17/10/2025
አስደሳች የሚዲያ ጥቆማ !!
የዳራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት የፌስቡክ ገጽ ይፋ ሆነ
========
የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት አካል የሆነው የዳራ ማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት በይፋ የፌስቡክ ሚዲያ ገጽ ከፍቶ ወደ አገልግሎት ገብቷል። ይህ ገጽ በዋናነት ከሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ጋር በመተባበር የሚከናወኑ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን፣ አገልግሎቶችን እና ወቅታዊ ጉዳዮችን ለምዕመናን በጊዜና በፍጥነት ለማድረስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ አዲስ የተከፈተ የሚዲያ ገጽ የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በያዘው የአስር አመት መሪ እቅድ ውስጥ የሚዲያ ተደራሽነትን ማስፋት እና መረጃዎችን በፍጥነት ወደ ምዕመናን ማድረስ የሚለውን ግብ ለማሳካት እንደሚያግዝ ተመላክቷል።
በዚሁ እቅድ መሰረት፣ በሀገረ ስብከቱ ስር የሚገኙ ሌሎች ወረዳ ቤተክህነቶች፣ የተመረጡ አድባራትና ገዳማትም በቅርቡ የየራሳቸውን ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እንደሚከፍቱ እና ወደ ስራ እንደሚገቡ ይጠበቃል።
የዳራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሚዲያ ከቁጫና ቁጫ አልፋ ፣ከኮንሶ ዞን ፣ከሠገን ፣ከምዕራብ አባያ ከነዚህ ከአራቱ ወረዳ ቤተ ክህነቶች ሚዲያ ቀጥሎ በአምስተኛነት ከተከፈቱት ሚዲያዎች አንዱ ነው።
የዳራማሎ ወረዳ ቤተክህነት ይፋ ባደረገው መልዕክት፣ ምዕመናን አዲሱን የፌስቡክ ገጽ like፣ share እና follow በማድረግ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ "በእግዚአብሔር ስም" ጥሪ አቅርቧል።
ይህ ሚዲያ በሀገረ ስብከቱ መመሪያ ሰጪነት በምዕራብ አባያ ወረዳ ቤተ ክህነት እውቅናና ፍቃድ የተከፈተ በመሆኑ፣ ምዕመናን የሚዲያው ተከታይ እንዲሆኑ እና እንዲያግዙም በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61582382014530