Addis Mereja

Addis Mereja Visit us for reliable information

   በ2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታ...
17/09/2024



በ2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ ጥሪ ቀርቧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት ነው የሚቀበሉት።

የትምህርት መስኮቹ ምን ምን ናቸው ?

/ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ /

#ኢንጂነሪንግ ፦ አርክቴክቸር፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ፣ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሮ መካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ፣ ማይኒንግ ኢንጂነሪንግ ፣ ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

#አፕላይድሳይንስ ፦ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ፣ ፉድ ሳይንስ፣ አፕላይድ ኒውትሪሽን ፣ ጂኦሎጂ፣ ባዮቴክኖሎጂ

/ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ /

#ኢንጂነሪንግ ፦ አርክቴክቸር፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ፣ ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ ፣ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፣ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ ኢንጂነሪንግ፣ ሶፍት ዌር ኢንጂነሪንግ

#አፕላይድሳይንስ ፦ አፕላይድ ቦዮሎጂ፣ አፕላይድ ኬሚስትሪ፣ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ፣ ፋርማሲ፣ አፕላይድ ፊዚክስ ፣ አፕላይስ ጂኦሎጂ፣ አፕላይድ ማቲማቲክስ

የምዝገባ ጊዜ፡- ከመስከረም 06 እስከ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሆነ ተገልጿል።

ምዝገባው የሚጠናቀቀው መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ ነው።

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et / www.astu.edu.et ድረገጽን በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን በድህረ ገጽ የምዝገባው ቀን ካበቃ በኋላ ይደረጋል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ ፤ በምዝገባ ወቅት በመረጡት ዩኒቨርሲቲ (የፈተና ጣቢያ) በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

NB. ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ ሲሆን የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው አመልካቾች ይህን አውቀው ቅድሚያ እንዲመዘገቡ ተብሏል።

17/09/2024
03/09/2024

የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ.

13/08/2023

ጋሞ ዞንን የወከሉት ይህን ሰምተዋል?!🙄



" ሠልፉ የተከለከለው ለማፈን ሳይሆን የሕዝቡ ጥያቄ በውይይት በመፈታቱ ነው " - ኮማንድ ፖስት

በከምባታ ጠምባሮ ዞን በቡድን መንቀሳቀስና መሰብሰብን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎች ተጣሉ።

ማምሻውን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት አስቸኳይ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫው በነገው እለት የሚካሄድ ምንም አይነት ሠላማዊ ሰልፍ የለም ብሏል።

" የሀገሪቱን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተካተቱ ክልከላዎችንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነገ በዱራሜ የሚካሔድ ሰልፍ እንደማይኖር ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።

የሰልፉ ዓላማ ከቢሮ ቁጥር ማነስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ ከክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት አፋጣኝ ምላሽ እንዳገኘ በመግለጫው ጠቁሟል።

በዱራሜ ተፈቅዶ የነበረው ሠላማዊ ሠልፍ የተከለከለው " ለማፈን ሳይሆን የሕዝቡ ጥያቄ በውይይት በመፈታቱ ነው " ሲል የገለፀው የዞኑ ጊዜያዊ ኮመንድ ፖስት ከሰዓት ጀምሮ በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች ተከልክለዋል ያላቸውን ተግባራት አሳውቋል።

- በቡድን መንቀሳቀስና መሰብሰብ ተገድቧል።

- ከሰልፉ ጋር በተያየዘ ቀስቃሽ መልዕክት የያዙ አልባሳት፣ ባነሮችና ጽሑፍፎችን መጠቀም ተከልክሏል።

- ከጀምሮ የባለ 2 እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል።

- በሁሉም አካባቢ ለአፍታም ቢሆን የንግድ ተቋማትና የመንግስት መሥሪያ ቤቶች መደበኛ ሥራ መቆም እንደሌለበት አሳስቧል።

በየአቅጣጫው በፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እንደሚደረግም ገልጿል።

በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለሚፈጠሩ ጥሰቶች መንግስትም ሆነ የፀጥታ ኃይል ኃላፊነት አይወስዱም ሲል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን፤ ከ ' ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ' የተቋማት ድልደላ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬታ አለ።

የቅሬታው ምንጭ፤ በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ተቋም አላገኘም፤ ሚዛናዊ ያልሆነ የቢሮዎች ክፍፍል ነው የተደረገው የሚል ነው።

ክፍልሉ እኩል የመልማት፣ የመበልፀግና የማደግ መብትን የሚገድብ በመሆኑ እንዲታረም ነው እየተጠየቀ ያለው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለነገ ጥዋት ከ3 - 5 ድረስ የሚቆይ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቶ ነበር፤ ሰልፉም እየተፈፀመ ያለውን ኢፍትሐዊ አሰራር ለመቃወም ሲሆን፦
👉 ፍትሕ ለተጨቆነው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ህዝብ
👉 12 ለ 1 የክላስተር ቢሮ ሽንሸናን እናወግዛለን
👉 የዞናችን ህዝብ ያነሳው የኢ-ፍትሃዊነት ጥያቄ ሳይመለስ በክልል ምስረታ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አካላት ህዝባችንን አይወክሉም
👉 በከምባታ ጠምባሮ ዞን ላይ እየተፈፀመብንን ያለውን ኢፍትሃዊነት አጥብቀን እቃወማለን የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች ለማስተላልፈ ዝግጅቶች ተደርገው ነበር።

ይህ ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ እውቅና አግኝቶ ዝግጅቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኃላ ዛሬ ፍቃዱን የሰጠው የከተማው አስተዳደር ሰልፉ መሰረዙን ይፋ አድርጓል።

ዞኑ ባወጣው መግለጫ፤ የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት ከደቡብ ክልል አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ቢሮዎች እንዲጨመሩ ከስምምነት ደርሰዋል ሲል ገልጿል።

ለዱራሜ ከተማ እንዲጨመሩ የተወሰኑት ቢሮዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስፈፃሚ መ/ቤቶችን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በሚወጣው አዋጅ ተካትተው ከሌሎች የክላስተር ማዕከላት እኩል ሥራ እንዲጀምሩ እንደሚደረግም ነው ዞኑ ያሳወቀው።

በዚህም መነሻ ነገ ሰልፍ እንደማይደረግ ገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ምን ያህል ቢሮ እንደተጨመረ ግልጽ አይደለም

የ13 ዓመት ልጅ ከመደብር ዳቦ ሲሠርቅ እጅ ከፍንጅ ተያዘ። ከተያዘበት ሊያመልጥ ሲሞክር የመደብሩ መደርደሪያ ወድቆ ተሰበረ።ዳኛው የወንጀሉን ዝርዝር ሰማና ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው!👨‍⚖️"...
24/07/2023

የ13 ዓመት ልጅ ከመደብር ዳቦ ሲሠርቅ እጅ ከፍንጅ ተያዘ። ከተያዘበት ሊያመልጥ ሲሞክር የመደብሩ መደርደሪያ ወድቆ ተሰበረ።
ዳኛው የወንጀሉን ዝርዝር ሰማና ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው!

👨‍⚖️"የሆነ ነገር፥ ማለትም ዳቦ ሰርቀህ ነበር?"

🧑‍🦲ልጁ - (እያፈረ) "አዎን ሰርቄአለሁ"

👨‍⚖️ዳኛው - "ለምን?"

🧑‍🦲ልጁ - "አስፈልጎኝ"

🧑‍⚖ዳኛው - "መግዛት አትችልም ነበር?"

🧑‍🦲ልጁ - "ገንዘብ አልነበረኝም"

🧑‍⚖ዳኛው - "ከቤተሰብህ ለምን አትወስድም?"

🧑‍🦲ልጁ - "እናት ብቻ ናት ያለችኝ፥ እሷም በጠና ታምማ እቤት ተኝታለች"

🧑‍⚖ዳኛው - "ምንም ስራ የለህም?"

🧑‍🦲ልጁ - "መኪና እጥበት እሰራ ነበር፥ ነገር ግን እናቴን ለማስታመም አንድ ቀን ከስራ ስቀር አባረሩኝ"

🧑‍⚖ዳኛው - "ሌሎች እንዲረዱ አልጠየቅኽም?"

🧑‍🦲ልጁ - "በጧት ነው ከቤት የወጣሁ፥ እንዲረዱኝ 50 የሚሆኑ ሰዎች ጋ ሄጄ ነበር፤ አንድም የሚረዳኝ ሰው ግን አላገኘሁም፤ በቃ መጨረሻ ላይ ይህንን መጥፎ ውሳኔ ወሰንሁ"።

ጥያቄው ሲጠናቀቅ #ዳኛው ውሳኔ ማስተላለፍ ጀመረ።

#ውሳኔ🧑‍⚖

"ዳቦ መስረቅ፥ በተለይ የተራበ ልጅ ዳቦ መስረቅ እጅግ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው፤ እናም እኛ ሁላችንም የዚህ ወንጀል ተጠያቂ ነን። እኔን ጨምሮ በዚህ ቤት ውስጥ ያላችሁ በሙሉ ወንጀለኛና ተጠያቂ ነን። ስለዚህ እያንዳንዱ በዚህ ችሎት ላይ የታደመና እዚህ ቤት ውስጥ ያለ አስር (10) አስር ዶላር$ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

ማንም ሰው ሳይከፍል መውጣት አይችልም በማለት
👉አስር ዶለር ከኪሱ አውጥቶ ወረቀት ላይ መመዝገብ ጀመረ።
👉በተጨማሪ ዳቦ ቤቱ የተራበ ልጅ ለፖሊስ አሳልፎ በመስጠቱ 1000 ዶላር እንዲከፍል ውሳኔ አስተላለፈ።
👉ይህ በ24 ሰአት ውስጥ ካልተፈጸመ ፍርድ ቤቱ ዳቦ መደብሩን ያሳሽጋል።
👉ፖሊስም የተራበ ልጅ ፍርድ ቤት በማቅረቡ 1000 ዶላር እንዲቀጣለት ወሰነ።
👉የተወሰነለትን ገንዘብ ለልጁ ካስረከበ በኋላ ፍርድ ቤቱ ልጁን ህዝብ ፊት ይቅርታ ጠየቀው!
የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ በችሎቱ ላይ የነበሩ ታዳሚዎች ሁሉ በእንባ ተራጩ።
👉የልጁ እጅ ላይ የነበረው ሰንሰለት ተፈታለት። ዳኛው እንባ እየተናነቀው ሲያወራ ልጁ ያይ ነበር።
---------------------------------------
በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ያለው የፍትህ ስርዓት ግን ምን ይመስላል? የተራበ ልጅ ዳቦ ሰርቆ ቢያዝ ወንጀሉም እፍረቱም ለህዝቡ ነው ይህ መልዕክት ልብህን ከነካ እባክህን ለአንድ ሰው ዳቦ ግዛ።
👉አንተ እያለ ሌላው ጾም ማደር የለበትም።
👉በዙሪያህ ካሉ ከብዙዎች አንድ መካከል ቢያንስ ለ አንድ ሰው የአቅምህን አድርግ!

!

👉ከብዙዎች ትሻላለህና ካለህ ጥቂት ነገር ላጡት አካፍል!
ይህንን ከባድ ጊዜ ተጋግዘን እንለፈው
ይህንን በማረጋችሁ ፈጣሪ ያስብልናልና!

(Source: Facebook)

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምን አሉ ?የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦" ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ...
06/07/2023

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምን አሉ ?

የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦

" ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን ማሸፋፈን ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል።

ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ ፦
- የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ፣
- ነጋዴው ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ እና ነግዶ የሚኖርበት
- ገበሬው ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ አግኝቶ አርሶ የሚበላበት እንዲሁም ከተሜውን የሚቀልብበት ሁኔታ መፍጠር አልቻለም።

የኢትዮጵያ ህዝብ በችጋር እየተጠበሰ፣ በረሃብ እየተሰቃየ ነው።

የኑሮ ውድነቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ወገናችንን ከእጅ ወደ አፍ የነበረውን ኑሮ እንኳን መግፋት ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል።

ኢኮኖሚው ታሟል፣ መካከለኛ ነዋሪ የነበረውም ተመቶ ወደ ድህነት ወለል ወርዷል።

ስራ አጥነት ተስፋፍቷል፣ የሀገራችን የነገ ተስፋ የሆኑ ወጣቶችም ሀገራቸው ውስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ብቸኛ ምርጫ አድርገውታል።

ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ በሚሊዮን ብር ይጠየቅቸዋል፣ የመንግስት የፀጥታ መዋቅር በተለይም ፖሊስ ደግሞ አማራዎችንን እና የአማራ ልሂቃንን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን በማንሳታቸውና መንግሥትን በተለያየ ማንገድ በመተቸታቸው ብቻ የፈጠራ ወንጀል እየተሰጣቸው በማንነታቸው በጅምላ ይታሰራሉ ፣ በጅምላ ይከሰሳሉ ፍርድ ቤት ነፃ ሲላቸው ፖሊስ ግለሰቦችን አስሮ ያቆያል።

የኢትዮጵያ መልካፖለቲካ በሙሉ ያዳረሰ በሚባል ደረጃ ሀገራችን ሁሉም አካባቢዎች የደም ምድር ሆነዋል።

ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ተደርጓል፣ ከፊል ኦሮሚያ ክልል የጦርነት ቀጠና ሆኖ ባጅቷል፣ ትግራይ አማራ እና አፋር ፋይዳ ባልነበረው የብልፅግናና የህወሓት የስልጣን ጦርነት ምክንያት ደቋል። ቤኒሻንጉል ፣ጋምቤላ፣ አብዛኛው የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎችም ከሌሎች የተለየ አይደለም።

በማህበራዊ ዘርፍም ወንጀል ተበራክቷል፣ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች / ዜጎች በመንግስት ቤታቸው ፈርሶ ጎዳና ላይ ወድቀዋል ፤ እንደ ብልፅግና ሹማምንት አባባል ' ህጋዊ ድሃ ተደርገዋል ' ።

በሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በሰሜኑና በምዕራቡ ሀገራችን ክፍሎች በነበረው ጦርነት እና ማንነት ተኮር ጥቃቶች የውስጥ ተፈናቃይ ሆነው የሰቆቃ ኑሮን ይገፋሉ።

ባለፉት 5 ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን ተነጥቀዋል። ለዚህ ሁለንተናዊ ሀገራዊ ምስቅልቅል ቀውስ እና ውድመት ወይም ሀገራዊ መክሸፍ ዋነኛው ተጠያቂው የብልፅግና መራሹ መንግስት እና የእርሶ የወደቀ አመራር / failed leadership ነው።

ገዢው ፓርቲ ብልፅግናን አመጣለሁ እያለ ቢምል ቢገዘትም በተግባር ለኢትዮጵያ ህዝብ ያመጣለት ግን ጉስቅልና ሆኗል።

ብልፅግና ሀገርን ከቀውስ ማውጣት ካልቻለ እና ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የብልፅግና / የአገዛዙ አገልጋይ በመሆናቸው እና የችግሩም አካል በመሆናቸው ከፓርቲዎቹ የሚጠበው መፍትሄ አይኖርም።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለወደቀው የእርሶ እና የብልፅግና ፓርቲዎ አመራር መፍትሄው ምንድነው ? የሀገራዊ ቀውስ መፍትሄ አፈላላጊ ጉባኤ እንዲዘጋጅ አድርገው ስይረፍድ ለሀገራዊ ቀውሱ መላ ቢበጅ አይሻልም ወይ ? እንደእኔ እንደ አንድ የህዝብ ተወካይነቴ ብልፅግና ፓርቲ መራሹም ሆነ ፓርላማው ሀገራችን ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር ማውጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 60 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበትኑ እና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ መጠየቅ እፈልጋለሁ።

አመሰግናለሁ ! "

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
03/07/2023

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

Address

Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Mereja posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share