19/08/2026
የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀምራል!)
በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ፣ ረቡዕ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም ይጀመራል።
በአርባምንጭ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም አምሳሉ እንዳስታወቁት፣ ምዝገባው ከነሐሴ 13-30/2018 ይካሄዳል።
በከተማዋ ባሉ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ፋይዳ መታወቂያ ይዘው እንዲገኙ እና ከ1ኛ–12ኛ ክፍል ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎች በተቀመጠላቸው ቀን የተማሪ ካርዳቸውን በመያዝ በወቅቱ እንዲመዘገቡ መምሪያው አሳስቧል።
የወላጆች ሚናም ወሳኝ ነው! ወላጆች ልጆቻቸውን በተጠቀሱት ቀናት በፍጥነት በማስመዝገብ፣ ትምህርት በወቅቱ እንዲጀመርና የትምህርት ብክነት እንዳይፈጠር የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ መምሪያው ጥሪ አቅርቧል።
📚 ልጆቻችንን በወቅቱ እናስመዝግብ፤ የትምህርት ጊዜን እንጠብቅ!
አርባምንጭ ከተማ ትምህርት መምሪያ