Gamo tv

Gamo tv ይህ የጋሞ ተለቪዥን ትክክለኛ የፈስቡክ ገጽ ነው።ገጹን
ላክ፣ሸርና ኮሜንት በማድረግ፣ወቅታዊና እውነተኛ መረጃዎችን በየዕሌቱ ይከታተሉ።

ክልሉ በበጀት ዓመቱ 13 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ጎበኙ ። አርባ ምንጭ ፡ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም (ጋሞ ቴቪ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘ...
24/07/2026

ክልሉ በበጀት ዓመቱ 13 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ጎበኙ ።

አርባ ምንጭ ፡ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም (ጋሞ ቴቪ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።


የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ ከሀገር ውስጥና ጎብኚ 978 ሚሊዮን ገቢ የተገኘ ሲሆን አፈፃፀሙን ከ100% በላይ ማሳደግ ተችሏል።


የማዜና የማጎ ብሔራዊ ፓርኮችን ህልውና ለማስጠበቅ በኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን እንዲሁም በዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን በተደረገ የ3 ሚሊዮን ብር በጀት ድጋፍ በጎፋና አሪ ዞኖች ለ330 የህግ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።

አክለውም በጥበቃ ረገድም 1 ሺህ 765 ነጥብ 36 ሺህ ሰዓት (82%) ሰዓት ተኮር ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን፤ ህገ-ወጥ ተግባራትን በ55% መቀነስ እና ከህገ-ወጥ ድርጊት ነፃ የሆነ የፓርኮች ሽፋን 60% በማድረስ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል ነው ያሉት።

በተጨማሪም 12 የሰፈራና እርሻ ሥራ ቅኝቶች የተካሄዱ ሲሆን፤ በዱር እንስሳትና መኖሪያቸው ላይ የሚደርሱ አደጋዎችንና ግጭቶችን የመከላከል ዝግጁነትን 40% ማሳደግ ተችሏል።

የዱር እንስሳት ጤና ክትትል 11 ዙር እና የመጨ አረም ቁጥጥር 4 ጊዜ ለማካሄድ ታቅዶ ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ማከናወን የተቻለ ሲሆን፤ በዚህም የጥበቃ ቦታዎች ሽፋኑን 47.5% እንዲሁም ያገገሙ የዱር እንስሳት መኖሪያዎች ሽፋኑ 40% ላይ ደርሰዋል።

በይመኙሻል ዮሴፍ

"ለእኔ ሳይሆን ለእኛ ለሰፈሬ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ካልን ይሄ ምክክር ፍሪያማ ይሆናል" ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ
15/07/2026

"ለእኔ ሳይሆን ለእኛ ለሰፈሬ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ካልን ይሄ ምክክር ፍሪያማ ይሆናል" ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ

ፈረንሳይ 0 - 1 ስፔን :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት************************በፈረንሳይ እና በስፔን መካከል በዳላስ እየተደረገ ያለው ተጠባቂ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው ...
14/07/2026

ፈረንሳይ 0 - 1 ስፔን :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
************************

በፈረንሳይ እና በስፔን መካከል በዳላስ እየተደረገ ያለው ተጠባቂ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ በስፔን 1 ለ 0 መሪነት ተጠናቅቋል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድንን መሪ ያደረገችውን ግብ ሚኬል ኦያርዛባል 22ኛው ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

የቲቢ በሽታን በመከላከል ስራው ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠየቀ።‎‎ቲቢን የመለየት፣ የማከም፣ የመከላከያ መድኃኒት የመስጠትና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስ...
13/07/2026

የቲቢ በሽታን በመከላከል ስራው ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠየቀ።

‎ቲቢን የመለየት፣ የማከም፣ የመከላከያ መድኃኒት የመስጠትና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ "የቲቢ ተግባራት ሳምንት" በሚል በጋሞ ዞን እና በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ተጀምሯል።

‎አርባምንጭ፤ ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)

'‎የቲቢ ተግባራት ሳምንት' ስራ ማስጀመሪያ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን ስራውን "ዩ ኤስ ጂ እሊሚኔት ቲቢ"የተሰኘ ፕሮጄክት (USG Eliminate TB project) ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ፣ ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ እና ከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል።

‎በመድረኩ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የአጋር ድርጅቶች ተወካዮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

‎የቲቢ በሽታ ቀድሞ መከላከልና ማከም ካልተቻለ እስከ ሞት የሚያደርስ የጤና ጉዳትን የሚያስከትል በአይን በማይታዩና 'ማይኮባክቴሪየም ቲቢ' በሚባሉ ረቂቅ ተህዋሲያን አማካይነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው።

‎በመድረኩ ማህበረሰቡ ከቲቢ በሽታ ራሱን ለመጠበቅ የጤና ባለሙያዎችን ምክረ ሀሳብ ሊቀበል፤ ህክምና ላይ ያሉም ህክምናውን በአግባቡ እንዲያጠናቅቁ መርዳት እንደሚገባ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

‎በመድረኩ ማስጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የቲቢ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ታዴዎስ ጤና፣ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ዋናቃ፣ የአርባምንጭ ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር አንተነህ ካሳዬ፣ የ"ዩ ኤስ ጂ እሊሚኔት ቲቢ" ፕሮጄክት የሀዋሳ ማስተባበሪያ ቢሮ ማናጀር አቶ ተፈራ ግርማ ቲቢን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የጤና ባለሙያው ተቀናጅቶ ለውጤት እንዲተጋ አሳስበው ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

‎ለተግባሩ ስኬታማነት ፕሮጄክቱን በገንዘብ ለደገፈው የአሜሪካ መንግስትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎ለመድረኩ ተሳታፊዎች የተግባር መነሻ ሰነድ እየቀረበና የሥራ መመሪያ እየተሰጠ ይገኛል።

1.Gaammo zoonen Borodda woradan diza bayra atte meqqeththay aappun laytha taybissidee?‎2. Woyshappe ooththettiza puutto ...
13/07/2026

1.Gaammo zoonen Borodda woradan diza bayra atte meqqeththay aappun laytha taybissidee?

2. Woyshappe ooththettiza puutto suqqanaas go'ettiza miishshay ay geettettizee?

የክልሉ አደጋ ስጋት ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠበርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ሰብሳቢነት የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት በወቅታ...
10/07/2026

የክልሉ አደጋ ስጋት ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ሰብሳቢነት የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ምክር ቤቱ ወቅታዊ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ አኳያ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር በተሰሩ ስራዎች እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት ለአደጋ በተጋለጡ አካባቢዎች የተከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል።

ምክር ቤቱ በመጀመሪያ አጀንዳው ወቅታዊ የቅደመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን በተመለከተ በተለይ በክልሉ ከበልግ ወቅት ጋር ተያያዥ በሆኑ የምርታማነት እና ተያያዥ የህብረተሰብ ጤና ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፤ በክልሉ 50 በመቶ የምግብ ዋስትና የሚወሰነው በበልግ ወቅት ምርታማነት መሆኑን ገልፀው፤ በዘንድሮ ዓመት የበልግ ዝናብ ቀድሞ መጥቶ ያለጊዜው ከመውጣቱ ጋር ተያይዞ የደረሱ ዓመታዊ ሰብሎች በተለይም የበቆሎ ሰብል ላይ በተወሰነ ደረጃ ጉዳት ማጋጠሙን ተናግረዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ በአለም ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተለይ በበልግ ወቅት በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ካገጠመ የዝናብ ዕጥረት ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የምፍትሄ ስራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በዚህ ረገድ ከአጭር ጊዜ አኳያ አርሶ አደሩ ለምርት በመድረስ ላይ እያሉ የዝናብ ዕጥረት የገጠማቸውን ሰብሎች ከማሳ በማንሳት ለከብቶች መኖ ማዋል እንደሚገባ ጠቁመው፤ በመኽር አዝመራ በአጭር ጊዜ ሊደርሱ ለሚችሉ ሰብሎች ትኩረት ሰጥቶ መስራትን ጨምሮ ተያያዥ አፋጣኝ መፍትሄዎች መወሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል በተከታታይ የተመዘገቡ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስኬት የሚያጠናክሩ ተግባራትን በማጠናከርና ከተረጂነት ዕሳቤ የተላቀቀ ስነልቦና በመገንባት እንዲሁም በተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በአግባቡ መምራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በተያያዘ በበልግ ካጋጠመ የአየር ፀባይ ለውጥ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አካባቢዎች የወባ ወረርሽኝ ምልክቶች እየታዩ መሆኑንም ጠቅሰው፤ ምልክቱ በታየባቸው አካባቢዎች በሽታው እናቶችና ህፃናትን ጨምሮ ህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል ሰራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባም በአጽንኦት ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳው የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ ከተረጂነት ለመላቀቅና የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን በአደጋ ስጋት ምክር ቤት እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ ተወያይቷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገውን ሽግግር በማጠናከር ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተያዘውን ግብ ከማሳካት ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተቀመጡ ስትራቴጂዎችን እና የማስፈጸሚያ ስልቶች በሙሉ አቅም ገቢራዊ በማድረግ ማሳካት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ለዚሁ ስኬት የተቀመጡ አምስት ስልቶችን፡- መግባባት፣ ማጥራት፣ ማዘጋጀት፣ ማቀናጀት እና ማሰራጨት በቁርጠኝነት በመተግበር በቅርቡ እንደ ሀገር ለሚታወጀው የምግብ ሉዓላዊነት ግብ ስኬት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገውን ሽግግር ለማጠናከር የምርታማነት መጠንን ማሳደግ፣ የመጠባበቂያ እህል ክምችት ተግባራትን ማጎልበት እና የምርት ማከማቻ መጋዘኖች ግንባታን የማጠናከር ስራዎችን በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻ አጀንዳው በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት በደረሱ አደጋዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ተግባር የቤቶች ግንባታ ሥራዎች የሚገኙበት ደረጃን፣ እንዲሁም የኦቶና ሆስፒታል መልሶ ግንባታ እና የዳሰነች መልሶ ማቋቋም የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ በዘላቂነት ለማቋቋም እየተከናወነ የሚገኘው ስራ አበረታች መሆኑን ተናግረው፤ ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም ኑሮ በጀመሩባቸው አካባቢዎች የማህበራዊ መስጫ ተቋማት ተደራሽነት እና የስራ ዕድል ፈጣራ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከኦቶና (የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል) ጋር በተያያዘም የክልሉ መንግስት ለሆስፒታሉ መልሶ ግንባታ ቀጥተኛ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ሀብት በማሰባሰብና በመልሶ ግንባታ ተግባራት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ የክልሉ መንግስት ለሆስፒታሉ ግንባታ የወሰነውን የ100 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ጨምሮ ዝግ የባንክ ሂሳብ በመክፈት ሀብት በማሰባሰቡ ስራ ከግለሰቦች መሰብሰብ የተቻለውን ገንዘብ በቀጥታ ዩንቨርሲቲው ወደ ከፈተው አካውንት ማስተላለፉን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ ሆስፒታሉን የሚያስተዳድረው የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲት የሆስፒታሉን መልሶ ግንባታ ለማከናወን ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡ ለሆስፒታሉ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት በቀጣይም የሆስፒታሉ መልሶ ግንባታ ከዳር እስክደርስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

 !አርባ ምንጭ፦ ሰኔ 28/10/2018 ዓ.ም(ጋሞ ቴሌቪዥን)ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ዲያቆን ፍቅሩ አያልቅበት ይባላል። ‎ ዕድሜው 19 ሲሆን  በሼቻ ክፍለ ከተማ ገሮ ትምህርት አካባቢ ከ...
09/07/2026

!

አርባ ምንጭ፦ ሰኔ 28/10/2018 ዓ.ም(ጋሞ ቴሌቪዥን)

ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ዲያቆን ፍቅሩ አያልቅበት ይባላል።
‎ ዕድሜው 19 ሲሆን በሼቻ ክፍለ ከተማ ገሮ ትምህርት አካባቢ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖርበት ቤት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም።

የደረሰበትን ለማወቅ ቤተሰብ፣ ዘመድና ጎረቤት ከጠፋበት ሰዓት ጀምሮ በከፍተኛ ጭንቀትና በትጋት ቢፈልገውም ሊገኝ አልቻለም።

ስለሆነም ይህንን ዲያቆን ያየ፣ የት እንዳለ የሚያውቅ ወይም መረጃው ያለው ልበ-ቅንና ደግ የአርባ ምንጭ ሕዝብ በሰብአዊነት እንድትረዱንና ከታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በመደወል እንድታሳውቁን በፈጣሪ ስም እንማጸናለን።



ሸሚዝ፦ ውኃ ሰማያዊ መሳይ (ነጭ መስመር ያለበት ስኳር ሸሚዝ)

ሱሪ፦ ጥቁር ቱታ ሱሪ
ልታገኙን የምትችሉባቸው ስልክ ቁጥሮች፦

📞 0912440735
📞 0916873431
📞 0988716061
📞 0930730171
📞 0910321824

ማሳሰቢያ፦ ይህንን መረጃ ሼር (Share) በማድረግ ለብዙኃን እንዲደርስና ወንድማችን በፍጥነት ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዶርዜ ሎጅ የቱሪዝም መዳረሻ ያደረጉት ጉብኝት በምስል፡-
03/07/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዶርዜ ሎጅ የቱሪዝም መዳረሻ ያደረጉት ጉብኝት በምስል፡-

አስደማሚው የአርባምንጭ ፕሮጀክት - የMICE ቱሪዝም እና የተፈጥሮ ውበት መገናኛ አዲሱ የኢኮኖሚ ማዕከል
01/07/2026

አስደማሚው የአርባምንጭ ፕሮጀክት - የMICE ቱሪዝም እና የተፈጥሮ ውበት መገናኛ አዲሱ የኢኮኖሚ ማዕከል

1. Gayrosinne  Gerersas diza dummateththa paattidi Gaammothora  xaafite.‎2. ‎Halaythan kumeththa Tophphiyan puute tokket...
30/06/2026

1. Gayrosinne Gerersas diza dummateththa paattidi Gaammothora xaafite.

2. ‎Halaythan kumeththa Tophphiyan puute tokketanaas halchettida puuteta tayboy aappunee? Inte zaaro xaafite.

Address

Gamo
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share