Kussita Aspiron

Kussita Aspiron This page is credible in all sources. All posts herein are trusted.
(1)

Aimed to share information on events, experience, talent, knowledge and skill from corners of the universe to the digital community.

16/04/2025

ከመጋቢት 30 የተጀመረው በልማት እና በአካባቢ ጉዳዮች ላይ ምክክር አመርቂ ለውጦችን እያመጣ ነው:: በዚህ መሰረት በሚያዚያ 8 ቀን ከዞኑ እና ከወረዳው ሲቪል ሰርቫንት ጋር የተደረገው ምክክር ትልቅ የእሳቤ ለውጥ አምጥቷል:: በዚህ መድረክ የክልሉ የብሔር ብሔረሰቦች ዋና አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አዳማ ትንጳዬ, ኮሚሽነር ፍስሃ እና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ያስተላለፉት ዋና ዋና ፍሬ ሃሳቦች: በአካባቢው ስለተፈጠረው ዘግናኝ ድርጊት ሁሉም ሰው መፀፀት አለበት, እንዲህ አይነት ድርጊት ዳግም እንዳይከሰት ሁሉም ሰው እጁን መሰብሰብ አለበት, ለተፈጠረው ቀውስ እጃቸው ያለበት ሁሉ ላይ የሕግ የበላይነት እንደሚረጋገጥባቸው, የተጉዱትን ሕብረተሰብ መልሶ የማቋቋም ሥራ በሙሉ በአጥፊዎች እና በሕዝቡ እንደሚሰራ, ከእርቅ በፊት ወንጀለኞች ተላልፎ መሰጠት እንዳለበት, የተዘረፈው ንብረት መመለስና የወደመው ንብረት በሙሉ መተካት አለበት የሚል ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል:: አያይዞም ለዲራሼ ወረዳ ልማት እንቅፋት የሚሆን ሁሉ ጠላት ነውና እርምጃ ይወሰድበታል::
በሌላ በኩል ለአካባቢው ትርምስ ምክንያት ነው ተብሎ ስለ የተለዩት:- የጉማይዴ ማንነት (ወረዳ) አስመላሽ ጉዳይ የሞተን ፈረስ መጋለብ እንደሆነ, -የወየሳ ደን ውስጥ መግባት የሞት ወጥመድ መርገጥ እንደሆነ, -የቀጠናው ህገ ወጥ ትጥቅ አሁን በህግ መልክ መያዝ እንዳለበት, -ከሰገን ዙሪያ ወረዳ ባልተገባ መንገድ ወደ ጋርዱላ ዞን የገቡ ከ400 መቶ በላይ ሰራተኞች የሌላ ሕዝብ በጀት ለደመወዝ እየተከፈላቸው ነገር ግን ከተማ ተቀምጦ አርሶ አደሩን ለጥፋት የሚያደራጁ, መዋጮ ከፍለው መሳሪያና ጥይት የሚገዙ ላይ የሕግ እርምጃ እንደሚወሰድ, - የተዛባ ትርክት እየፈጠሩ ውዥምብር በሚፈጥሩት በግጭት ነጋዴዎች (ከሰገን ዙሪያ ወረዳ አምፆ የመጣው ኃይል እና አንዳንድ አቅጣጫ የጠፋው የጋርዱላ ዞን ተወላጅ) እና ፀረ ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልፁአል::
ስለዚህ ሁሉም ሰው ከዚህ እኩይ ተግባር ራሱን ሰብስቦ መንግስት በሚያስቀምጠው የልማት አቅጣጫ ልክ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበት ተግባብተው በቀጣይ የማጥራት ሥራዎች ላይ ሲቪል ሰርቫንቱ ከመንግስት ጎን በመቆም ሙያዊ እና ቴክኒካዊ እገዛ እንደሚያደርግ ተስማምተዋል::

14/04/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የብሔር ብሄርብሔረሰቦች ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ የሚመራው ቡድን በጋርዱላ ዞን በዲራሼ ወረዳ ከመጋቢት 30/2017 ዓ/ም ጀምሮ በዞኑ ልማትና በአካባቢዉ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይገኛል:: በዚህ ምክክር ትልቅ ውጤት እየተገኘ ስለሆነ አመራር, ምሁራን, የመንግስት ሰራተኞች, አርሶ አደር, ነጋዴ, የአካባቢ ሽማግሌዎች, የእምነት ቤት መሪዎች, የሕዝባዊ አደረጃጀት መሪዎች በአጠቃላይ ሙሉ ሕዝብ ለዚህ ታሪካዊ ሥራ ቀኝ እጃችሁን ሰጥታችሁ እንድትደግፉ በታላቅ ትህትና እንጋብሳለን::

03/02/2025

የቴክኖሎጂ/ሙያዊ ሥልጣኔ እና የዘዴ/ብልሀት ልዩነት//Technology Vs Technique

ሁለቱም ስያሜዎች አንድ ነገር ለማድረግ ከሚያደርጉት ዘዴዎች ጋር ይዛመዳሉ፤ "ቴክኖሎጂ" አንድ የተወሰነ ሥራ ለማከናወን/ችግሮችን ለመፍታት ሳይንሳዊ ዕውቀትን በሰፊዉ በመጠቀም የተደረገው ልዩ ዘዴ ወይም ችሎታ ነው፤ ብልሀት ግን ብዙውን ጊዜ በትላልቅ የቴክኖሎጂ ማዕቀፍ ውስጥ ነው፤ በመሠረቱ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን እና መርሆዎችን ያካተታል፤ ቴክኒኩ/ብልሀቱ ግን ውጤትን ለማሳካት የሚጠቀሙበት የተለየ መንገድ ነው።

02/02/2025

Shonqaa‹‹ሾንቃአ››//ክራር// Lyre
Shonqaa‹‹ሾንቃአ››//ክራር// በማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ ተወዳጅና የተለመድ ባለ ስድስት ክር መሣሪያ ነው። ሕዝቡ በተለያየ ጊዜ በግለሰብ፣ በቤተሰብ አሊያም ሰብሰብ ብሎ በቡድን ደረጃ ይጫወታል። በተጨማሪም ሴት ልጅ በቅድመ ሙሽሪትነት ጊዜ//‘Helba Qoramat’// ማታ ማታ ወጣቶች በዙሪያዋ መድዶ፤ ክራር ትጫወትላቸዋለች። ማህበረሰቡ ክራርን በፖፖጋ፣ በቶሀ፣ በጭፈራ፣ በካንታሉኬ፣ ወዘተ መልክ ይጫወታል።

21/04/2024

ትግላችን ... የቀጠለ
በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ የትግል ጽንሰ ሐሳብ በዋናነት “አንዱ ሌላውን ለመጣል ወይም ለማጥቃት፣ ለማሸነፍ፣ ለመጉዳት፣ ... ወዘተ የሚያደርገው ትንቅንቅ፣ ፍትጊያ፣ ግብግብ” ላይ ያረፈ ይመስላል። እንዲህ ከሆነ የጋራ ሀገር እና ዓላማ ልኖረን አይችልም ማለት ነው። የሠፈር ነጻ አውጪ፣ የቀጠና ነጻ አውጪ፣ ወዘተርፈ ሆነን ከገምስ በላይ ጠላት በሀገር አፍርተን፤ የነጻ አውጪ ታጋይ ግን ነጻነት ናፋጊ፤ በነገ ነጻ አውጪዎች ተወጋጅ፤ በተራው ቀጣይ ለነጻነት ታጋይ፤ እንዲህና እንዲያ የእምቡሽዬ አዙሪት ውስጥ መዳከር ነው ፍሬ ነገሩ። ለነገ የማይባል የቤት ሥራችን የሚሆነው ከእንዲህ ዓይነት ትግል ወጥተን “በሐሳብ የበላይነት ወደምንጫወትበት ሜዳ” ላይ መሰለፍ ግዴታችን ነው።

Tanaw ‘Filla’ ‹‹ፊላ ጨዋታ››የ‘Filla’‹‹ፊላ›› ጨዋታ መቼት ሲጠና ተጽፎ የተቀመጠ ሠነድ ባይኖርም ወደ ኃሏ ረዘም ያለ ታሪክ ያለው ከጥንት አያቶቻችን ተወራርሰን የመጣ እንደሆን...
25/01/2024

Tanaw ‘Filla’ ‹‹ፊላ ጨዋታ››
የ‘Filla’‹‹ፊላ›› ጨዋታ መቼት ሲጠና ተጽፎ የተቀመጠ ሠነድ ባይኖርም ወደ ኃሏ ረዘም ያለ ታሪክ ያለው ከጥንት አያቶቻችን ተወራርሰን የመጣ እንደሆን ነገር አዋቂዎች ይናገራሉ። ‹‹ፊላ›› ጨዋታ የዺራሼ ማህበረሰብ እና በጋርዱላ ምድር የሚኖሩ ወንድሞቹ ከፍ ያለ የደስታ ስሜት፣ የእረፍት፣ የመርካት ሁኔታን የሚገልጹበት ባህላዊ ጨዋታ ነው። ስለሆነም የ‹‹ፊላ›› ጨዋታ የደስታ፣ የፍቅር፣ የመያያዝ፣ የአብሮነት፣ የወንድማማችነት፣ የመሳሰሉት መገለጫ ነው።
‘Filla’‹‹ፊላ›› ከቀርከሃ ወይም ከሸምበቆ የሚሠራ ባለብዙ ‘Fiilet’‹‹ፊለት›› ባህላዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። ባህላዊ ጨዋታውም የ‹‹ፊላ›› ጨዋታ ይባላል። እያንዳንዱ የ‹‹ፊላ›› ‹‹ፊለት›› እንደ ‹‹ማይራ›› ከቀኝ ወደ ግራ በቁመትም ሆነ በውፍረት (ካንድ ቀርከሃ የሚቆረጡ ስለሆነ የውፍረት ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው) የሚቀንስ ሆኖ፤ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ (‘Tontolit/Kasanit’, ‘Ensharit,) ከሌሎቹ ትንሽ በተለየ ሁኔታ የመርዘም አዝማሚያ ይኖራቸዋል። የመጨረሻዎቹ የተወሰኑት ትንንሽ ‹‹ፊለት›› ‘Fitinfitaya’ ይባላሉ። ሰፋ ሰፋ ያለ ቀዳደ አፍ ያለቸው ላይ እንደ ‹‹ማይራ›› ከቀርከሃው በጣም በአጭር አጭር የተቆረጠው አንድ ወይም ሁለት አፍ ‘Thoota’ ይገባለታል።
‘Filla’‹‹ፊላ›› በርከት ያለ ‹‹ፊለት›› (30-40 ቀሰም) ይይዛል። በጨዋታ ጊዜ ከትልቁ (‘Tontolit/Kasanit’) መንፋት ይጀመርና ቀጣዩ የመጀመሪያው ሰው ነፍቶ እንደጨረሰ ይነፋል። በእንዲህ ሁኔታ በቅብብሎሽ እየነፉ እስከ መጨረሻው ይከዳል። ‹‹ፊላ›› የሚሰጠው የተለየ ወቅተልክ (Rhythm) ከ‹‹ሎላት››፣ እልልታ፣ እና በሥርዓትና ጥበብ በሚደረግ ውዝዋዜ ጋር ተዳምሮ እጅግ መሳጭ ባህላዊ ጨዋታ ነው። ምናልባት ሴቶች በቁጥር የማነስ ካልሆነ በስተቀር የፆታ ልዩነት የማይደረግበት ጨዋታ መሆኑ ደግሞ የበለጠ ሳቢና ማራኪ ያደርገዋል።
‘Filla’ በበዓላት ጊዜ፣ በሠርግ ጊዜ እንዲሁም ‹‹ካላ›› በሥራ የሰበሰቡትን ገንዘብ በሚበሉበት ጊዜ የተደረጁ ወጣቶች ወይም ሳይደራጁም ወጣቶች ተሰብስቦ ሲጀምሩ ሰዎች ዙሪያቸው ላይ ተሰብስበው የዚህ ገራሚ ባህላዊ ጨዋታ ይካፈላሉ። በበዓላት ጊዜ የተሰበሰቡትን ሰዎች የባህል ጨዋታ ወደሚካሄድበት መስክ እያደረሰ መንደር ለመንደር እየዞሩ ሰዎችን ያሰባስባል።
በጋርዱላ ዞን 5ኛውን የ‹‹ፊላ›› ጨዋታ ክብረ በዓል ስናከብር ለመላው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደስታን፣ ፍቅርን፣ መያያዝን፣ አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን፣ ይቅርታን፣ ወዘተ የጋራ ገንዘባችን በማድረግ ጥላቻን፣ ስንፍናን፣ መናናቅን፣ ወዘተ ከመሀከላችን በማስወገድ ለሀገር ሰላም፣ ዕድገት፣ ልማት እና ብልጽግና በጋራ እንትጋ የሚል መልዕክት ለማስገንዘብም ጭምር ነው።

የሦስት መጽሐፎች አረንጓዴ፣ ብጫ እና ቀይ ቀልማት የተሞሉ 1,096 ገጾች እነሆ ዛሬ ጥር 16/2016 ዓ/ም በጌታ ምሕረት እና ቸርነት ብዛት ተገልጦ ተጠናቅቀዋል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ባደ...
25/01/2024

የሦስት መጽሐፎች አረንጓዴ፣ ብጫ እና ቀይ ቀልማት የተሞሉ 1,096 ገጾች እነሆ ዛሬ ጥር 16/2016 ዓ/ም በጌታ ምሕረት እና ቸርነት ብዛት ተገልጦ ተጠናቅቀዋል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ባደረግነው ወርቃማ ጉዟአችን ሁሉ የልዑል እግዚአብሔር ጥበቃና እርዳት ስለበዛልን፤ እንዲሁም ሁለት ሥጦታዎችን ከእርሱ ተሰጥቶን አራት ቤተሰብ ስላደረገን ወዳጆቻችን እና አድናቂዎቻችን የሆናችሁ ሁሉ ልዑል እግዚአብሔርን ከእኛ ጋር አመስግኑ።

03/01/2024

የዕውቀት፣ የጥበብ እና የመረዳት ልዩነት
ዕውቀት የምሁርነት የመጨረሻው እርከን ሲሆን ነገሮችን በስም፣ በቁጥር፣ ወዘተ የማወቅ፣ የመገንዘብ እና የማስታወስ ችሎታ ነው።
ጥበብ የምሁርነት መካከለኛው ደረጃ ሆኖ ነገር ግን በክህሎት እና ውጤታማ ኑሮ ለመኖር በጣም አስፈላጊ ነው ተብሎ ይታሰባል። የዚህ ዓይነት ምሁርነት ዕውቀትን በተግባር ላይ የማዋል ወይም የተማርነውን ወይም ያወቅነውን የመተግበር ችሎታን ያመላክታል።
መረዳት የምሁርነት ከፍተኛው ጥግ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ ያለ ሰው ነገሮችን ግልፅ አድርጎ መናገር እንዲሁም ዕውቀቱን፣ ጥበቡን እና አስተውሎቱን በመተንተን፣ እንደገና በማዋቀር እና መረጃን በመገምገም ለሌሎች ማካፈል ይችላል።

03/01/2024

ክፍል 3... የቀጠለ
ታዲያ ትልማችንን ለመገንባት፣ ለለውጥ፣ ለዕድገት እና ለልማት መሆን ካለበት ሀገርንና ፖለቲካን፣ ዛሬና ነገን፣ መንገድና ሜዳን፣ ስልትና ሥርዓትን በአግባቡ አጥርቶ መለየት ተገቢ ይሆናል። ብዙዎቻችን ትናንትና ስንጫወትበት የነበረው ኳሱና ሜዳው ለነገዋ ኢትዮጵያ ገጽታ ግንባታ በሚሆን መልኩ ሳይሆን መንግሥትንም ሆነ ማህበረሰብን በማጥላላት፣ በማንቋሸሽ፣ አልፎም በመሳደብ እንዲሁም የተሠራውን ከልክ በላይ በማኳንሰስ፤ ጉድለቶችን ከልክ በላይ ለጥጦ በማግነን የሁለት ወይም ከዚያም በላይ ሀገራት ሰዎች ሆነን ነበር።
እንዲህ ዓይነት የእኛ እና የእነርሱ ተረክ የጋራ የሆነ ታላቅ ትርክት አሳጥቶናል፤ እያሳጣንም ይገኛል። የትናንትና ታሪካችን እንደሚያስረዳን በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚውም አንድ የጋራ ማህበረሰብ መገንባት ላይ ሰፊ ክፍተት እንዳለብን፤ ሀገርን እንመራለን ብሎ የሚደራጁት ፓርቲዎች ሁሉ ከስም ስያሜዎቻቸው ጀምሮ እስከ ተግባሮቻቸውም ጭምር አግላይ፣ አሳታፊነትና አካታችነት የሌላቸው ነበሩ፤ አሁንም አሉም።
በሌሎች ሀገራት ከአፍሪካ ሀገራት ውጭ ሀገር እና ዓላማ ዕንቁ የጋራ ፈርጦቻቸው ናቸው። ስለዚህ የሚደረገው ማንኛውም ትግል በሐሳብ ልዕልና ወይም በመታገያ ስልት ላይ ይሆናል ማለት ነው። የተሻለ ሐሳብ በተመረጠ የመፈጸሚያ ስልት ወይም ሥነ-ዘዴ (Methodology) የተቀመርው ገዢ ይሆናል። የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መመሥረቻ መነሻ ሐሳባቸውም በእነዚህ በሁለቱ ጽንሰ ሐሳቦች ላይ ያጠነጠነ ይሆናል ማለት ነው።

11/12/2023

ከክፍል 1 ... የቀጠለ ሁሉም ሀገራት በለውጥ እና ዕድገት ምዕራፎች አልፎ ካደጉት ተርታ መመደባቸው አይቀረ ጉዳይ መሆኑ ቢታመንም የሀሳብ፣ የጊዜ፣ እና የቦታ አጠቃቀም ሁኔታን ሊያፈጥን ወይም ሊያዘግይ ይችላል። ሀሳባቸውን፣ ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን ሰብሰብ አድርጎ እምቅ አቅማቸውን ... ሙሉ ሃሳቡን ለማግኘት ልንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/infoforal

This page is credible in all sources. Aimed to share information on events, experience, talent, knowledge and skill from corners of the universe to the digital community. All posts herein are trusted.

10/12/2023

ከክፍል 1 .... የቀጠለ
ሁሉም ሀገራት በለውጥ እና ዕድገት ምዕራፎች አልፎ ካደጉት ተርታ መመደባቸው አይቀረ ጉዳይ መሆኑ ቢታመንም የሀሳብ፣ የጊዜ፣ እና የቦታ አጠቃቀም ሁኔታን ሊያፈጥን ወይም ሊያዘግይ ይችላል። ሀሳባቸውን፣ ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን ሰብሰብ አድርጎ እምቅ አቅማቸውን በጊዜ አውቆ በትክክለኛ ቦታ ላይ ያዋሉት ሀገራት በኢኮኖሚውም ሆነ በእሳቤ ልቀት አድገዋል፤ እያደጉም ይገኛሉ።
በታሪክ ቅብብሎሽ ውስጥ ከታሪክ መዛግብት ትንተና ወይም ከህያው ምስክሮች የምንገነዘበው የሰው ልጅ በትግሉ ያስመዘገበው የዕድገት ውጤቶች ይለያያል። ትግሎች እንደ ዘመኑ ሁኔታ፣ ሥልጣኔ፣ ሰዎች የደረሱበት መረዳት እንደሚለያዩ ሁሉ ዓላማቸው፣ ይዘታቸው፣ ስልታቸውና አውዳቸው ይለያያል። የብዙ ትግሎች ዓላማ ለመገንባት፣ ለለውጥ፣ ለዕድገት፣ ወዘተርፈ ሲሆን፤ ለማፍረስ፣ ለማደናቀፍ፣ ለመጣል፣ ሌሎች ላይ በኃይል ለመጫን፣ ወዘተርፈ የሚደረጉም ትግሎች ጥቂቶች ኣይደሉም።
ትግል የአንድ አካባቢ፣ የክፍለ ሀገር፣ የሀገር፣ ወይም የሀገራት ጥምረት ይዘት ኖሮት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ እንደምታን አንግቦ ሰዎች በተለያዩ መታገያ ስልቶች ሊተባበሩ ይችላሉ። የሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ የአካባቢያችን ጋርዱላ ዞን የሚታዩ የትግል አውዶች ከእነዚህ የተለየ አይደሉም። እንደ አንድ ሀገር ዜጋ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ በተለይም ደግሞ ምጡቅ ምሁራንና መሪዎች ጋር “በድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ሁኔታ መያያዝ፣ መተባበር፣ መደማመጥ፣ መረዳዳት ለአዎንታዊ ውጤት የጎላ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው በሕብረ ብሄራዊነትና በወንድማማችነት እሳቤና ተግባር ማዕቀፍ ውስጥ መሆን የውደታ ብቻ ሳይሆን የግዴታም ጭምር ይሆናል።
#የኢትዮጵያ #የኢትዮጵያ

Address

Arba Minch
Arba Minch'
4000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kussita Aspiron posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kussita Aspiron:

Share