
23/04/2025
የ20 አመቷ ወጣት ጃዝሚን ያለአባት የምታሰድገውን የአንድ አመት ልጇን በእቅፎ ይዛ ወደ አንድ አነስተኛ ሱፐር ማርኬት ትገባለች።
ወተት፣ የህፃን ልጅ ምግብ እና ዳቦ መግዛት ፈልጋ በቦርሳዋ ያለው አንድ ዶላር ብቻ ነው፣ ለመግዛት የፈለገችው ምግብ እና እሷ የያዘችው ገንዘ አይመጣጠንም፣ ገንዘቡ ያንሳል።
ወተት፣ የህፃን ልጅ ምግብ እና ዳቦ በመያዝ ወደ ባለቤቱ ጋር በመሄድ ቀስ ብላ ማንም ሳይሰማ እንዲህ አለችው።
ያላትን ገንዘብ እየሰጠችው "ያለችኝ እቺ ናት ቀሪውን ገንዘብ ነገ አመጣለሁ የያዝኩትን ልውሰድ " አለችው ።የሱፐር ማርኬቱ ባለቤት ከማዘን ይልቅ አሳቀቃት፣ አሸማቀቃት ፣ አዋረዳት።
የሱፐር ማርኬቱ ባለቤት፣ እየጮኸ ሌሎች ሰዎች እንዲሰሙ እያመናጨቃት እንዲህ በማለት ተናገራት ።
አንቺ እና መሰሎችሽ ሁልግዜ ምንም ሳይኖራቹ እዚህ እየመጣቹ የሆነ ነገር ማግኘት ትፈልጋላችሁ ፤ መክፈል የማትችይ ከሆነ ለመለመን ሁለተኛ እዚህ እንዳትመጪ"
ባለቤቱ ጃዝሚንን ሲናገራት ሰዎች ሁሉ ጃዝሚንን እንደጉድ ይመለከቷት ነበር፤ ጃዝሚን በሃፍረት ሰውነቷ ቀዘቀዘ፤ የአንድ አመት ልጇ ምን እንደተባለ የሰማ ይመስል እሪ ብሎ እየጮኸ አለቀሰ።
ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ማይክል ጆርዳን በሱፐር ማርኬቱ ውስጥ እቃ እየገዛ ነበረ። ባለቤቱ ጃዝሚንን ምን ሲላት እንደነበር ይሰማል።
ጆርዳን በልጅቷ መሸማቀቅ በጣም በማዘን ወደ ባለቤቱ በመሄ፣ የኪስ ቦርሳውን በማውጣት የዛሬን ብቻ ሳይሆን ለጃዝሚን እና ለህፃን ልጇ ለአንድ ወር የሚሆናቸውን የሚያስፈልጋቸውን የምግብ ሂሳብ ከፈለ።
የዛን ግዜ ሁሉም ፀጥ አለ።
ጆርዳንም ለሱፐር ማርኬቱ ባለቤት እንዲህ አለው:-
" የአንተ ስራ ደንበኞችን ማገልገል ነው፣ መፍረድ የለብህም ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው፤አንዳንዴ ለተቸገረ ሰው ትንሽዬ ደግነት ያስፈልጋል ።"
©️አዳነ ካሳሁን