Visit Arba Minch

Visit Arba Minch promoting all aspects of hotel and tourism about Gamo Arba Minch and Ethiopia.

16/08/2025

Blessed Arba Minch 🌴🌱🌿🍀🍃

አዲስ የጀልባ ጉዞ መዳረሻ በአባያ ሐይቅ ወደ አባያ ወሽመጥ (ሞጬ ደሴት)መነሻዎን ከአርባምንጭ አዞ ራንች ጀርባ በማድረግ አባያ ሐይቅን እየቀዘፉ በሐይቁ ሌላኛው ዳርቻ ወደሚገኘው ወሽመጥ (ሞ...
31/05/2025

አዲስ የጀልባ ጉዞ መዳረሻ በአባያ ሐይቅ ወደ አባያ ወሽመጥ (ሞጬ ደሴት)

መነሻዎን ከአርባምንጭ አዞ ራንች ጀርባ በማድረግ አባያ ሐይቅን እየቀዘፉ በሐይቁ ሌላኛው ዳርቻ ወደሚገኘው ወሽመጥ (ሞጬ ደሴት) የሚደረግ የጀልባ ጉዞን የጋሞ ልማት ማሕበር አስጀምሯል።

ከጀልባ ጉዞው አስቀድሞ ከአዞ በተጨማሪ በራንቹ የተካተቱ እንደ አሳማ ፣ ጥንቸል ፣ ዘንዶ የመሳሰሉ እንስሳዎችን ይጎበኛሉ።

ቀጥሎ በጥቅጥቅ ደኑ ውስጥ እንደ ጉሬዛ ጦጣ እና ዝንጀሮ የመሳሰሉ የዱር ሕይወቶች ጋር እያወጉ ለአንድ ኪሎ ሜትር ያህል የእግር ጉዞ አድርገው ከሐይቁ ዳርቻ ጀልባ መሳፈርያ ይደርሳሉ።

በጀልባ ጉዞው ጉማሬ ፣ አዞ እና አእዋፍትን ጨምሮ የተለያዩ የውሃ ውስጥ ሕይወቶችን ይቃኛሉ። የአባያ ሐይቅ ድፍርስ ውሃን በድፍረት ይቀዝፋሉ። የሞጨ ደሴትንም ይረግጣሉ።

ከጉዞዎ መልስ እዛው በአዞ ራንች ግቢ ውስጥ ፍሬሽ የአባያ አሳ እየተመገቡ ከቡናውም ከገብሱም መጎንጨት ይችላሉ።

የጋሞ ልማት ማሕበር አዞ ራንችን ከተረከበ ጀምሮ ጥሩ ለውጦች በማድረግ ላይ ይገኛል። እናመሠግናለን !

ይህንን ስፍራ በቅርቡ ከአንጋፋው Bayra Hiking ጋር ለመጎብኘት ይዘጋጁ!

Bayra Hiking and Tours

ARBA MINCH❤️
10/12/2024

ARBA MINCH❤️

I LOVE ARBAMINCH !I LOVE GAMO !
05/12/2024

I LOVE ARBAMINCH !
I LOVE GAMO !

ARBA MINCHGamo Square, Inaugurated !
05/12/2024

ARBA MINCH
Gamo Square, Inaugurated !

03/12/2024

ለብሔረሰቦች ቀን አጥቢያ የሚመረቀው 'ጋሞ አደባባይ'
አርባምንጭ

29/11/2024

የማያረጅ ውበት የማያልቅ ቁንጅና
የማይደርቅ የማይነጥፍ ለዘመን የጸና 🧡
አርባ ምንጭ 🚣‍♂️ 💦

27/11/2024

Vist Arba Minch
Land of paradise !

26/11/2024

ሕዳር 29 የብሔር 19 ነኛውን ብሔረሰቦችን ቀን በድምቀት ለማክበር ዝግጅቷን ያጠናቀቀች ውብ ከተማ

22/11/2024

አርባምንጭ አዞ ራንች 🐊

በ 1976 ዓ.ም የተቋቋመው አርባምንጭ አዞ ራንች በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ሲሆን የናይል አዞ ስነ ሕይወትን ለመጠበቅ ፣ ለጥናት እና ምርምር ፣ በአዞ ቆዳ እና ስጋ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት እንዲሁም ቱራስቶችን በማስጎብኘት ከቱሪዝሙ ገብ ለማግኘት ታልሞ የተቋቋመ ነው!

በአሁን ሰዓት የተሻለ አገልግልት ለመስጠት እንዲያስችል በጋሞ ልማት ማህበር እየተመራ የለ ሲሆን እድሳት ተደርጎለት ለ19ኛው ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል !

ምድረ ገነት አርባምንጭን ይጎብኙ !

19/11/2024

Gamo - Land of Peace and Art !
Arba Minch - Land of Paradise !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎችን በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እየተመራ እንዲያከናውን የኢ/እ/ፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮ...
23/10/2024

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎችን በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እየተመራ እንዲያከናውን የኢ/እ/ፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ አሳልፏል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ላለፉት 12 ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ሲሰሩ እንደቆዩ የሚታወቅ ሲሆን ቡድናችን ከኤርትራ ጋር የሚያከናውናቸውን ጨዋታዎች ጨምሮ የቻን ማጣርያን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት የሚመሩ ይሆናል።

Via Ethiopian Football Federation

Address

Arba Minch
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Arba Minch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Visit Arba Minch:

Share

ነጭ ሳርን እንታደግ!

promoting tourist attractions and accomodation of Arba Minch,Gamo, Ethiopia .