
09/04/2025
የሚያስፈልገን ምንድ ነው?
➡️ የሚያስፈልገን ተጨማሪ ጊዜ ሳይሆን ሃሳባችንን የበታተነውን ነገር መቀነስ ነው!
➡️ የሚያስፈልገን ተጨማሪ መነቃቃት ሳይሆን ተጨማሪ ዲሲፕሊን ነው!
➡️ የሚያስፈልገን ተጨማሪ አቅርቦት ሳይሆን የቀረበልንን ነገር በትክልል መጠቀምና ማሳደግ ነው!
➡️ የሚያስፈልገን ተጨማሪ እድል ሳይሆን እድሉ ሲገኝ የተዘጋጀ ማንነት ነው!
➡️ የሚያስፈልገን የበለጠ “ቢዚ” በመሆን መስራት ሳይሆን በበለጠ ጥበብና ትኩረት መስራት ነው!
➡️ የሚያስፈልገን ሁሉንም ነገር ማወቅ ሳይሆን ባወቅነው ነገር አቅጣጫ አንድን ነገር መጀመር ነው!
➡️ የሚያስፈልገን ተጨማሪ ወዳጅ ሳይሆን አጠገባችን ያሉትን ወዳጆቻችንን ማክበር እና መንከባከብ ነው!