙህዲን ሁሴን የሚመራ ልኡክ በማልት ወዳዱ በሀላባ ህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ ያለውን የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ያለበትን ደረጃ ተመልክቷል።
በዚህ ወቅትም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደገለጹት ታሪካዊ የሆነው በልማት ወዳዱ በሀላባ ህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ ያለውን የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ፕሮጀክት ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የስታዲየሙ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለአካባቢው ኢኮኖሚ እና ቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት ተጨማሪ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ በተያዘለት ግዜ ገደብ እስኪጠናቀቅ ድረስ የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህን ትልቅ ፕሮጀክት የዞኑ የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ በማድረግ አሻራውን አሳርፎ የተጀመረው ግንባታ በተያዘለት ግዜ ገደብ ለመጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የሚፈልቁበትና የስፖርት ቤተሰብ በብዛት ያለበት መሆኑን ጠቅሰው፣ ስታዲየሙ በአካባቢው መገንባቱ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
በህዝብና በመንግስት ትብብር እየተገነባ ያለው የስታዲየም ፕሮጀክት እንዲጠናቀቅ ህዝቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
በሁሉም ህብረተሰብ ክፍል እየተሳተፈ የሚገኘው ይህ ታሪካዊ ፕሮጀክት እንዲሳካ በኩላቸውን አስተዋጽኦ እየበረከቱ ይገኛሉ ብለዋል።
በዚህም የዞኑ ህዝብን ጨምረው ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚኖሩ የብሄሩ ተወላጆችና ወዳጆችን አቶ ሙህድን ሁሴን ምስጋና አቅርበዋል።
በሹኩር ሀ/ሀሰን