Wello Broadcasting Corporation

Wello Broadcasting Corporation መረጃዎችን ለ ህብረተሰቡ ማድረስ በተጨማሪም ስለ ወሎ እና አ?

እነዚህ ታዳጊዎች ዛሬ የትምህርት ቀን ሆኖ ሳለ ትምህርት ቤት መገኘት ሲገባቸው ነፃነታቸውን ለማስከበር አደባባይ ለመውጣት መገደዳቸው፤ ለትግራይና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ውድቀት ነው፤...
21/01/2025

እነዚህ ታዳጊዎች ዛሬ የትምህርት ቀን ሆኖ ሳለ ትምህርት ቤት መገኘት ሲገባቸው ነፃነታቸውን ለማስከበር አደባባይ ለመውጣት መገደዳቸው፤ ለትግራይና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ውድቀት ነው፤ ለአክሱምና መሪዎቻቸው ልዩ ውርደት ነው።

ታሪክ ይመሰክራል‼

አምባገነንነት ይብቃ‼

#ፍትህ ለሂጃብ
#ኒቃቧንም ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች

21/01/2025
21/01/2025
26/07/2024

Wello Broadcasting Corporation

Wello first

Jun 25,2024 2:01 pm ♥ወሎ የወሎዬዎች ነው♥ #ወሎ ክልል ቢሆን ማን ይጠቀማል? #ወሎ ክልል ቢሆን ማን ይጎዳል?
25/06/2024

Jun 25,2024 2:01 pm
♥ወሎ የወሎዬዎች ነው♥
#ወሎ ክልል ቢሆን ማን ይጠቀማል?

#ወሎ ክልል ቢሆን ማን ይጎዳል?

1 ሺህ 170 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱአዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016  በዛሬው ዕለት በሦስት በረራዎች በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 1 ...
17/04/2024

1 ሺህ 170 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 በዛሬው ዕለት በሦስት በረራዎች በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 1 ሺህ 170 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከሚያዝያ 4 ቀን 2016ዓ.ል ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ4 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

30/09/2023

ሰላም
የሁሉም ምርጫ ነው።

07/09/2023

ይህንንም እየሰማችሁ
ከ ልጅ ያሬድ ያነሰ
ልጅ ዲያቆን
ይህ ሰው ካልተከሰሰ የልጅ ያሬድ መከሰስ ዋጋ የለውም
ፍትህ ለሁሉም

400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ዋለ******************************  መነሻውን ጅቡቲ ወደብ፣ መዳረሻውን ወረታ ከተማ አድርጎ የተንቀሳ...
24/07/2023

400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ዋለ
******************************

መነሻውን ጅቡቲ ወደብ፣ መዳረሻውን ወረታ ከተማ አድርጎ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ አሽከርካሪው ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ህገወጥ ተግባር ሲሰራ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ህገወጥ ድርጊቱ የተፈፀመው በባህርዳር ከተማ፣ ሰባታሚት ቀበሌ ሀምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን፤ በአሳቻ ሰዓት ከሌሊቱ 6:00 የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ለግለሰቦች ሲያከፋፍል በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የሰባታሚት ቀበሌ ፖሊስ ኦፊሰር ኮንስታብል ዮሐንስ ጥላሁን ተናግረዋል።

አብዛኛው ማዳበሪያ ሳይራገፍ ከነተሽከርካሪው መያዝ ቢቻልም ከ140 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለግለሰቦች በህገወጥ መንገድ መሰራጨቱን ፖሊስ ባደረገው ክትትል ደርሶበታል።

ፖሊስ ባደረገው የቤት ለቤት ፍተሻ ከተሽከርካሪው ተራግፎ በግለሰቦች ቤት የተከዘነ በርካታ የአፈር ማዳበሪያ ማግኘቱን አስታውቋል።

89 ኩንታል ማዳበሪያ በአንድ ግለሰብ ቤት ተከዝኖ የተገኘ ሲሆን፤ 24 ኩንታል ማዳበሪያ ደግሞ በሌላ ግለሰብ ቤት በአልጋ ስር እና በኩሽና ተከዝኖ መገኘቱ ተጠቅሷል።

አሽከርካሪው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጓዘአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት 20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈ...
24/07/2023

20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጓዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት 20 ሺህ 411 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገለጸ፡፡

ማዳበሪያው በ439 ተሽከርካሪዎች እና በባቡር ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙም ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ÷ በቀጣይ ቀናት ጅቡቲ ወደብ የደረሰውን የአፈር ማዳበሪያ በአጭር ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ አጠቃሎ ለማጓጓዝ እየሠራ መሆኑን ከድርጅቱ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር ) ÷ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር አ.ማ ፣ በኢባትሎ ጅቡቲ ኤም ቲ ኤስ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ በትጋት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እና የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር አ.ማ በሀገሪቱ ወሳኝ የሚባሉ ግብዓቶችን በፍጥነትና በብዛት ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ላይ የጋራ ውይይት አድርገዋልም ነው የተባለው፡፡

Address

Ancharo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wello Broadcasting Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category