Diriba Melkamu D.

Diriba Melkamu D. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Diriba Melkamu D., Media/News Company, Ambo.

18/09/2026
ሮሃ እና አንከር ሚዲያዎች የሰራጩት ዜና ፍጹም ዉሸት ነዉ!ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳነት ሸመልስ አብዲሳ የተለያዩ የሸዋ ዞኖችና የቄለም ወለጋ ዞን አርሶደሮች መሳርያ ...
18/09/2026

ሮሃ እና አንከር ሚዲያዎች የሰራጩት ዜና ፍጹም ዉሸት ነዉ!

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳነት ሸመልስ አብዲሳ የተለያዩ የሸዋ ዞኖችና የቄለም ወለጋ ዞን አርሶደሮች መሳርያ በመግዛት እዲታጠቁ የሚለዉ መልክት አስተላልፈዋል የሚል ፍጹም ዉሸት፤ስም የማጥፋት ዘመቻና ለፖሊቲካ አላማ ሲባል የተቀነባበረ ወሬ ነዉ፤
ይህ ዉሸት መሆኑ ደግሞ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት ኃይሉ አዱኛ በፌስቡክ ገጻቸዉ በግልጽ ጽፈዉታል፡፡https://web.facebook.com/share/p/19jAeFbbzQ/

አቢቹ የተናገረውን የሚሠራ፣ ቃል ገብቶ የሚፈጽም መሪ ነው‼️የአቢቹ አመራር በወሬ የተወሰነ ሳይሆን በሀገሪቱ ውስጥ በሚታዩ ተላላቅ ሥራዎች ላይ የተመሠረተ ነው። የልማት ዕቅዶችን ወደ ተግባር...
18/09/2026

አቢቹ የተናገረውን የሚሠራ፣ ቃል ገብቶ የሚፈጽም መሪ ነው‼️

የአቢቹ አመራር በወሬ የተወሰነ ሳይሆን በሀገሪቱ ውስጥ በሚታዩ ተላላቅ ሥራዎች ላይ የተመሠረተ ነው። የልማት ዕቅዶችን ወደ ተግባር በመቀየር፣ ግብርናንና ምርታማነትን ማሳደግ፣ በኮሪደር ልማት ከተሞችን ለመኖሪያ ምቹ ማድረግና ገጠሩን ማዘመን ላይ ትኩረት በማድረግ፣ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንትን ማጠናከር፣ ኢንዱስትሪን ማሳደግ፣ ዲጂታላይዜሽንን ማፋጠን፣ እንዲሁም የመኖሪያ ቤቶችንና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ለዘመናት የቆየውን የሀገሪቱን ስብራት ለመጠገን የሚያስደንቁ እርምጃዎች ተወስደዋል።

በተጨማሪም እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኑክሌር ኃይል እና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ግንባታ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ። ስለዚህ ይህ የሚያሳየው ቃል ወደ ዕቅድ፣ ዕቅድ ወደ ተጨባጭ ሥራ፣ ሥራ ደግሞ ወደ ዜጎችን ማዕከል ያደረገ ውጤት እየተሸጋገረ መሆኑን ነው!

የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን ከሁሉም ሀገራት ጋር በትብብርንና ወዳጅነት እንድን ስራ የሚያስችል ፖሊሲ ነዉ! የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲችን ሀገራዊ ጥቅምንና ሉዓላዊነትን በማስከበር ከሁሉም...
18/09/2026

የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን ከሁሉም ሀገራት ጋር በትብብርንና ወዳጅነት እንድን ስራ የሚያስችል ፖሊሲ ነዉ!

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲችን ሀገራዊ ጥቅምንና ሉዓላዊነትን በማስከበር ከሁሉም ሀገራት ጋር መተባበር ላይ የሚያተኩር ነዉ፡፡
ሀገራችን ከሌሎች ጋር የምታደረገዉ ግንኙነት ቁልፍ በመባል የሚታወቀዉን ብሄራዊ ጥቅማችንን የሚያስከብርና የሌላዉን ጥቅም የሚያከብርና በጋራ በማደግን መሶሶ ያደረገ ፖሊሲ ነዉ፡፡

በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባትና በራሷም እንዳይገቡ የመከላከል መርህን መሰረት ያደረገ ሲሆን ይህ ሃሳብ በ1969 በቬይና ኮንቬንሽን ስምምነት መሰረት የሁሉንም የሃገራት እኩነትና ሎአላዉነት ከመፈራረም ጋር የተመጋገበ ፖሊሲ ነዉ።
ባለ ብዙ ወገን ዲፕሎማሲ የመከተል ጉዳይ፤ይህ ማለት ከምስራቁም ከምራቡም ጎራ ጋር እንዲሁ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት እንደነ ብሪክስ፤ተመድ፤የአዉሮፓ ህብረትና ሌሎች ቀጠናዊና ሀጉራዊ ተቋማት ጋር በትብብርና በጋራ መስራት ሲሆን እየሰራችበትም ትገኛለች፡፡

በመጨረሻም የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ ብቻ ማደግና መበልጸግን ሳይሆን በአከባቢዋና በቀጠናዋ በጋራ በሁሉም መስክ በኢኮኖሚዉ(በመንገድ፤በባቡር፤በንግድ)፤በፖሊቲካዉ(በጋራ ሰላምን ማስፈን)፤በማህበራዊዉ(በቴሌኮም፤በትምህርት) እና በሌሎች መስክ የመስራትን አስቀምጦል፤እየሰራችበትም ትገኛለች፡፡

ስለሆነም ሀገራችን በለዉጡ መንግስት በሀገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን የመደመርን/ሲነርጅን ጉዳይ የሚፈልገዉ በቀጠናዉም አልፎ በአለምም ትብብርን አጥብቆ የሚፈልግና ለዝህም የሚሰራ ነዉ፡፡

በሕወኃት ጠባብና እብረተኛ ፍላጎት ምክንያት የታጠቁ የትግራይ ልጆች ከመሞት እራሳቸዉን ማዳን አለባቸዉ!መላዉ የክልሉ ወጣት መረዳት ያለበት ማብቂያ ላሌለዉና ዘመኑን ያልዋጀ የጦርነት አባዜ ፈ...
18/09/2026

በሕወኃት ጠባብና እብረተኛ ፍላጎት ምክንያት የታጠቁ የትግራይ ልጆች ከመሞት እራሳቸዉን ማዳን አለባቸዉ!

መላዉ የክልሉ ወጣት መረዳት ያለበት ማብቂያ ላሌለዉና ዘመኑን ያልዋጀ የጦርነት አባዜ ፈጽሞ ለክልሉ ህዝብም ይሁን ለመላዉ ኢትዮጵያ እንደማይጠቅም በተጨባጭ ጉዳዩ ላይ በተለያዩ አመታተት በመኖር ከማንም በላይ ተረድቶታል፤ማለትም የግድ የአንድን ቡድን ፍላጎት ለሞሞላት ለምን እኛ እናልቃለን፤ለምን የህወሕት ልጆች በምራባዊያን ሀገራት እየኖሩ እኔ እሞታለሁ ብሎ መጠየቅና መታገል ይኖርበታል፤

እንደሚታወቀዉ ይህ ቡድን ለሶስት አስርት አመታትን ሀገርን ካስተዳደረና ከዘረፈ በሓላ በህዝባዊ አመጽ በግድ ከስልጣኑ መነሳቱ የሚታወቅ ነዉ፤
ሀገራችን ደግሞ ህወሓትን ብቻ ሳይሆን የብዙ ቡድኖች ያሉባት ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሌላዉ ሀገር ሲመራም እንደሱ ባለ መብት መሆኑን እዉቅና በመስጠት በሰላማዊ መንገድ መቃወምም ሆነ መታገል እየተቻለ በወጣቶች ደም መጫዎት ለምን?

ስለሆነም የታጠቀዉም ያልታጠቀዉም የትግራይ ወጣት እብርተኛዉን ቡድን በመታገል የራሱን ህይወት ማዳን፤የቤተሰቡን ንብረትና ኑሮ ማትረፍ እንድሁም የመላዉን ትግራይን ሰላምና ድህንነት የማረጋገጥ ታሪካዊና ትዉልዳዊ ሃላፊት አለበት፡፡

ሠራዊታችን በጀግንነት ጠላትን የሀገር ሉዓላዊነትን እየጠበቀ ይገኛል‼በጦር ሜዳ ጀግንነት ጠላትን የሚያንበረክክ፤ ወገንተኝነቱ ለህዝብ የሆነነ እና ለአንድ ዓላማ የቆመ፣ እርሱም ለሕዝብ ሰላምና...
18/09/2026

ሠራዊታችን በጀግንነት ጠላትን የሀገር ሉዓላዊነትን እየጠበቀ ይገኛል‼

በጦር ሜዳ ጀግንነት ጠላትን የሚያንበረክክ፤ ወገንተኝነቱ ለህዝብ የሆነነ እና ለአንድ ዓላማ የቆመ፣ እርሱም ለሕዝብ ሰላምና ለሀገር ሉአላዊነት አስተማማኝ ዘበኛ በመሆን ቀንና ሌሊት ማገልገል ነው። የጽንፈኞች ስብስብ በሕዝብ አንድነት መንፈስ እና በሠራዊታችን የጀግንነት ስሜት ተደርምሶ እየተበታተኑ ነው።

እነሆ ዛሬ የሀገር ሰላምና ልማት ጠላቶች በሆኑ ቡድኖች ላይ አስተማሪ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። በጀግንነት ክንድና በሀገር ፍቅር ስሜት የተሞላው፣ በጥሩ ሥነ-ምግባር የተገነባው ሠራዊታችን በሚሄድበት ቦታ ሁሉ የሕዝብን ሰላም የማረጋገጥ ሥራ እየሠራ ነው። የጽንፈኞችን እግር በመከታተል የማጥራይ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያን የባህር በር ማረጋገጥ የብሔራዊ ጥቅም እና የኢኮኖሚ ሉአላዊነት ጉዳይ ነው!የኢትዮጵያን የባህር በር ማረጋገጥ የአጭር ጊዜ ጉዳይ ሳይሆን፤ የብሔራዊ ጥቅም፣ የኢኮኖሚ ሉአላዊነት እ...
18/09/2026

የኢትዮጵያን የባህር በር ማረጋገጥ የብሔራዊ ጥቅም እና የኢኮኖሚ ሉአላዊነት ጉዳይ ነው!

የኢትዮጵያን የባህር በር ማረጋገጥ የአጭር ጊዜ ጉዳይ ሳይሆን፤ የብሔራዊ ጥቅም፣ የኢኮኖሚ ሉአላዊነት እና የመጪው ትውልድ ዕድል ነው።

ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ ብትሆንም፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገቷን ለማስቀጠል፣ ዓለም አቀፍ ንግዷን ለማጠናከር፣ የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ እና ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማሳደግ አስተማማኝ እና ዘላቂ የባህር በር ማግኘት ወሳኝ ጉዳይ ነው።

ስለሆነም ከባህር በር ጋር በተያያዘ ውይይት ማድረግ፣ ቀጠናዊ ትብብር መፍጠር እና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥቅም እና ፍላጎት ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት።

የኢትዮጵያ ሰላማዊና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄዷና ሀገራዊ ምክክር በስኬት ማጠናቀቋ የዲፕሎማሲ ተፅኖዋን እያሳደገ ነዉ!የዓለም ቁልፍ ተቋማት ፊታቸዉን እያዞሩላት መሆን፤ሀገራችን በከሄደችዉ ሰላማዊና...
17/09/2026

የኢትዮጵያ ሰላማዊና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄዷና ሀገራዊ ምክክር በስኬት ማጠናቀቋ የዲፕሎማሲ ተፅኖዋን እያሳደገ ነዉ!

የዓለም ቁልፍ ተቋማት ፊታቸዉን እያዞሩላት መሆን፤ሀገራችን በከሄደችዉ ሰላማዊና ፍትሃዊ ምርጫና ምክክር ጉባኤ የሀገሪቷን የራሶን ጉዳዮች በራሷ አቅም መፈጸም የሚያሳይና አበዳሪና ለጋሽ ተቋማትም እንደ ዓለም ባንክና የአለም ገንዘብ ፈንድ ለዴሞክራሲ ማበብ ካላቸዉ ፍላጎት ጋር ስለሚስማማ በቀጣይነት ከሀገራችን ጋር ለመስራት በተጨባጭ ፍላጎት እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

በቢሪክስ ስብሰባም ሀገራችን ከሚደመጡና ዋጋ ከሚሰጣቸዉ አባል ሀገራት ዉስጥ መሆኗ በተጨባጭ በህንድ በተደረገዉ ስብሰባ ላይ የመናገርና ሃሳቧን የማራመድ እድል መሰጠቱ የዝሁ ማሳያ ነዉ፡፡

ከኢንቨስትመንት አንጻር፤ሁለቱ ትላልቅ ሀገራዊ ኁነቶች የዉጭ ኢቨስተሮች በሀገራችን እንዲተማመኑና እንዲሳቡ በማድረጉ የዉጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እነዲጨምርና የሀገር ኢኮኖሚን እዲያሳድግ አቅም የሚሆን መሆኑ ነዉ፡፡

በቀጣናው ያላት የመፈለግ ጉዳይ፤ሀገራችን በጣም ሰላም አልባ የሆነ በአፍሪካ ቀንድ ብትገኝም ከሌሎች ጎሮቤት ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ብዙ ምራባዊያን ማለትም አሜሪካና አዉሮፓ እና ምስራቃዊያን ቻይና፤ህንድ፤ቱርኪዬና ሌሎች ከፍተኛ መሪዎቻቸዉን በመላክ የሚጎበኞት ሀገር መሆን የዲፕሎማያችንን እድገት ያሳያል፡፡
በአጠቃላይ ሀገራችን ባመጣችዉ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ለዉጥ፤በከናወነችዉ ሰላምዊና ፍትሃዊ ምርጫ በአለም ማህበረሰብ ዘንድ ትሰሚነቷና ዲፕሎማሲያዊ ተጽኖ ፈጣሪነቷ እየጨመረ መጥቷል፡፡

በመደመር መንግስት የተገነቡእ እና እየተገነቡ ያሉ ጠንካራ ተቋማት የሀገሪቱን የብልፅግና ጉዞ እያፋጠኑት ነው።የመደመር መንግሥት ሀገርን ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። የሥራዎችን ቀ...
17/09/2026

በመደመር መንግስት የተገነቡእ እና እየተገነቡ ያሉ ጠንካራ ተቋማት የሀገሪቱን የብልፅግና ጉዞ እያፋጠኑት ነው።

የመደመር መንግሥት ሀገርን ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። የሥራዎችን ቀጣይነት ማረጋገጥ የሀገርን አንድነት ለማጠናከር፣ ትውልድን ለማስቀጠልና ልማትን ዘላቂ ለማድረግ ወሳኝ ነው። ለሚቀጥለው ትውልድ ጠንካራ መሠረት የሚጥሉና ለዘመናት የሚቆዩ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መገንባታቸው የዚህ ተግባራዊ ማሳያ ነው።

በአሁኑ ወቅት በልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጡ ናቸው። የሀገሪቱ ዕድገት በተቋሞቿ ጥንካሬ ላይ እንዲመሠረትና ለትውልድ የሚሸጋገር የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ የለውጡ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ጤና መድኅን የዜጎች ዋስትና ❗️የጤና መድኅን ሥርዓት ማጠናከር ማለት ዜጎች በሕመም ጊዜ ብቻቸውን እንዳይቆሙ፣ የሕክምና ወጪ በቤተሰቦች ላይ ከባድ የገንዘብ ጫና እንዳይፈጥር እና ሕመም በጊዜ...
17/09/2026

ጤና መድኅን የዜጎች ዋስትና ❗️

የጤና መድኅን ሥርዓት ማጠናከር ማለት ዜጎች በሕመም ጊዜ ብቻቸውን እንዳይቆሙ፣ የሕክምና ወጪ በቤተሰቦች ላይ ከባድ የገንዘብ ጫና እንዳይፈጥር እና ሕመም በጊዜው ታክሞ ወደ ከባድ ችግር እንዳይሸጋገር መሥራት ነው።

የዓለም የጤና ልምድም የጤና መድኅንን ከዜጎች የጤና ጥበቃ በተጨማሪ ከማኅበራዊ ጥበቃ እና ከቤተሰብ የኢኮኖሚ ደህንነት ጋር ያገናኘዋል።

ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል የጤና መድኅን ሽፋንን ለማስፋት፣ የዜጎችን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሻሻል እና የጤና ወጪ በዜጎች ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው።

በተመጣጣኝ ዓመታዊ ክፍያ ዜጎች ለአንድ ዓመት የጤና ዋስትና እንዲኖራቸው የሚያደርገው የጤና መድኅን ሥርዓት፣ ሕመምን ከመታከም ባሻገር ቤተሰብን ከድንገተኛ የጤና ወጪ የሚጠብቅ የማኅበራዊ ጥበቃ መሣሪያ ነው።

በተለይ ዐቅመ ደካሞችንና የጤና መድኅን ክፍያቸውን መሸፈን የማይችሉ ወገኖችን መደገፍ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነታችን ነው። የግለሰቦች፣ የድርጅቶች፣ የማኅበራትና የበጎ አድራጎት ተቋማት ድጋፍ ማንም ዜጋ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ከሕክምና እንዳይርቅ ለማድረግ የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ ነው።

ጤናማ ዜጋ የጠንካራ ሀገር መሠረት ነው።
ጤናን መጠበቅ የዛሬን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የነገን ትውልድ መገንባት ነው።

ጤና ለሁሉም፤ ዋስትና ለሁሉም!

Address

Ambo
AE

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Diriba Melkamu D. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share