ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት

  • Home
  • ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት

ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት በመቅደስህ ለዘላሌም እንድንኖር እርዳን

''ወደየት ነህ ስትለኝ'' በማፍርበት ቦታ እንዳልገኝ እርዳኝ

የደበበ እስጢፋኖስ ከዲቁና እስከ ቅስና ያለውስልጣነ ክህነት መሻሩን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አስታወቁ ።==================================ሐምሌ7ቀን 2017 ዓ.ም +++++++...
14/07/2025

የደበበ እስጢፋኖስ ከዲቁና እስከ ቅስና ያለው
ስልጣነ ክህነት መሻሩን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አስታወቁ ።
==================================
ሐምሌ7ቀን 2017 ዓ.ም
++++++++++++++

የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ
አቡነ ፋኑኤል ሐምሌ 7ቀን 2017 ዓ/ም በቁጥር ሀ/ስ/053/17 በጻፉት ደብዳቤ የደበበ እስጢፋኖስን ከዲቁና እስከ ቅስና ያላቸውን ሥልጣነ ክህነት መሻራቸውን አስታወቁ።

ብፁዕነታቸው በደብዳቤያቸው እንደገለጹት ሰኔ 23,2017 ዓ.ም በቁጥር ሀ/ስ/050/17 በተጻፈ ደብዳቤ ደበበ እስጢፋኖስ ክብረ ክህነትን በሚያጎድፍ ድርጊት ስለተጠረጠሩ ጉዳዩ እስኪጣራ እንዲሁም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው አስፈላጊውን የዘረመል (DNA) ምርመራ አድርገው ነገሩ እስኪረጋገጥ ድረስ ስልጣነ ክህነታቸው ቀደም ሲል ተይዞ እንደነበር አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ ደበበ እስጢፋኖስ የእግድ ደብዳቤውን ወደ ጎን በመተው በንቀትና በድፍረት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ጥሰዋል።
ያሉት ብፁዕነታቸው በፍትሀ ነገሥት አንቀጽ 6 ቁ.228”ቄስ ወይም ዲያቆን ኤጴስ ቆጶሱን ቢንቀው ብቻውን ቤተ መቅደስ ቢሰራ እርሱ ከማዕረጉ ይሻር ተከታዮቹም ይሻሩ በሚለው ድንጋጌ እና ” በፍት.አን.6 ቁ.227”በታወቀች ኃጢአት በእርግጥ የተሻረ ቄስ ወይም ዲያቆን ቢኖር ከዚህም በኋላ ቀድሞ ሳይሻር በሰሞኑ ወራት ይሠራው የነበረውን የአገልግሎት ሥራ ተደፋፍሮ ቢሠራ ከቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ ይለይ ሥራውንም እያወቀ ከርሱ ጋር አንድ የሆነ ሁሉ ይሻር” በሚለው ሕግ መሠረት ለሕግ ተገዢ ባለመሆናቸው እንዲሁም ክህነታቸው መያዙን እያወቁ በዕለተ ሰንበት ሰኔ 29 ቀን እንዲሁም ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በድፍረትና በማን አለብኝነት ቀድሰው በማቁረብ ቀኖና ቤተክርስቲያንን መሻራቸውን ብፁዕነታቸው በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።

ስለዚህ ከዲቁና እስከ ቅስና ያላቸው ክህነት የተሻረ መሆኑን የገለጹት ብፁዕነታቸው ከደበበ እስጢፋኖስ ጋር አብሮ የሚቀድስ ዲያቆንም ሆነ ቄስ በቀኖናው መሠረት ከክህነቱ የሚሻር መሆኑን ገልጸው ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ክህነቱ ከተሻረ ጋር ሕብረት ካደረጉ የሚወገዙና ከምእመናን አንድነት የሚለዩ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።ብለዋል።

አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትም ይህንን ቀኖናዊ ውሳኔ
አክብረው እንዲሰሩ በጥብቅ እናሳሰባለን። በማለት የገለጹት ብፁዕነታቸው የደብረ ቁስቋም ቅ/ማርያም አስተዳደር፣ ካህናትና ምእመናን ስለ ቀጣዩ የቤተክርስቲያኑ አገልግሎት ምክክር ለማድረግ ወደ ሀገረ ስብከቱ መምጣት እንደሚኖርባቸው በዚሁ ደብዳቤ በግልባጭ የታዘዙ መሆኑን እናሳውቃለን።
በማለት በጥብቅ አስታውቀዋል።
ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት@topfans

14/07/2025

እሾ ሳይወጋን እንቅፋት ሳይመታን እንዲሁም ነፍሷ ከሥጋ ሳትለይ በሠላም ያዋሉን ሥላሴዎች እስክ አመስግኑዋቸው🙏😍💚

13/07/2025

✅✝️የቅድስት ስላሴ መዝሙር 🎵🎶ጋብዙኝ ☝️☝️☝️❕

13/07/2025

እንኳን አደረሳችሁ!!!!!🙏💚❤
ነገ0️⃣7️⃣ አብርሃምና ሣራ ስላሴን በቤታቸው ተቀብለው ያስተናገዱበት አመታዊ ክብረ በዓል ነው። ሥሉስ ቅዱስ ከሁላችሁ ጋር ይሁንልን🙏😘

ሰማዕቷ ትጠብቃችሁ!!❤🙏
12/07/2025

ሰማዕቷ ትጠብቃችሁ!!❤🙏

12/07/2025

ነገ 0️⃣6️⃣ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ወራዊ መታሰቢየ በዓሏ ነው ከክፉ ነገር ከሰይጣን ጤላትነት ሁሉ እርሷ በምልጃዋ ትጠብቃችሁ😍🙏

11/07/2025

የሁሉ ሰማዕታት በረከታቸው ይደርብን!!

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ውሎ አዳራቸውን ጎዳና ላደረጉ ወገኖች ከ100ሺ ብር በላይ ወጪ በማውጣት የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ።ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]የወላይታ...
11/07/2025

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ውሎ አዳራቸውን ጎዳና ላደረጉ ወገኖች ከ100ሺ ብር በላይ ወጪ በማውጣት የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ።

ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ''የጎዳና ልጅ የለውም ሰዎች ሁሉ የሰው ልጆች ናቸው'' በሚል ሀሳብ ወላጅ አጥ ልጆችን ከጎዳና ለማንሳትና ወደ ህብረተሰብ ለመቀላቀል የተጀመረው ተግባር ላይ የወላይታ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ለማገገሚያ ማዕከል ለመኝታ አገልግሎት የሚሆን ቁሳቁስ ከ100ሺ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በጎነት ለመሥራት ሃይማኖት፣ ቀለም እና ጎሳ ሳንለይ ዋጋውን ከእግዚአብሔር ለማግኘት የሁልጊዜ ተግባር አድርገን መስራት ይገባናል ብለዋል።

የተራቡትን በማብላት፣ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የተቸገሩትን በመረዳት፣ ለችግረኛና ለምስኪን በማሰብ፣ ሕሙማንን በመጠየቅ ዋጋውን ከሰው ሳንጠብቅ ከእግዚአብሔር ለማግኘት ሁሉም ማህበረሰብ በዚሁ በመልካም ሥራ ላይ መሳተፍ እንዳለበት ብፁዕነታቸው አሳስበዋል።

በዕለቱ ብፁዕነታቸው ላበረከቱት ድጋፍ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በከተማው ህዝብ እና በራሱ ስም የላቀ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ።

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ያበረከቱት ድጋፍ ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩት ከንቲባዋ ሌሎችም በከተማችን የሃይማኖት ተቋማት ተሞክሮን በመውሰድ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ከንቲባዋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ረ/ፕ ዘገየ ጳውሎስ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ከሃይማኖታዊ ተግባራት ባሻገር በከተማችን በማህበራዊ ዘርፉ በሰው ተኮር ተግባራት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተጋላጭ የጎዳና ልጆች ላደረጉት አሰተዋጽዖ ምስጋናቸውን ገልፀው ለሌሎችም ቤተ እምነት ጥሩ ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ያበረከቱትን ድጋፍ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም እና የከተማው የመንግስት ዋና ተጠሪ ረ/ፕ ዘገየ ጳውሎስ ጨምሮ የከተማው ሴቶች ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት ዮሐንስ በተገኙበት አበርክተዋል።

©እጨጌ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

🎤🎤>እንዲህ በቅዳሴው ዜማ የሚታወጅ  በአለም መድረክ ላይ ተዋህዶ ናት  ✝️✝️🙏🙏
11/07/2025

🎤🎤>እንዲህ በቅዳሴው ዜማ የሚታወጅ በአለም መድረክ ላይ ተዋህዶ ናት
✝️✝️🙏🙏

 #ጴጥሮስ ሆይ ቤተክርስቲያን ያንተን ውሌታ አልራሳትም እኛም ዛሬ ጼጥሮሳዊያን እስከ ዘላሌም ዝክርህን እየዘከርን እንኖራለን👏❤
11/07/2025

#ጴጥሮስ ሆይ ቤተክርስቲያን ያንተን ውሌታ አልራሳትም

እኛም ዛሬ ጼጥሮሳዊያን እስከ ዘላሌም ዝክርህን እየዘከርን እንኖራለን👏❤

 ። 👏💞💕ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴጥርስ ማለት ኰኩሐ ሃይማኖት ማለት ነው። ማቴ. ፲፮፡፲፰ (16፡18) በዕራይስጥ ኬፋ ይለዋል። ቀዳሚ ስሙ...
11/07/2025



👏💞💕

ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴጥርስ ማለት ኰኩሐ ሃይማኖት ማለት ነው። ማቴ. ፲፮፡፲፰ (16፡18) በዕራይስጥ ኬፋ ይለዋል። ቀዳሚ ስሙ ስምዖን ነው። ዮሐ.፩፡፵፭ (1፥45)፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል። እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መነኸርያ በነበረችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡

ከዚያም በኋላ በዚያ ከተማ ቤት ሰርቶ ኮን ኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱ እንደ ዮና ይተዳደር የነበረው ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ነበር። ዓሣ እያጠመደና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗለ። ማቴ. ፬፡፲፱ (4:19) ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኋላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን ዕዳ በዕዳ ከተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋያ ነውና ሮምን ደርቦ ሰርቶታል።

በሮምም ፳፭ (25) አስተምሯል። ከዚያ በፊ ግን በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣በቀጳዶያና በቢታኒያ አስተምራል። በትምህርቱም ጣቢታ ከሞት አስነስቷል። ሐዋ. ፱፡፴፪-፴፬ (9፡32¬-34) ያስተማራቸው ምዕመናም ከሃማኖታቸው እንዳይወጡ ፪ (2) መዕክታትን ጽፎላቸዋል። ንጉሱ ኔሮን ቄሳር ጣኦት አምላኪ ነበርና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር። ለጣዖትም እንዲሰግድ ባስገደደው ጊዜ ለጣኦ አልሰግድም በማለቱ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት።

አይሁድ ሲጣሉት ወደ ጌታ ቢያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር። ይዞ ዳግም ቢሰቅሉትም ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው። በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅሎታል። ሥጋውን ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንቦ እንዳይፈርስ በማረ በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

እንዴት አደራችሁ?  ቤተሰብ ክረምቱም እንዴት ነው??💚😍ፈጣሪ ይመስገን ነው ሁሌ መልሳችን💚🙏😍
11/07/2025

እንዴት አደራችሁ? ቤተሰብ ክረምቱም እንዴት ነው??💚😍

ፈጣሪ ይመስገን ነው ሁሌ መልሳችን💚🙏😍

Address


Telephone

+251938784121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share