MULE HASID

MULE HASID የእግዚአብሔር አብ ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ጥልቅ ጥበብ ነዉ ለእኛ ለምንድን
ግን በጥልቀት ተገልጦልናል። 🔥🔥🔥🔥🔥😍😍😍

 📌 በየትኛዉ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ለይ ቆመዉ እንደሆነ ባይታወቅም ግን ቄሱ(OJ) ኢየሱስ ገልበጥ ሲል አብ ገልበጥ ሲል ደግሞ ስጋ ነዉ ብለዉናል።ለዚህም ነዉ ይሄንን ጥቅስ በዚህ መልኩ ሚ...
08/03/2026



📌 በየትኛዉ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ለይ ቆመዉ እንደሆነ ባይታወቅም ግን ቄሱ(OJ) ኢየሱስ ገልበጥ ሲል አብ ገልበጥ ሲል ደግሞ ስጋ ነዉ ብለዉናል።

ለዚህም ነዉ ይሄንን ጥቅስ በዚህ መልኩ ሚተረጉሙት

📖 “በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤”
— ቆላስይስ 2፥9

ይሄንንም ይጨምሩበታል

📖 “እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥”
— ዕብራውያን 1፥3

✍️ እነኚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ገልበጥ ገልበጥ ሲል ተብለዉ ሚብራሩ ናቸዉ እንግዲህ። አብ የማን ባህሪ ምሳሌ ሆኖ ነዉ ሚታየዉ? ምክንያቱም በኢየሱስ ስጋ የተገለጠዉ አብ ነዉ ስለምትሉን ይህንን መጠየቅ አለብን። የማንስ ባህሪ ምሳሌ ነዉ የሆነዉ?

📌 ኢየሱስ ገልበጥ ሲል አብ አይደለም ይሄ የትምህርት መፍገምገም ነዉ እዉነት አይደለም OJዎች ተመለሱ።

📌 ኢየሱስ ራሱ አዕማድ ለሆነዉ ለሐዋርያው ጴጥሮስ ያለዉ
" " የሚለዉ እንደሆነ ከሆነ ቄሶቻችሁ ከየት አምጥተዉ ነዉ ታዲያ ኢየሱስ ገልበጥ ሲል አብ ገልበጥ ሲል ደግሞ ስጋ ነዉ የሚሉት? ከዚህ በላይ የትምህርት መፍገምገም የለም።

08/01/2026

ከክርስቶስ ልደት ምን ተማራችሁ??

07/12/2025
 #ልሳን 📖 1ኛ ቆሮንቶስ 14¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁶ አሁን ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ ም...
21/11/2025

#ልሳን

📖 1ኛ ቆሮንቶስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ አሁን ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?
⁷ ነፍስ የሌለበት ነገር እንኳ ዋሽንትም ክራርም ቢሆን ድምፅ ሲሰጥ የድምፁን ልዩነት ባይገልጥ በዋሽንት የሚነፋው ወይስ በክራር የሚመታው መዝሙር እንዴት ይታወቃል?
⁸ ደግሞም መለከት የማይገለጥን ድምፅ ቢሰጥ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?
⁹ እንዲሁ እናንተ ደግሞ የተገለጠውን ቃል በአንደበት ባትናገሩ ሰዎች የምትናገሩትን እንዴት አድርገው ያስተውሉታል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁና።

📌 አሁን ለይ አብዛኛዉ ሰዉ ምን ይላል? ልሳን ተናጋሪዉን ያንጻልና በመንፈስ ቅዱስ አትቀልድ። መጽሐፉ ካለ/ካዘዘዉ ውጪ እያደረገ ያለዉን ምን ሊሉት ነዉ እኛ በማህበር ውስጥ የማይተረጎም ልሳን አትናገሩ ብለን የቃሉን ትዕዛዝ ተናግረን እንዲህ ከተባልን? ይላሉ ሌለኞቹ።

✍️ አሁን መረዳት ያለብንን አንድ ትልቅ ነገር እንመልከት እስቲ፦

📖 1ኛ ቆሮንቶስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በዓለም ምናልባት ቁጥር የሌለው የቋንቋ ዓይነት ይኖራል ቋንቋም የሌለው ሕዝብ የለም፤
¹¹ እንግዲህ የቋንቋውን ፍች ባላውቅ ለሚናገረው እንግዳ እሆናለሁ፥ የሚናገረውም ለእኔ እንግዳ ይሆናል።

✍️ ነጮች ወደ እኛ ሀገር ለአገልግሎት በሚመጡበት ጊዜ በገዛ ቋንቋቸው ቢያገለግሉ አስተርጓሚ ባይኖር ቋንቋዉን የማናዉቅ እኛ ምን ዓይነት መልስ የምንሰጥ ይመስላችኋል? ልክ እንደዚህ ነዉ በማህበር ውስጥ የሚነገር ልሳን እስካልተተረጎመ ድረስ ለእኛ የማይገባን። ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ዘግቶታል፣

📖 1ኛ ቆሮንቶስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
¹⁵ እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ።
¹⁶ እንዲያማ ካልሆነ፥ አንተ በመንፈስ ብትባርክ ባልተማሩት ስፍራ የተቀመጠው የምትለውን ካላወቀ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ አሜን ይላል?
¹⁷ አንተማ መልካም ታመሰግናለህ፥ ሌላው ግን አይታነጽበትም።
¹⁸ ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
¹⁹ ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።

✍️ ስለዚህ ከቃሉ ትዕዛዝ ውጪ መሆን አመጽ ነዉና ትዕዛዙን እንጠብቅ።

📖 “ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥20

ሌሎች የሮም መንገዶች ናቸዉ“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥”  — ዕብራ...
12/04/2025

ሌሎች የሮም መንገዶች ናቸዉ

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥”
— ዕብራውያን 10፥19-20

ወደ አብ መድረሻዉ መንገድ አንዱ ኢየሱስ ብቻ ነዉ። መንገዶች ሁሉ ወደ ሮም ይወስዳሉ እንደሚሉት ማሪያምና ቅዱሳን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አያደርሱም። መንገድም አይደሉም።

እና አሁንም አስረግጬ መናገር የምፈልገዉ ትልቁ ጉዳይ፦ መንገዶች ሁሉ ወደ ሮም እንጂ ወደ ዘለዓለም ህይወት አይወስዱም። ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏል፦

“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
— ዮሐንስ 14፥6

በቃ ሌላዉ መንገድ ወደ ሮም ኢየሱስ ብቻዉን ግን ወደ አብ የሚወስደን መንገዳችን ነዉ።
አሜን!!!!

https://t.me/betibeblihiketwbhhjdvxfhikkmnvc

በጥበብ ላቅ ያለ ህይወትን በማስተዋል መኖር።

ሙሌ የአባቱ ልጅ ደም ውጤት

25/01/2025

“በአንድ ጊዜ ሰንፈዋል፥ ደንቍረውማል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት የእንጨት ነገር ብቻ ነው።”
— ኤርምያስ 10፥8

23/01/2025

ወገኖቼ እየሱስ ይመጣል
ተዘጋጅታቹሃል???

15/01/2025

እግዚአብሔርን ምን ያህል ታውቁታላችሁ???

ምላሻችሁስ ምን ይመስላል???

በጌታ ፍቅር በትህትና መልሱልኝ።

1ዮሐንስ መልእክት - 2 : 3 - 5 ውስጥ ራሳችሁን እዩና መልሱ

11/01/2025

ምንም ማንም ክፉ ቢሆን
እኔ እንደሆን ደስታዬ
በጌታ ሙሉ ነዉ።
እርሱ ደስታዬ ደግሞ ሊመጣ ነዉ።😊😊

Address

Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MULE HASID posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share