Dr Union Dream-DUD

Dr Union Dream-DUD 💓ይህ ማሕበራዊ ሚዲያ የጤና ባለሙያዎችን መብት ይጠይቃል፣ለጤና ባለሙያዎች ድምጽ ይሆና ጤናና ጤና ነክ መረጃዎችን ያሰራጫል💓-DUD-💓 follow&like💓

 👉ይህን ስር ነቀል ዘመቻን ስናካሂድ በሀገርቱ ኢኮኖሚ፣ማሕበራዊ፣ሀይማኖት፣ሠላምና፣ፖለቲካ ላይ ምንም አይት ተጽዕኖ የማናደርስ መሆኑን እያሳሰብን ግን ከላይ የተዘረዘሩትን፣የምያደፈርሱትንና፣የ...
19/10/2025



👉ይህን ስር ነቀል ዘመቻን ስናካሂድ በሀገርቱ ኢኮኖሚ፣ማሕበራዊ፣ሀይማኖት፣ሠላምና፣ፖለቲካ ላይ ምንም አይት ተጽዕኖ የማናደርስ መሆኑን እያሳሰብን ግን ከላይ የተዘረዘሩትን፣የምያደፈርሱትንና፣የሳቱትን የምይዝ፣አደገኛ፣ወጥመድ እና መንጠቆ፣ስለተዘጋጀ በያላችሁበት ስፍራ ክፋትን፣በመቃወም፣መልካሙን በመስራት፣ለሀገራችን እድገት፣ብርቱ ትግል፣በማድረግ ከዝህ ወጥመድ እና ማንጠቆ፣ራሳችሁን እንድትጠብቁ በቀድምያ መልዕክታችንን ልናስተላልፍ እንወዳለን።





🚫 ወላጆች፣ ይህን ማድረግ አቁሙ! 🙏👉ይህ መረጃ ጉዳት የሌለው በሚመስል ነገር ላይ ትኩረት ያደርጋል — ሕፃናትን በእጃቸው ወይም በእጅ አንጓቸው አንስቶ መያዝ — ነገር ግን ይህ “የሞግዚት ...
16/10/2025

🚫 ወላጆች፣ ይህን ማድረግ አቁሙ! 🙏

👉ይህ መረጃ ጉዳት የሌለው በሚመስል ነገር ላይ ትኩረት ያደርጋል — ሕፃናትን በእጃቸው ወይም በእጅ አንጓቸው አንስቶ መያዝ — ነገር ግን ይህ “የሞግዚት ክርን” (Nursemaid’s Elbow) ወይም የራዲያል ጭንቅላት መንሸራተት (radial head subluxation) የሚባል ከባድ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። 😢

👉ልጅን በክንዳቸው ጎትቶ ወይም አሽከርክሮ ሲያነሱ፣ በክርናቸው ውስጥ ያሉት ለስላሳ ጅማቶች ከቦታቸው ሊንሸራተቱ ይችላሉ — ይህም ድንገተኛ ህመም፣ ማልቀስ፣ እና ህፃኑ እጁን ማንቀሳቀስ አለመፈለግ ያስከትላል። ይህ ችግር እርስዎ ከሚያስቡት በላይ በተለይም ከ1–4 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ታዳጊዎች ዘንድ የተለመደ ነው።
💡 ደህንነቱ የተጠበቀ ምክር:
* ✅ ልጅዎን በሚያነሱበት ጊዜ ሁል ጊዜ ከክንዳቸው ስር ወይም በሰውነታቸው ዙሪያ በመያዝ ያንሱ — በፍጹም በእጃቸው ወይም በእጅ አንጓቸው አይያዙ።
* ✅ ልጅዎ ከተጎተተ ወይም ከተነሳ በኋላ ድንገት እጁን መጠቀም ካቆመ፣ ወዲያውኑ ሐኪም ያማክሩ — ብዙውን ጊዜ በሕፃናት ሐኪም በቀላሉ ሊስተካከል ይችላል።
ወላጅነት በብዙ ፍቅር እና ትምህርት የተሞላ ነው ❤️

— ያስታውሱ፣ ትንሽ ጥንቃቄ ብዙ ሥቃይን መከላከል ይችላል!

14/10/2025



የሳንባ ምች(pneumonia) በሳንባ ላይ እብጠትን የሚያመጣ በሽታ ነው።በተለምዶ ስንተነፍስ አየር ከመተንፈሻ ቱቦ (trachea) → (bronchi) → (bronchioles) → በመጨረሻም አልቪዮላይ(Alveoli) ወደሚባሉት ጥቃቅን የአየር ከረጢቶች ይደርሳል።
እነዚህ ጥቃቅን የአየር ከረጢቶች
✅ ኦክስጅንን ወደ ደም መላክ
✅ ካርቦን ዳይኦክሳይድን ከሰውነት ማስወገድ ዋነኛ ስራቸው ነው።
ስለዚህም የሳንባ ምች ሲከሰት ስራቸውን በማስተጓጎል እነዚህን የአየር ከረጢቶች በፈሳሽ እንዲሞሉ ይሆናል።

ይህ በሽታ በየዓመቱ ወደ 450 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን፣ ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለሞት ይዳረጋል። በተለይም አረጋውያን፣ህጻናትና የበሽታ የመከላከል አቅማቸው በተዳከሙ ሰዎች ላይ በሽታው የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው።

የሳንባ ምች በተለያዩ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ሊከሰት ይችላል፦
1.ባክቴሪያ (ለምሳሌ፡ Streptococcus pneumoniae) - ብዙውን ጊዜ ይበልጥ ከባድ ሲሆን፣ ከጉንፋን ወይም ከፍሉ በኋላ ሊከሰት ይችላል።
2.ቫይረሶች (ለምሳሌ፡ የፍሉ ቫይረሶች) - በአብዛኛው የከፋ ባይሆንም፣ በትንሽ ሕፃናት እና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ግን በብዛት ይከሰታል።
3.ፈንገስ - የበሽታ የመከላከል አቅማቸው በተዳከመ ወይም ሥር የሰደደ የጤና ችግር ባለባቸው ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ ይታያል።

ከምልክቶቹ መካከል
✅የማያቋርጥ ሳል (አክታ ሊኖረው ይችላል)
✅በሚተነፍሱበት ወይም በሚያስሉበት ጊዜ የደረት ህመም
✅ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት
✅የድካም ስሜት
✅የትንፋሽ ማጠር
✅ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ ወይም ተቅማጥ
✅በአረጋውያን ላይ ከወትሮው የተለየ ዝቅተኛ የሰውነት ሙቀት መኖር ያካትታል።

💊 ህክምና
ህክምናው በበሽታው መንስኤ፣ በእድሜ እና በአጠቃላይ የጤና ሁኔታ የሚለያይ ሲሆን
አንቲባዮቲክስ (ለባክቴሪያ የሳንባ ምች)
አንቲቫይራል (ለቫይረስ የሳንባ ምች)
አንቲፈንጋል (ለፈንገስ የሳንባ ምች) ያካትታል።

የሳንባ ምች ቀድሞ ከተደረሰበት መከላከልም ሆነ ማከም የሚቻል በሽታ ነው፣ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከታየባችሁ ባቅራቢያችሁ ወደሚገኝ ህክምና ጣቢያ ይሂዱ።

#ዶ/ር_ዩኒየን_ድሪም

የአቮካዶ የጤና ጠቀሜታዎችአቮካዶ ባለው ከፍተኛ የሆነ የቫይታሚንና የሚነራል ይዘት፣ በውስጡ የያዘው ፋይበርና እጅግ አነስተኛ የስብ መጠን የዓለማችን ተመራጭ የፍራፍሬ ዓይነት እንዲሆን አድርጎ...
14/10/2025

የአቮካዶ የጤና ጠቀሜታዎች

አቮካዶ ባለው ከፍተኛ የሆነ የቫይታሚንና የሚነራል ይዘት፣ በውስጡ የያዘው ፋይበርና እጅግ አነስተኛ የስብ መጠን የዓለማችን ተመራጭ የፍራፍሬ ዓይነት እንዲሆን አድርጎታል

✧ አቮካዶ በሰውነታችን የሚገኝን የኮሌስትቶል መጠን ዝቅ በማድረግ ረገድ አቻ የለውም

አቮካዶ በውስጡ የያዘው ከፍተኛ የፋቲ አሲድ መጠን በሰውነታቸን ያለውን የኮሌስትቶል መጠን ዝቅ እንዲል ያስችላል።
በአንፃሩ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆነው የኮሌስትሮል መጠን ከፍ እንዲል ያደርጋል

✧ አቮካዶ በውስጡ የያዘው ቫይታሚን ኢ ለልብ ህመም ወይም ስትሮክ የመጋለጥ ዕድላችንንም በእጅጉ ይቀንሳል

✧ እርጅናን ለመከላከል እና የቆዳ ውበት ተጠብቆ እንዲቆይ ይረዳል

በአቮካዶ ውስጥ በብዙ መጠን የሚገኘው አንቲ ኦክሲዳንት ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና የሞቱ የቆዳ ሴሎች እራሳቸውን እንዲተኩ ሲያግዝ፥ ካሮቲኖይድስ የተባለው ንጥረ ነገርም በቆዳ ላይ የሚታዩና የቆዳን ውበት የሚቀንሱ ምልክቶች እንዳይከሰቱ ያደርጋል

አቮካዶን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች ከማያዘወትሩት የተሻለ ለስላሳ ቆዳ እና ፀጉር፣የሰውነት ጠረን፣ የአዕምሮ ዕድገት እንደሚጎናፀፉም ጥናቶች ያመላክታሉ

✧ ክብደት ለመቀነስ ፍቱን ነው፣

አቮካዶ ሙቀት ሰጪ ምግብ ከምንላቸው የምግብ አይነቶች እንደመመደቡ፥ በየማዕዳችን በቂ የጊዜ ልዩነት እንድናደርግ ዕድል ይሰጠናል ፤ በዚህም ቶሎ ቶሎ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማን በማድረግ የምግብ ፍጆታንና ክብደታችንን እንድንቀንስ ያስችላል

✧ ለስኳር ህመምተኞች ተመራጭ ነው

በአቮካዶ ውስጥ በጥሩ መጠን የሚገኘው ፖታሺየም በደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን በማመጣጠን በሰውነት ውስጥ የልብ ስራንና የስኳር መጠንን የተረጋጋ እንዲሆን ያስችላል

✧ ለፅንስ ጤንነት ወሳኝ ነው

አቮካዶ ጥሩ የቫይታሚን ኤ ፣ ቢ ኮምፕሌክስ፣ ሲ፣ ኢ፣ ኤች፣ ኬ እና ፎሊክ አሲድ መገኛ ነው።
በተጨማሪም በውስጡ የሚገኙት እንደ ማግኒዢየም፣ ኮፐር፣ አይረን ፣ ካልሲየም እና ፖታሲየም የመሳሰሉትን ንጥረ ነገሮች ለፅንሱ ዕድገት እጅግ ወሳኝ ናቸው

14/10/2025



👉ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ወቅት በጣም ጠቃሚ ነው ምክንያቱም በተለይ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት — ሴትየዋ እርግዝናዋን ሳታውቅ እንኳ — የሕፃኑ አንጎልና የአከርካሪ ገመድ (spinal cord) እንዲዳብር ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
📌 1. የኒውራል ቲዩብ ጉድለቶችን (NTDs) ይከላከላል
* ኒውራል ቲዩብ የሕፃኑን አንጎልና አከርካሪ ገመድ የሚያቋቁም የመጀመሪያው መዋቅር ነው።
* ፎሊክ አሲድ ከተፀነሰ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ 28 ቀናት ውስጥ ይህ ቲዩብ በአግባቡ እንዲዘጋ ይረዳል።
* እጥረት ከተከሰተ ከባድ የልደት ጉድለቶችን ሊያስከትል ይችላል፣ ለምሳሌ፦
* ስፒና ቢፊዳ (Spina bifida) – የአከርካሪ ገመድ በትክክል አለመዘጋት
* አኔንሰፋሊ (Anencephaly) – የአንጎል እና የራስ ቅል ክፍሎች በትክክል አለመፈጠር
🩸 2. ፈጣን የሕዋስ እድገትን ይደግፋል
* በእርግዝና ወቅት የእናትና የሕፃኑ ሕዋሳት በፍጥነት ይከፋፈላሉ።
* ፎሊክ አሲድ ዲኤንኤን (DNA) እና አዳዲስ ሴሎችን ለመሥራት ይረዳል፣ ይህም የሚከተሉትን ይደግፋል፦
* የእንግዴ እምብርት (placenta) መፈጠር
* የፅንስ ሕብረ ሕዋሳት እድገት
* የእናት ደም መጠን መጨመር
📌 3. የእናት የደም ማነስን ይከላከላል
* ፎሊክ አሲድ ቀይ የደም ሴሎችን ለማምረት ይረዳል፣ ይህም ሜጋሎብላስቲክ የደም ማነስ (Megaloblastic anemia) የመከሰት አደጋን ይቀንሳል፤ ይህ ደግሞ፦
* ድካም (Fatigue)
* የሰውነት መዛል (Weakness)
* ለሕፃኑ በቂ ኦክሲጅን አለማድረስ ሊያስከትል ይችላል።
🧠 4. የሌሎች የልደት ጉድለቶችን አደጋ ሊቀንስ ይችላል
* በቂ የፎሊክ አሲድ መጠን መኖር የሚከተሉትን አደጋዎች ከመቀነስ ጋር ተያይዟል፦
* የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ (Cleft lip and palate)
* የልብ የልደት ጉድለቶች (Congenital heart defects)
* ዝቅተኛ የወሊድ ክብደት (Low birth weight)
Dr_Union Dream

እንግዴልጅ ቀድሞ መምጣት(Placenta Previa) ➡️እንግዴልጅ(placenta): ጽንሱ ለመኖር እና ለማደግ የሚያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች ከእናት ወደ ጽንስ የሚያልፉበት ነዉ። በትክክለኛዉ አ...
07/10/2025

እንግዴልጅ ቀድሞ መምጣት(Placenta Previa)

➡️እንግዴልጅ(placenta): ጽንሱ ለመኖር እና ለማደግ የሚያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች ከእናት ወደ ጽንስ የሚያልፉበት ነዉ። በትክክለኛዉ አፈጣጠር እንግዴልጅ በላይኛዉ ማህጸን ክፍል ዉስጠኛዉ ሽፋን ላይ መተከል አለበት። ይህንን ስቶ ማህጸን በር ተጠግቶ ወይም ሙሉ በመሸፈን የሚተከል እንግዴልጅ ቀድሞ የመጣ(placenta previa) እንለዋለን።

➡️ለህክምና ዉሳኔ እንዲያመች ለሁለት ይከፈላል።
👉1.ማህጸን ሙሉ የሸፈነ(placenta previa)
👉2.ማህጸን በር የተጠጋ(lowlying placenta)

➡️ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች
👉 በኦፕሬሽን መውለድ (prevous c/s scar)
👉የበፊት ተመሳሳይ ታሪክ(prevous history)
👉መንቲያ እና ከዛ በላይ ጽንስ የያዘ እርግዝና
👉 ብዙ መውለድ (multiparity)
👉የእናት እድሜ ከ35 በላይ መሆን
👉ስጋራ ማጬስ

➡️ልታዩ የምችሉ ምልክቶች
👉 በእርግዝና ወቅት የህመም ስሜት ሳይኖር የሚከሰት የደም መፍሰስ ነዉ። የደም መጠን ትንሽ ወይም ብዙ ልሆንም ይችላል።

💊አልትራሳዉንድ(ሶኖግራፍ) የተባለ የህክምና ምርመራ መሳሪያ ምስጋና ይግባዉና ምንም ምልክት ሳያሳይ እንዲሁም እናት ላይ ጉዳት ሳይደርስ የእንግዴልጅ ቀድሞ መምጣት ችግር ቀድሞ ማወቅ ይቻላል። ቀድሞ ማወቅ➡️ቀድሞ መዘጋጀት➡️ጉዳት ሳይደርስ ማከም! ስለዚህ የእርግዝና ክትትል ሲያደርጉ የአልትራዉንድ(ሶኖግራፍ)ምርመራ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ።

➡️የሚሰጥ ህክምና
👉እንግዴልጅ ቀድሞ መምጣት የተከሰተባት እናት ሁኔታዉ ቀድሞ ከታወቀ በተለይም ከ28 ሳምንት በኃላ ሆስፒታል ዉስጥ ሆና እንግዴልጅ ቦታ፣ የጽንስ እድገት፣ እና ጠቅላላ ሁኔታዋ ቅርብ ክትትል ይደረግላታል።
👉እየደማች ከሆነ፣ ምጥ ከጀመራት እና ሌሎች ነገሮች ካሉ በድንገተኛ ኦፕሬሽን እንዲትወልድ ይደረጋል።
👉 ሌላ ችግር ከለሌ 37ሳምንት ሲሞላት በኦፕሬሽን እንዲትወልድ ይደረጋል።

➡️የእንግዴልጅ ቀድሞ መምጣት ተያይዞ ልከሰቱ የምችሉ ችግሮች
🤰እናት ጤና ላይ
👉1. ብዙ ደም መፍሰስ እና መዘዞቹ
👉2.በኦፕሬሽን መዉለድና እና ተያያዥ ነገሮች
👉3.እንግዴልጅ ከማህጸን ጡንቻ ጋር መጣበቅ እንዲሁም አልፎ ከሌሎች ብልቶች ጋር መጣበቅ(placenta accreta spectrum)
👉4.ቀጣይ እርግዝና ላይ ደጋሜ የመከሰት እድል መጨመር
👉ሌላም
🤱ጸሰንስ ጤና ላይ
👉ያለጊዜ መወለድ እና ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች

➡️ከእናት ምን ይጠበቃል
👉የእርግዝና ክትትል በጊዜ መጀመር
👉በእርግዝና ወቅት የአልትራሳዉንድ(ሶኖግራፍ)ምርመራ ማድረግ
👉የእንግዴልጅ ቀድሞ መምጣት እንዳለ ከታወቀ ጾታዊ ግንኙነት አለማድረግ
👉የደም ምልክት ማሳየት ካለ በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም መሄድ
👉ለሚሰጠዉ የህክምና ዉሳኔ ከሐኪም ጋር መመካከር

➡️የሚታየንን እሾህ እያነሳን ጉዟችን እንቀጥል

DUD

‎የኢትዮጵያ (ለጤና ባለሙያው የሚከፈለው ደመወዝ በዶላር )‎_ዶክተሮች 12765 /132 =96.7 ዶላር 😭‎-ነርሶች 7600/132=-57.5 ዶላር‎‎ የ2025 ዓ.ም. ለተለያዩ የአፍሪቃ ሀገ...
07/10/2025

‎የኢትዮጵያ (ለጤና ባለሙያው የሚከፈለው ደመወዝ በዶላር )
‎_ዶክተሮች 12765 /132 =96.7 ዶላር 😭
‎-ነርሶች 7600/132=-57.5 ዶላር
‎
‎ የ2025 ዓ.ም. ለተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት የጤና ሠራተኞች የደሞዝ መጠን (በዶላር/ወር) መረጃ ከኢኮኖሚያዊ እቅዶች፣ የጤና ልማት ፕሮግራሞች ጋር በሀገር ውስጥ ያሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ይዘት አንጻር
‎
‎በምሥራቅ አፍርካ
‎ኬንያ፤
‎ - ዶክተሮች: 1,000–3,000 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 2,500–5,000 ዶላር (ግል).
‎ - ነርሶች: 500–1,200 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 800–2,000 ዶላር (ግል).
‎ - የህክምና ባለሙያዎች: 600–1,500 ዶላር.
‎
‎ሩዋንዳ
‎ - ዶክተሮች: 1,200–2,500 ዶላር.
‎ - ነርሶች: 400–1,000 ዶላር.
‎**ምዕራብ አፍሪቃ**
‎- **ናይጄሪያ**
‎ - ዶክተሮች: 800–2,000 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 2,000–6,000 ዶላር (ግል).
‎ - ነርሶች: 300–800 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 500–1,500 ዶላር (ግል).
‎
‎- ጋና
‎ - ዶክተሮች: 1,000–2,500 ዶላር.
‎ - ነርሶች: 400–1,000 ዶላር.
‎
‎ መካከለኛ አፍሪቃ
‎- የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (DRC)
‎ - ዶክተሮች: 600–1,800 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 1,500–3,000 ዶላር (NGO/ግል).
‎ - ነርሶች: 300–700 ዶላር.
‎
‎ካሜሩን
‎ - ዶክተሮች: 700–1,500 ዶላር.
‎ - ነርሶች: 250–600 ዶላር.
‎ደቡብ አፍሪቃ
‎- **ደቡብ አፍሪቃ**
‎ - ዶክተሮች: 3,000–8,000 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 5,000–15,000 ዶላር (ግል).
‎ - ነርሶች: 1,000–2,500 ዶላር.
‎ ዝምቧብዌ
‎ - ዶክተሮች: 500–1,200 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 1,000–3,000 ዶላር (ግል).
‎ - ነርሶች: 200–600 ዶላር.
‎ሰሜን አፍሪቃ
‎ግብጽ
‎ - ዶክተሮች: 400–1,000 ዶላር (መንግስታዊ)፤ 1,500–4,000 ዶላር (ግል/በገርቢ ሀገራት ሥራ).
‎ - ነርሶች: 200–600 ዶላር.
‎ሞሮኮ
‎ - ዶክተሮች: 1,000–2,500 ዶላር.
‎ - ነርሶች: 300–800 ዶላር.
‎
‎Source : Global health organization
Nb 1$=132 ብር በነበረበት የተሰላ ነው
‎
‎
‎

  ➥ጡት የተገነባው/የተሰራው ከብዙ መዋቅሮች እንደ ስብ፣ከወተት ማመንጫ ፣ከዕጢዎች እና አያያዝ ህብረ ህዋሶች ነው ፡፡በእዚህ መዋቅሮች ላይ የሚከሰቱ ችግሮች የጡት እብጠት ያስከታላሉ ፡፡ #...
07/10/2025



➥ጡት የተገነባው/የተሰራው ከብዙ መዋቅሮች እንደ ስብ፣ከወተት ማመንጫ ፣ከዕጢዎች እና አያያዝ ህብረ ህዋሶች ነው ፡፡በእዚህ መዋቅሮች ላይ የሚከሰቱ ችግሮች የጡት እብጠት ያስከታላሉ ፡፡

#ምልክቶቹ

➥የጡት መጠን መጨመር ጡት ሲነካ ህመም፣ ጡት ላይ ያሉ የደም ስሮች ከወትረው በተለየ መልኩ መታየት፣ የጡት መክበድ፣ ብብት አካባቢ ህመም፣ የጡት ቆዳ ቀለም መቀየር፣ ህመም ስሜት መኖር
መቅላት፣ ማሳከክ እንዲሁም መቁሰል ወዘተ ናቸው፡፡



➥የጡት እብጠት ሲሰማን መጥፎውን መጀመርያ ማሰብ የተለመደ ነው የጡት ካንሰር አንዱ ምልክት ጡት ላይ የሚፈጠር እብጠት ነው። ነገር ግን የጡት እብጠት ብዙ መንስኤዎች አሉት፡፡



➥ብዙ የሰውነት ሎሽኖች ለስላሳ እና ወዛማ ቆዳ እንደሚሰጡ ይነገራል፤ ነገር ግን አንዳንዴ አለርጂ ሊፈጥሩ ይችላሉ ጡት ቆዳ ላይ ከተቀባናቸው የጡት እብጠት ፣ ህመም እና የጡት መሳሳት ያስከትላሉ፡፡

# እርግዝና

➥የጡት ማበጥ ፣ መሳሳት እና መቁሰል የእርግዝና ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ እርግዝና እንደተፈጠረ የሚፈጠሩ የሆርሞን ለውጦች ጡት ሰውነት ከሚያድግበት ፍጥነት በላይ እንዲያድግ ያደርጋሉ የኤስትሮጅን መጠን ሲጨምር በጡት ውስጥ የሚገኙ የጡት ቧንቧዎች ስፋት ይጨምራል ይህ ሲሆን የጡት ህመም እና መሳሳት ሊከሰት ይችላል፡፡



➥የጡት ማስያዣ መጥበብ እና አለመመቸት ከጡት ህመም መንስኤዎች ውስጥ ይካተታል ከ12 ሰአት በላይ ምቾት የማይሰጥ ጡት መያዣ ለብሶ ከመዋል የተሻለ አማራጭ መፈለግ ይሻላል፡፡



➥ከባድ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ መስራት
አካል ብቃት እንቅስቃሴ ብዙ በሽታዎችን የሚከላከሉበት የአኗኗር ስልት ነው አንዳንድ ግዜ ግን ከአቅም በላይ እንቅስቃሴ ማድረግ የጡት ህመም ሊያስከትል ይችላል ደረት ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ለዚህ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

#ኢንፌክሽን

➥የተዘጋ የወተት ቱቦ ፣ ወደ ውስጥ የሚያድግ የጡት ጸጉር ፣ የተደፈነ የላብ እጢ እና ባክቴሪያዎች ጡት ላይ ለሚፈጠር ኢንፌክሽን ቀዳሚ ተጠያቂዎች ናቸው ኢንፌክሽን ሲፈጠር ጡት ይቀላል ፣ ያብጣል ፣ የህመም ስሜት ይፈጥራል ፣ ጡት ደም ወይም ፈሳሽ እንዲያወጣም ምክንያት ሊሆን ይችላል ትኩሳት እና የድካም ስሜት አብሮ ሊፈጠር ይችላል፡፡



➥ሆርሞን የሚቀይር ማንኝውም መድሃኒት የጡት መቁሰል ሊያስከትል ይችላል ብዙ ግዜ ተጠያቂዎቹ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች ናቸው እነዚህ መድሃኒቶች የኤስትሮጅን ሆርሞን መጠንን ይጨምራሉ ይህ የመድሃኒት ተጽእኖ ከግዜ በኋላ እየጠፋ ሊሄድ ይችላል፡፡



➥ጉርምስና ፣ የወር አበባ እና ማረጥ የሰውነት የሆርሞን መጠን ይቀይራሉ በእነዚህ ግዜዎች የሚፈጠር የጡት ህመም የተለመደ ነው።

#ማጥባት

➥በእርግዝና ወቅት ጡት እና የወተት ቧንቧዎች እድገት ያሳያሉ ይህ እድገት ልጅ ከተወለደም በኋላ ይቀጥላል የጡት እድገት ህመም ሊያስከትል ይችላል።

# የጡት_ጉዳት

➥በኳስ መታመምም ሆነ በማንኛውም የሃይል ግጭት የጡት እብጠት ሊከሰት ይችላል ብዙ ግዜ በጉዳት ምክንያት የሚፈጠር እብጠት በራሱ ግዜ ይጠፋል፡፡



➥ካንሰር በሚኖርበት ወቅት ሙሉ የጡት እብጠት ሊታይ ይችላል በተጨማሪ የጡት ጫፍ አካባቢ ላይ ህመም ሊኖር ይችላል
ጡታችን ስለታመመ ብቻ የጡት ካንሰር አለ ማለት አይደለም ሌሎች የጡት ህመም ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብም ይኖርብናል፡፡

ለበለጠ መረጃ https://www.facebook.com/61557450698815/posts/122237248442248356/

አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ይፋ ሆነ።የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከመስከረም 2018 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን አዲሱን የመንግሥት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል ይፋ አድርጓ...
02/10/2025

አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ይፋ ሆነ።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከመስከረም 2018 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን አዲሱን የመንግሥት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል ይፋ አድርጓል።

Dr-Union Dream

 #የወንድ  #ልጅ  #ግርዛት መቼ ነው  #መገረዝ ያለበት እና ጠቀሜታው የወንድ ልጅ ግርዛት በሃይማኖታዊ ምከንያት የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ዘመን ለጤና ባለው ጠቀሜታ እየተከናወነ ይገኛል። ያ...
28/09/2025

#የወንድ #ልጅ #ግርዛት መቼ ነው #መገረዝ ያለበት እና ጠቀሜታው

የወንድ ልጅ ግርዛት በሃይማኖታዊ ምከንያት የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ዘመን ለጤና ባለው ጠቀሜታ እየተከናወነ ይገኛል።

ያለመገረዝ ከሚከተሉት የጤና ችግሮች ጋር ሊያያዝ ይችላል።
- ተደጋጋሚ የሆነ የሽንት መስመር ኢንፌክሽን
- የብልት መቆጣት
- የሸለፈት ጥበት/ የሸለፈት ወደሗላ የመመለስ ማስቸገርን ሊያስከትል ይችላል ።

በወጣትነት ወይም በአዋቂ እድሜ አለመገረዝ ደግሞ ለአባላዘር በሽታዎች ለኤች.አይ.ቪ የማጋለጥ እድል ሊጨምር ይችላል ፡ ብዙውን ጊዜ ባይሆንም ለብልት ካንሰርም ተጋላጭነትን ይጨምራል።

በማንኛውም እድሜ ግርዛትን ማከናወን ይቻላል ነገር ግን ከ1 አመት በታች በተለይም ከ3 ወር በታች ቢሆን ይመረጣል ምክንያቱም ለመስራት ቀላል ነው ፣ ቁስሉ በቀላሉ ይደርቃል ፣ ከሰርጀሪ ወይም ከማደንዘዣ ጋር የተያያዘ የጎንዮሽ ጉዳት አነስተኛ ነው ፡ በጨቅላነት እድሜ የተከናወነ ግርዛት የተሻለ እይታ (Cosmetic appearance) ያለው ብልት እንዲኖር ያደርጋል።

- አብዛኛው ለሀይማኖት ተብሎ የሚደረግ ግርዛት በ7ኛው ቀን ይከናወናል ይህም ከህክምና አንፃርም ይመከራል።

 # # # #የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት # # #********************************👉ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለ...
24/09/2025

# # # #የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት # # #
********************************
👉ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል ነጭ ሽንኩርት መብላት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

👉ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡

👉በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡

👉ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡

👉ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ መልሶ ይጠነክራል፡፡

👉ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡

👉ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡

👉በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት varicose የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡

👉ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማትን ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡

መስ 14/2018 ዓ.ም-ዶ/ር ዩኒየን ድሪም

 👉በጋሞ ዞን በቦንኬ ወረዳ ለጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣ከቆመ ሶስት ዓመት ከስድስት ወር ሆነዋል በነዛ፤ግዜያቶች ያለምንም፤መንጠባጠብ በሳምንት መጨረሻ፤ቀናት ቅዳሜና፣ዕሁድ ቀን ሆነ...
17/09/2025



👉በጋሞ ዞን በቦንኬ ወረዳ ለጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣ከቆመ ሶስት ዓመት ከስድስት ወር ሆነዋል በነዛ፤ግዜያቶች ያለምንም፤መንጠባጠብ በሳምንት መጨረሻ፤ቀናት ቅዳሜና፣ዕሁድ ቀን ሆነ ማታ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ፣የመንግሥትንና የሕዝብን አደራ ተሸክመዉ፣የሕክምና፤አገልግሎታቸዉን፣ለሕብረተሰባቸዉ በታማኝነትና፣በቅንነት እየሰጡ ቆይተዋል።

👉ሆኖም ያለ እረፍት 30 ቀኑንና፤ማታዉን ሕብረተሰቡን እያገለገለን ይከፈላል በምል ተስፋ እየሠራን ሳለን ተስፋ አስቆራጭ ተግባር ተፈጽሞብናል። ዉስጣችን ቆስሏል ይላሉ።

👉ስለዝህ በቅርቡ ስር-ነቀል የጤና ፖሊስ፣ ስርዓትና፣ለዉጥ ዘመቻ አካል ከሆነዉ አንዱ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በመሆኑ መንግሥትም ሆኔ ግለሰብ ላሰራዉ ጉልበት ካልከፈለ በአሰር ሰራተኞች አዋጅ ደንብ እና በፍታብሔር ስነ-ስርዓት ህግ ይጠየቃል።

👉ስለሆነም ለዉጡ የወረዳ መንግሥት እና ፓርቲ ለዝህ ጉዳይ በአድሱ ዓመት ችግሮቹን በመለየት ለችግሮቹ መብትሄና ምላሽ በመስጠት የጤና ባለሙያዎችን ጩሄት መልሰዉ መልካም ዜናን እንድያሰሙን ጥርያችን ነዉ።


*መስከ 7/2018 ዓ.ም--ዶ/ር ዩኒየን ድሪም

Address

Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Union Dream-DUD posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share